Biblia Todo Logo
La Biblia Online

- Anuncios -




ዕዝራ 5:1 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

1 ነቢ​ያቱ ሐጌና የአዶ ልጅ ዘካ​ር​ያስ በይ​ሁ​ዳና በኢ​የ​ሩ​ሳ​ሌም ለነ​በሩ አይ​ሁድ በእ​ስ​ራ​ኤል አም​ላክ ስም ትን​ቢት ተና​ገ​ሩ​ላ​ቸው።

Ver Capítulo Copiar

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

1 በዚያ ጊዜ ነቢዩ ሐጌና የአዶ ልጅ ነቢዩ ዘካርያስ፣ በይሁዳና በኢየሩሳሌም ለሚኖሩ አይሁድ ከእነርሱ በላይ በሆነው በእስራኤል አምላክ ስም ትንቢት ተናገሩላቸው።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

1 ነቢያቱ ሐጌና የዒዶ ልጅ ዘካርያስ በይሁዳና በኢየሩሳሌም ለነበሩ አይሁድ በእነርሱ ላይ በነበረው በእስራኤል አምላክ ስም ትንቢት ተናገሩላቸው።

Ver Capítulo Copiar

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

1 በዚያን ጊዜ ሁለቱ ነቢያት፥ ሐጌና የዒዶ ልጅ ዘካርያስ በኢየሩሳሌምና በይሁዳ ምድር ለሚኖሩ አይሁድ፥ ስለ ቤተ መቅደሱ ሥራ ጉዳይ በእስራኤል አምላክ ስም ትንቢት ተናገሩላቸው።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

1 ነቢያቱም ሐጌና የአዶ ልጅ ዘካርያስ በይሁዳና በኢየሩሳሌም ለነበሩ አይሁድ በእስራኤል አምላክ ስም ትንቢት ተናገሩላቸው።

Ver Capítulo Copiar




ዕዝራ 5:1
9 Referencias Cruzadas  

በንጉሡ በዳርዮስ በሁለተኛው ዓመት በስድስተኛው ወር ከወሩም በመጀመሪያው ቀን የእግዚአብሔር ቃል በነቢዩ በሐጌ እጅ ወደ ይሁዳ አለቃ ወደ ሰላትያል ልጅ ወደ ዘሩባቤል፥ ወደ ታላቁም ካህን ወደ ኢዮሴዴቅ ልጅ ወደ ኢያሱ እንዲህ ሲል መጣ፦


እርሱም ይቆማል፥ በእግዚአብሔርም ኃይል በአምላኩ በእግዚአብሔር ስም ግርማ መንጋውን ይጠብቃል፥ እነርሱም ይኖራሉ፥ እርሱ አሁን እስከ ምድር ዳርቻ ድረስ ታላቅ ይሆናልና።


በዚ​ያን ጊዜም በኢ​የ​ሩ​ሳ​ሌም ያለው የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ቤት ሥራ ተቋ​ረጠ፤ እስከ ፋር​ስም ንጉሥ እስከ ዳር​ዮስ መን​ግ​ሥት እስከ ሁለ​ተ​ኛው ዓመት ድረስ ተጓ​ጐለ።


የአ​ይ​ሁድ ሽማ​ግ​ሌ​ዎ​ችና ሌዋ​ው​ያ​ንም በነ​ቢዩ በሐ​ጌና በአዶ ልጅ በዘ​ካ​ር​ያስ ትን​ቢት መሠ​ረት ሠሩ፤ ተከ​ና​ወ​ነ​ላ​ቸ​ውም። እንደ እስ​ራ​ኤ​ልም አም​ላክ ትእ​ዛዝ፥ እንደ ፋር​ስም ነገ​ሥ​ታት እንደ ቂሮ​ስና እንደ ዳር​ዮስ፥ እንደ አር​ተ​ሰ​ስ​ታም ትእ​ዛዝ ሠር​ተው ፈጸሙ።


ከዛሬው ከዘጠነኛው ወር ከሀያ አራተኛው ቀን ጀምራችሁ የሚመጣውን ዘመን ልብ አድርጉ፣ የእግዚአብሔር መቅደስ መሠረት ከተተከለበት ቀን ጀምሮ ልብ አድርጉ።


የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ መቅደሱ ይሠራ ዘንድ የሠራዊት ጌታ የእግዚአብሔር ቤት ከተመሠረተበት ቀን ጀምሮ ከነቢያት አፍ ይህን ቃል በዚህ ዘመን የሰማችሁ እናንተ ሆይ፥ እጃችሁን አበርቱ።


የእግዚአብሔርም ቃል በነቢዩ በሐጌ እጅ እንዲህ ሲል መጣ፦


Síguenos en:

Anuncios


Anuncios