ዕዝራ 8:33 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) በአራተኛውም ቀን ብሩና ወርቁ፥ ዕቃዎቹም በአምላካችን ቤት በካህኑ በኦርያ ልጅ በሜሪሞት እጅ ተመዘኑ፤ ከእርሱም ጋር የፊንሐስ ልጅ አልዓዛር ነበረ፤ ከእነርሱም ጋር ሌዋውያን የኢያሱ ልጅ ኢዮዛብድና የቤንዊ ልጅ ናሕድያ ነበሩ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም በአራተኛው ቀን ብሩን፣ ወርቁንና ንዋያተ ቅድሳቱን በአምላካችን ቤት መዝነን ለኦርዮ ልጅ ለካህኑ ለሜሪሞት በእጁ አስረከብነው፤ ከርሱም ጋራ የፊንሐስ ልጅ አልዓዛር፣ ሌዋውያኑ የኢያሱ ልጅ ዮዛባትና የቢንዊ ልጅ ኖዓድያ ነበሩ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) በአራተኛውም ቀን ብሩ፥ ወርቁና ዕቃዎቹም በአምላካችን ቤት በካህኑ በኡሪያ ልጅ በምሬሞት እጅ ተመዘነ፤ ከእርሱም ጋር የፊንሐስ ልጅ አልዓዛር ነበረ። ከእነርሱም ጋር ሌዋውያኑ የኢያሱ ልጅ ዮዛባድና የቢኑይ ልጅ ኖዓድያ ነበሩ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ከዚህም በኋላ በአራተኛው ቀን ወደ ቤተ መቅደስ ሄድን፤ ብሩን፥ ወርቁንና ንዋያተ ቅድሳቱንም ሁሉ መዝነን ለኡሪያ ልጅ ለካህኑ ለመሬሞት አስረከብነው፤ የፊንሐስ ልጅ አልዓዛርና እንዲሁም ሌዋውያኑ ዮዛባድ ተብሎ የሚጠራው የኢያሱ ልጅና ኖዓዲያ ተብሎ የሚጠራው የቢኑይ ልጅ ከእርሱ ጋር አብረው ነበሩ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) በአራተኛውም ቀን ብሩና ወርቁ፥ ዕቃዎቹም በአምላካችን ቤት በካህኑ በኦርዮ ልጅ በሜሪሞት እጅ ተመዘኑ፤ ከእርሱም ጋር የፊንሐስ ልጅ አልዓዛር ነበረ። ከእነርሱም ጋር ሌዋውያን የኢያሱ ልጅ ዮዛባትና የቢንዊ ልጅ ኖዓድያ ነበሩ። |
ንጉሡና አማካሪዎቹ፥ አለቆቹም፥ በዚያም የተገኙት እስራኤል ሁሉ ያቀረቡትን፥ ለአምላካችን ቤት የቀረበውን ብሩንና ወርቁን፥ ዕቃውንም መዝኜ ሰጠኋቸው።
በካህናትና በሌዋውያን አለቆች፥ በእስራኤልም አባቶች ቤቶች አለቆች ፊት በኢየሩሳሌም በእግዚአብሔር ቤት ጓዳዎች ውስጥ እስክትመዝኑ ድረስ ተግታችሁ ጠብቁ” አልኋቸው።
ካህናቱና ሌዋውያኑም ወደ ኢየሩሳሌም ወደ አምላካችን ቤት ይወስዱት ዘንድ ብሩንና ወርቁን፥ ዕቃዎቹንም በሚዛን ተቀበሉ።
ከእርሱም በኋላ የአቆስ ልጅ የኡርያ ልጅ ሚራሞት ከኤልያሴብ ቤት መግቢያ ጀምሮ እሰከ ኤልያሴብ ቤት መጨረሻ ድረስ ሌላውን ክፍል ሠራ።
ከእርሱም በኋላ የኢንሓዳድ ልጅ ባኒ ከዓዛርያስ ቤት ጀምሮ እስከ ማዕዘኑ እስከ ግንቡመዞሪያ ድረስ ያለውን ሌላውን ክፍል ሠራ።
በአጠገባቸውም የቆስ ልጅ የኡርያ ልጅ ሚራሞት ይሠራ ጀመረ። በአጠገባቸውም የሜሴዜቤል ልጅ የበራክያ ልጅ ሜሱላም ይሠራ ጀመረ። በአጠገባቸውም የበሃና ልጅ ሳዶቅ ይሠራ ጀመረ።
ደግሞ ኢያሱና ባኒ፥ ሰራብያ፥ ያሚን፥ ዓቁብ፥ ሳባታይ፥ ሆዲያ፥ መዕሤያ፥ ቆሊጣ፥ ዓዛርያ፥ ኢዮዛባድ፥ ሐናን፥ ፌልዕያ፥ ሌዋውያኑም ሕጉን ለሕዝቡ ያስተምሩ ነበር፤ ሕዝቡም በየስፍራቸው ቆመው ነበር።