Biblia Todo Logo
La Biblia Online

- Anuncios -




ዕዝራ 4:24 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

24 በዚያን ጊዜም በኢየሩሳሌም ያለው የእግዚአብሔር ቤት ሥራ ቀረ፤ እስከ ፋርስም ንጉሥ እስከ ዳርዮስ መንግሥት እስከ ሁለተኛው ዓመት ድረስ ተቋረጠ።

Ver Capítulo Copiar

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

24 ስለዚህም በኢየሩሳሌም የሚሠራው የእግዚአብሔር ቤት ሥራ እስከ ፋርስ ንጉሥ እስከ ዳርዮስ ዘመነ መንግሥት ሁለተኛ ዓመት ድረስ ተቋረጠ።

Ver Capítulo Copiar

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

24 ስለዚህ ዳርዮስ በፋርስ እስከ ነገሠበት እስከ ሁለተኛው ዓመት ድረስ የቤተ መቅደሱ ሥራ በመቋረጡ በጅምር ቀርቶ ነበር።

Ver Capítulo Copiar

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

24 በዚ​ያን ጊዜም በኢ​የ​ሩ​ሳ​ሌም ያለው የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ቤት ሥራ ተቋ​ረጠ፤ እስከ ፋር​ስም ንጉሥ እስከ ዳር​ዮስ መን​ግ​ሥት እስከ ሁለ​ተ​ኛው ዓመት ድረስ ተጓ​ጐለ።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

24 በዚያን ጊዜም በኢየሩሳሌም ያለው የእግዚአብሔር ቤት ሥራ ቀረ፤ እስከ ፋርስም ንጉሥ እስከ ዳርዮስ መንግሥት እስከ ሁለተኛው ዓመት ድረስ ተጓጐለ።

Ver Capítulo Copiar




ዕዝራ 4:24
19 Referencias Cruzadas  

ይህም በንጉሡ በዳርዮስ በሁለተኛው ዓመት፥ በስድስተኛው ወር ከወሩም በሀያ አራተኛው ቀን ነው።


የክፉ ሰዎች ፉከራ አጭር መሆኑን አምላክን የሚክዱ ደስታቸው ቅጽበት መሆኑን አታውቁምን?


ሁሉም እንዲህ እያሉ አስፈራሩን፦ “ከሥራው እጃቸውን ያላላሉ፥ አይሠራምም” አሁንም እጄን አበርታ።


እኔም እንዲህ ብዬ መልእክተኞችን ላክሁባቸው፦ “ትልቅ ሥራ እሠራለሁ፥ መውረድም አልችልም፤ ሥራውን ትቼ ወደ እናንተ በመውረዴ ሥራው ለምን ይቆማል?”


በዚን ጊዜ ንጉሡ ዳርዮስ ትእዛዝ አስተላለፈ። በባቢሎን መዛግብት ባሉበት ቤተ መጻሕፍት ምርመራ ተደረገ።


የአምላካቸው ዐይን ግን በአይሁድ ሽማግሌዎች ላይ ነበረ፥ ይህም ነገር ወደ ዳርዮስ እስኪደርስ ድረስ፥ መልሱም በደብዳቤ እስኪመጣ ድረስ አላስቆሙአቸውም።


ወደ እናንተ ልንመጣ ፈልገን ነበርና፤ በእርግጥም እኔ ጳውሎስ አንድና ሁለት ጊዜ ሞክሬ ነበር፥ ሰይጣን ግን መሰናክል ሆነብን።


የንጉሡም የአርጤክስስ ደብዳቤ ግልባጭ በሬሑምና በጸሐፊው በሺምሻይ በተባባሪዎቻቸውም ፊት በተነበበ ጊዜ ፈጥነው ወደ ኢየሩሳሌም ወደ አይሁድ ሄዱ፤ በግድና በኃይልም አስተዉአቸው።


ነቢያቱ ሐጌና የዒዶ ልጅ ዘካርያስ በይሁዳና በኢየሩሳሌም ለነበሩ አይሁድ በእነርሱ ላይ በነበረው በእስራኤል አምላክ ስም ትንቢት ተናገሩላቸው።


የአይሁድም ሽማግሌዎች በነቢዩ ሐጌና በዒዶ ልጅ በዘካርያስ ትንቢት እየተበረታቱ ሠሩ ተከናወነላቸውም። በእስራኤል አምላክ ትእዛዝ፥ እንደ ቂሮስ ትእዛዝ እንደ ዳርዮስ እንደ አርጤክስስ የፋርስ ንጉሥ ትእዛዝ ሠርተው ፈጸሙ።


በንጉሡ በዳርዮስ በሁለተኛው ዓመት በስድስተኛው ወር ከወሩም በመጀመሪያው ቀን የጌታ ቃል በነቢዩ በሐጌ እጅ ወደ ይሁዳ ገዢ ወደ ሰላትያል ልጅ ወደ ዘሩባቤልና ወደ ታላቁ ካህን ወደ ኢዮሴዴቅ ልጅ ወደ ኢያሱ እንዲህ ሲል መጣ፦


አሁንም ከዛሬ ጀምራችሁ ወደ ፊት ልብ አድርጉ፥ በጌታ መቅደስ ድንጋይ በድንጋይ ላይ ከመቀመጡ በፊት፥


ዳርዮስ በነገሠ በሁለተኛው ዓመት፥ በስምንተኛው ወር፥ የጌታ ቃል ወደ አዶ ልጅ ወደ በራክዩ ልጅ ወደ ነቢዩ ወደ ዘካርያስ እንዲህ ሲል መጣ፦


በኢየሩሳሌም ወዳለው ወደ እግዚአብሔር ቤት በመጡ በሁለተኛው ዓመት በሁለተኛውም ወር የሸአልቲኤል ልጅ ዘሩባቤል፥ የዮፃዳቅም ልጅ ኢያሱ፥ የቀሩትም ወንድሞቻቸው ካህናትና ሌዋውያን፥ ወደ ኢየሩሳሌምም የተመለሱት ምርኮኞች ሁሉ፥ ሌዋውያንንም ከሀያ ዓመት ጀምሮ ከዚያም በላይ የጌታን ቤት ሥራ እንዲቆጣጠሩ መረጧቸው።


ከቂሮስ የፋርሱ ንጉሥ ዘመን ሁሉ ጀምሮ እስከ ዳርዮስ የፋርስ ንጉሥ መንግሥት ድረስ ሥራቸውን እንዲያፈርሱ ባለሥልጣኖችን ቀጠሩባቸው።


ይህም ቤት በንጉሡ በዳርዮስ መንግሥት በስድስተኛው ዓመት አዳር በሚባል ወር በሦስተኛው ቀን ተፈጸመ።


ከዛሬው ከዘጠነኛው ወር ከሀያ አራተኛው ቀን ጀምራችሁ የሚመጣውን ጊዜ ልብ በሉ፤ የጌታ መቅደስ መሠረት ከተጣለበት ቀን ጀምሮ ልብ አድርጉ።


Síguenos en:

Anuncios


Anuncios