Biblia Todo Logo
La Biblia Online
- Anuncios -




ዕዝራ 6:1 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

1 በዚያ ጊዜም ንጉሡ ዳር​ዮስ በባ​ቢ​ሎን ቤተ መዛ​ግ​ብት ያሉ የታ​ሪክ መጻ​ሕ​ፍት እን​ዲ​መ​ረ​መሩ አዘዘ።

Ver Capítulo Copiar

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

1 ከዚያም ንጉሥ ዳርዮስ በባቢሎን ግምጃ ቤት የተቀመጡት መዛግብት እንዲመረመሩ ትእዛዝ ሰጠ።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

1 በዚን ጊዜ ንጉሡ ዳርዮስ ትእዛዝ አስተላለፈ። በባቢሎን መዛግብት ባሉበት ቤተ መጻሕፍት ምርመራ ተደረገ።

Ver Capítulo Copiar

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

1 በባቢሎን ቤተ መንግሥት የሚገኙ መዛግብት ሁሉ ይመረመሩ ዘንድ ንጉሠ ነገሥት ዳርዮስ ትእዛዝ አስተላለፈ፤

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

1 በዚያ ጊዜም ንጉሡ ዳርዮስ መዛግብት ባሉበት በባቢሎን ቤተ መጻሕፍት እንዲመረመር አዘዘ።

Ver Capítulo Copiar




ዕዝራ 6:1
16 Referencias Cruzadas  

በአ​ባ​ቶ​ችህ ታሪክ መጽ​ሐፍ ምር​መራ ይደ​ረግ፤ በዚ​ያም በታ​ሪክ መጽ​ሐፍ ይህች ከተማ ዐመ​ፀኛ እንደ ሆነች፥ ነገ​ሥ​ታ​ት​ንና አው​ራ​ጃ​ዎ​ች​ንም እንደ ጎዳች፥ ከጥ​ን​ቱም የገ​ባ​ሮች ሽፍ​ት​ነት በእ​ር​ስዋ እንደ ተጀ​መረ ታገ​ኛ​ለህ፤ ታው​ቃ​ለ​ህም፤ ስለ​ዚ​ህም ይህች ከተማ ፈርሳ ነበር።


እኔም አዝ​ዣ​ለሁ፤ ተመ​ረ​መ​ረም፤ ይህ​ችም ከተማ ከጥ​ንት ጀምራ በነ​ገ​ሥ​ታት ላይ ዐመ​ፀኛ እንደ ነበ​ረች፥ በእ​ር​ስ​ዋም ዐመ​ፅና ሽፍ​ት​ነት እንደ ተደ​ረገ ተገኘ።


አሁ​ንም ይህ ነገር በን​ጉሡ ዐይን መል​ካም ቢሆን ይህ የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ቤት በኢ​የ​ሩ​ሳ​ሌም ይሠራ ዘንድ ከን​ጉሡ ከቂ​ሮስ ታዝዞ እንደ ሆነ በባ​ቢ​ሎን ባለው በን​ጉሡ ቤተ መዛ​ግ​ብት ይመ​ር​መር፤ ስለ​ዚ​ህም ነገር ንጉሡ ፈቃ​ዱን ይላ​ክ​ልን።”


እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ደስ አሰ​ኝ​ቶ​አ​ቸ​ዋ​ልና፥ የእ​ስ​ራ​ኤ​ል​ንም አም​ላክ የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ቤት ለመ​ሥ​ራት እጃ​ቸ​ውን ያጸና ዘንድ የአ​ሦ​ርን ንጉሥ ልብ ወደ እነ​ርሱ መል​ሶ​አ​ልና የቂ​ጣ​ውን በዓል ሰባት ቀን በደ​ስታ አደ​ረጉ።


በመ​ን​ግ​ሥ​ቴም ውስጥ ካሉ ከእ​ስ​ራ​ኤል ሕዝብ ከካ​ህ​ና​ቱና ከሌ​ዋ​ው​ያኑ ወደ ኢየ​ሩ​ሳ​ሌም ይሄድ ዘንድ የሚ​ወ​ድድ ሁሉ ከአ​ንተ ጋር እን​ዲ​ሄድ አዝ​ዣ​ለሁ።


ለድ​ሃ​ዎች አባት ነበ​ርሁ፥ የማ​ላ​ው​ቀ​ው​ንም ሰው ክር​ክር መረ​መ​ርሁ።


ጠላ​ቶ​ቼም ሁሉ ይጠ​ቃ​ቀ​ሱ​ብ​ኛል፥ በእኔ ላይም ክፋ​ትን ይመ​ክ​ራሉ።


የይ​ሁ​ዳ​ንም ንጉሥ ኢዮ​አ​ቄ​ምን እን​ዲህ በለው፦ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እን​ዲህ ይላል፦ አንተ፦ የባ​ቢ​ሎን ንጉሥ በር​ግጥ ይመ​ጣል፤ ይች​ንም ሀገር ያፈ​ር​ሳ​ታል፤ ሰውና እን​ስ​ሳም ያል​ቃሉ ብለህ ለምን ጻፍ​ህ​በት? ብለህ ይህን ክር​ታስ አቃ​ጥ​ለ​ሃል።


ኤር​ም​ያ​ስም ሌላ ክር​ታስ ወሰደ፤ ለኔ​ር​ዩም ልጅ ለጸ​ሓ​ፊው ለባ​ሮክ ሰጠው፤ እር​ሱም የይ​ሁዳ ንጉሥ ኢዮ​አ​ቄም በእ​ሳት ያቃ​ጠ​ለ​ውን የመ​ጽ​ሐ​ፉን ቃል ሁሉ ከኤ​ር​ም​ያስ አፍ ጻፈ​በት፤ ደግ​ሞም እንደ ቀድ​ሞው ያለ ቃል ብዙ ቃል ተጨ​መ​ረ​በት።


በአ​የ​ሁም ጊዜ፥ እነሆ እጅ ወደ እኔ ተዘ​ር​ግታ ነበር፤ እነ​ሆም የመ​ጽ​ሐፍ ጥቅ​ልል ነበ​ረ​ባት።


እር​ሱም፥ “የሰው ልጅ ሆይ! ያገ​ኘ​ኸ​ውን ብላ፤ ይህን መጽ​ሐፍ ብላ፤ ሄደ​ህም ለእ​ስ​ራ​ኤል ልጆች ተና​ገር” አለኝ።


በዙፋኑ ላይም በተቀመጠው በቀኝ እጁ ላይ በውስጥና በኋላ የተጻፈበት በሰባትም ማኅተም የተዘጋ መጽሐፍን አየሁ።


Síguenos en:

Anuncios


Anuncios


¡Síguenos en WhatsApp! Síguenos