La Biblia Online

Anuncios


Toda la Biblia A.T. N.T.




ዕዝራ 4:24 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

በዚ​ያን ጊዜም በኢ​የ​ሩ​ሳ​ሌም ያለው የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ቤት ሥራ ተቋ​ረጠ፤ እስከ ፋር​ስም ንጉሥ እስከ ዳር​ዮስ መን​ግ​ሥት እስከ ሁለ​ተ​ኛው ዓመት ድረስ ተጓ​ጐለ።

Ver Capítulo

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

ስለዚህም በኢየሩሳሌም የሚሠራው የእግዚአብሔር ቤት ሥራ እስከ ፋርስ ንጉሥ እስከ ዳርዮስ ዘመነ መንግሥት ሁለተኛ ዓመት ድረስ ተቋረጠ።

Ver Capítulo

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

በዚያን ጊዜም በኢየሩሳሌም ያለው የእግዚአብሔር ቤት ሥራ ቀረ፤ እስከ ፋርስም ንጉሥ እስከ ዳርዮስ መንግሥት እስከ ሁለተኛው ዓመት ድረስ ተቋረጠ።

Ver Capítulo

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

ስለዚህ ዳርዮስ በፋርስ እስከ ነገሠበት እስከ ሁለተኛው ዓመት ድረስ የቤተ መቅደሱ ሥራ በመቋረጡ በጅምር ቀርቶ ነበር።

Ver Capítulo

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

በዚያን ጊዜም በኢየሩሳሌም ያለው የእግዚአብሔር ቤት ሥራ ቀረ፤ እስከ ፋርስም ንጉሥ እስከ ዳርዮስ መንግሥት እስከ ሁለተኛው ዓመት ድረስ ተጓጐለ።

Ver Capítulo



ዕዝራ 4:24
19 Referencias Cruzadas  

በኢ​የ​ሩ​ሳ​ሌ​ምም ወዳ​ለው ወደ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ቤት በመጡ በሁ​ለ​ተ​ኛው ዓመት በሁ​ለ​ተ​ኛ​ውም ወር የሰ​ላ​ት​ያል ልጅ ዘሩ​ባ​ቤል፥ የኢ​ዮ​ሴ​ዴ​ቅም ልጅ ኢያሱ፥ የቀ​ሩ​ትም ወን​ድ​ሞ​ቻ​ቸው ካህ​ና​ትና ሌዋ​ው​ያን፥ ከም​ርኮ ወደ ኢየ​ሩ​ሳ​ሌ​ምም የተ​መ​ለ​ሱት ሁሉ ጀመሩ፤ ሌዋ​ው​ያ​ን​ንም ከሃያ ዓመት ጀምሮ ከዚ​ያም በላይ የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ቤት ሥራ እን​ዲ​ያ​ሠ​ሩት ሾሙ​አ​ቸው።


የን​ጉ​ሡም የአ​ር​ተ​ሰ​ስታ መል​እ​ክ​ተኛ በደ​ረሰ ጊዜ በአ​ዛዡ በሬ​ሁ​ምና በጸ​ሓ​ፊው በሲ​ም​ሳይ፥ በተ​ባ​ባ​ሪ​ዎ​ቻ​ቸ​ውም ፊት መል​እ​ክ​ቱን ባነ​በበ ጊዜ ፈጥ​ነው ወደ ኢየ​ሩ​ሳ​ሌም ወደ አይ​ሁድ በፈ​ረስ ሄዱ፤ በኀ​ይ​ልም አስ​ተ​ዉ​አ​ቸው።


ምክ​ራ​ቸ​ው​ንም ያፈ​ርሱ ዘንድ በፋ​ርሱ ንጉሥ በቂ​ሮስ ዘመን ሁሉ እስከ ፋርስ ንጉሥ እስከ ዳር​ዮስ መን​ግ​ሥት ድረስ መካ​ሪ​ዎ​ችን ገዙ​ባ​ቸው።


ነቢ​ያቱ ሐጌና የአዶ ልጅ ዘካ​ር​ያስ በይ​ሁ​ዳና በኢ​የ​ሩ​ሳ​ሌም ለነ​በሩ አይ​ሁድ በእ​ስ​ራ​ኤል አም​ላክ ስም ትን​ቢት ተና​ገ​ሩ​ላ​ቸው።


የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ዐይን ግን በይ​ሁዳ ምር​ኮ​ኞች ላይ ነበረ፤ ይህም ነገር ወደ ዳር​ዮስ እስ​ኪ​ደ​ርስ ድረስ፥ መል​ሱም በመ​ል​እ​ክ​ተኛ እስ​ኪ​መጣ ድረስ አል​ከ​ለ​ከ​ሉ​አ​ቸ​ውም።


በዚያ ጊዜም ንጉሡ ዳር​ዮስ በባ​ቢ​ሎን ቤተ መዛ​ግ​ብት ያሉ የታ​ሪክ መጻ​ሕ​ፍት እን​ዲ​መ​ረ​መሩ አዘዘ።


የአ​ይ​ሁድ ሽማ​ግ​ሌ​ዎ​ችና ሌዋ​ው​ያ​ንም በነ​ቢዩ በሐ​ጌና በአዶ ልጅ በዘ​ካ​ር​ያስ ትን​ቢት መሠ​ረት ሠሩ፤ ተከ​ና​ወ​ነ​ላ​ቸ​ውም። እንደ እስ​ራ​ኤ​ልም አም​ላክ ትእ​ዛዝ፥ እንደ ፋር​ስም ነገ​ሥ​ታት እንደ ቂሮ​ስና እንደ ዳር​ዮስ፥ እንደ አር​ተ​ሰ​ስ​ታም ትእ​ዛዝ ሠር​ተው ፈጸሙ።


ይህም ቤት በን​ጉሡ በዳ​ር​ዮስ መን​ግ​ሥት በስ​ድ​ስ​ተ​ኛው ዓመት አዳር በሚ​ባል ወር በሦ​ስ​ተ​ኛው ቀን ተፈ​ጸመ።


እኔም እን​ዲህ ስል መል​እ​ክ​ተ​ኞ​ችን ላክ​ሁ​ባ​ቸው፥ “እኔ ታላቅ ሥራ እሠ​ራ​ለሁ፤ እወ​ር​ድም ዘንድ አይ​ቻ​ለ​ኝም። ስለ​ምን ወደ እና​ንተ በመ​ም​ጣ​ቴና በመ​ው​ረዴ ሥራው ይታ​ጐ​ላል? ሥራ​ውን እንደ ፈጸ​ምሁ እመ​ጣ​ለሁ።”


እነ​ር​ሱም ሁሉ ሥራው እን​ዳ​ይ​ፈ​ጸም፥ “እጃ​ቸው ይደ​ክ​ማል” ብለው አስ​ፈ​ራ​ሩን፤ ስለ​ዚ​ህም እጆ​ችን አበ​ረ​ታሁ።


የኀ​ጢ​ኣ​ተ​ኞች ደስታ ታላቅ ሰልፍ ነው፥ የዝ​ን​ጉ​ዎ​ችም ደስታ ጥፋት ነው።


በንጉሡ በዳርዮስ በሁለተኛው ዓመት በስድስተኛው ወር ከወሩም በመጀመሪያው ቀን የእግዚአብሔር ቃል በነቢዩ በሐጌ እጅ ወደ ይሁዳ አለቃ ወደ ሰላትያል ልጅ ወደ ዘሩባቤል፥ ወደ ታላቁም ካህን ወደ ኢዮሴዴቅ ልጅ ወደ ኢያሱ እንዲህ ሲል መጣ፦


አሁንም ድንጋይ በድንጋይ ላይ በእግዚአብሔር መቅደስ ሳይነባበር፥ ከዛሬ ጀምራችሁ ወዳለፈው ዘመን ልብ አድርጉ።


ከዛሬው ከዘጠነኛው ወር ከሀያ አራተኛው ቀን ጀምራችሁ የሚመጣውን ዘመን ልብ አድርጉ፣ የእግዚአብሔር መቅደስ መሠረት ከተተከለበት ቀን ጀምሮ ልብ አድርጉ።


በዳርዮስ በሁለተኛው ዓመት በስምንተኛው ወር የእግዚአብሔር ቃል ወደ አዶ ልጅ ወደ በራክዩ ልጅ ወደ ነቢዩ ወደ ዘካርያስ እንዲህ ሲል መጣ፦


ወደ እናንተ ልንመጣ ወደን ነበርና፤ እኔ ጳውሎስም አንድና ሁለት ጊዜ፥ ሰይጣን ግን አዘገየን።