ሕዝቤን እስራኤልን ከግብፅ ምድር ካወጣሁበት ቀን ጀምሮ እስከ ዛሬ ድረስ በድንኳንና በማደሪያ ኖርሁ እንጂ በቤት ውስጥ አልኖርሁም።
ዘፀአት 40:2 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) “በመጀመሪያው ወር በፊተኛው ቀን የምስክሩን ድንኳን ትተክላለህ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም “ማደሪያውን ይኸውም የመገናኛውን ድንኳን በወሩ የመጀመሪያ ቀን ትከለው፤ መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) “በመጀመሪያው ወር በመጀመሪያው ቀን የመገናኛውን ድንኳን ማደሪያ ትተክላለህ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም “የመጀመሪያው ወር በገባ በመጀመሪያው ቀን የመገናኛውን ድንኳን ትከል። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ከመጀመሪያው ወር በፊተኛው ቀን የመገናኛውን ድንኳን ማደሪያ ትተክላለህ። |
ሕዝቤን እስራኤልን ከግብፅ ምድር ካወጣሁበት ቀን ጀምሮ እስከ ዛሬ ድረስ በድንኳንና በማደሪያ ኖርሁ እንጂ በቤት ውስጥ አልኖርሁም።
“ለድንኳኑም ከተፈተለ ከጥሩ በፍታ፥ ከሰማያዊ፥ ከሐምራዊም፥ ከቀይም ግምጃ ዐሥር መጋረጆችን ሥራ፤ ኪሩቤልም በእነርሱ ላይ ይሁኑ፤ እንደ ሽመና ሥራም በብልሃት ትሠራቸዋለህ።
በምስክሩ ድንኳን ውስጥ በቃል ኪዳኑ ታቦት ፊት ካለው መጋረጃ ውጭ አሮንና ልጆቹ ከማታ እስከ ማለዳ ድረስ በእግዚአብሔር ፊት ያብሩት፤ በእስራኤል ልጆች ዘንድ ለልጅ ልጃቸው የዘለዓለም ሥርዐት ይሁን።
ከእርሱም ጥቂት ትወቅጣለህ፤ ታልመውማለህ፤ ከዚያም ለአንተ በምገለጥበት በምስክሩ ድንኳን ውስጥ በምስክሩ ፊት ታኖረዋለህ። እርሱም ቅዱሰ ቅዱሳን ይሁንላችሁ።
ድንኳኑንም፥ አደባባዩንም፥ መደረቢያውንም፥ መያዣዎቹንም፥ ሳንቆቹንም፥ መወርወሪያዎቹንም፥ ምሰሶዎችንና እግሮቻቸውን፤
በተማረክን በሃያ አምስተኛው ዓመት በዓመቱ መጀመሪያ ከወሩ በዐሥረኛው ቀን፥ ከተማዪቱ ከተመታች በኋላ በዐሥራ አራተኛው ዓመት፥ በዚያው ቀን የእግዚአብሔር እጅ በእኔ ላይ ነበረ፤ እርሱም ወደዚያ ወሰደኝ።
ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፥ “በመጀመሪያው ወር ከወሩም በመጀመሪያው ቀን ከመንጋው ነውር የሌለበትን ወይፈን ውሰድ፤ መቅደሱንም አንጻ።
እግዚአብሔርም ሙሴን በሲና ምድረ በዳ በምስክሩ ድንኳን ውስጥ፥ በሁለተኛው ወር በመጀመሪያው ቀን፥ ከግብፅ ምድር ከወጡ በኋላ በሁለተኛው ዓመት እንዲህ ብሎ ተናገረው፦
እንዲህም ሆነ፤ ሙሴ ድንኳኑን ፈጽሞ በተከለባት፥ እርስዋንና ዕቃዋን ሁሉ በቀባና በቀደሰባት፥ መሠዊያውንና ዕቃውንም ሁሉ በቀባና በቀደሰባት ቀን፥
የእስራኤል ልጆች ከግብፅ ምድር በወጡ በሁለተኛው ዓመት በመጀመሪያው ወር በሲና ምድረ በዳ እግዚአብሔር ሙሴን እንዲህ ብሎ ተናገረው፦
ድንኳንዋን በተከሉበት ቀን ደመናው የምስክሩን ድንኳን ሸፈናት፤ ከማታም ጀምሮ እስከ ጥዋት ድረስ በድንኳኑ ላይ እንደ እሳት ይመስል ነበር።