Biblia Todo Logo
La Biblia Online

- Anuncios -




ዘፀአት 26:1 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

1 “ለድ​ን​ኳ​ኑም ከተ​ፈ​ተለ ከጥሩ በፍታ፥ ከሰ​ማ​ያዊ፥ ከሐ​ም​ራ​ዊም፥ ከቀ​ይም ግምጃ ዐሥር መጋ​ረ​ጆ​ችን ሥራ፤ ኪሩ​ቤ​ልም በእ​ነ​ርሱ ላይ ይሁኑ፤ እንደ ሽመና ሥራም በብ​ል​ሃት ትሠ​ራ​ቸ​ዋ​ለህ።

Ver Capítulo Copiar

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

1 “በቀጭኑ ከተፈተለ የበፍታ ድርና በሰማያዊ፣ በሐምራዊና በቀይ ማግ በተሠሩ ዐሥር መጋረጃዎች ማደሪያ ድንኳኑን ሥራ፤ እጀ ብልኅ ሠራተኛም ኪሩቤልን ይጥለፍባቸው።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

1 “ከተፈተለ ከጥሩ በፍታ፥ ከሰማያዊ፥ ከሐምራዊና ከቀይ ግምጃ የተሠሩ ዐሥር መጋረጆች ያሉበትን ድንኳን ሥራ፤ ብልህ ሠራተኛ እንደሚሠራ ኪሩቤል በእነርሱ ላይ ይሁኑ።

Ver Capítulo Copiar

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

1 “እንዲሁም የተቀደሰውን ድንኳን ውስጠኛ ክፍል ከሰማያዊ፥ ከሐምራዊና ከቀይ ከፈይ ከተፈተለ በፍታ በተሠሩ ዐሥር መጋረጃዎች አብጀው፤ በእነርሱም ላይ ኪሩቤል በጥልፍ ጥበብ እንዲሳሉ አድርግ።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

1 ደግሞም ከተፈተለ ከጥሩ በፍታ፥ ከሰማያዊ ከሐምራዊም ከቀይም ግምጃ የተሠሩ አሥር መጋረጆች ያሉበትን ማደሪያ ሥራ፤ ብልህ ሠራተኛ እንደሚሠራ ኪሩቤል በእነርሱ ላይ ይሁኑ።

Ver Capítulo Copiar




ዘፀአት 26:1
29 Referencias Cruzadas  

ለድ​ን​ኳኑ ደጃ​ፍም ከሰ​ማ​ያዊ፥ ከሐ​ም​ራ​ዊም፥ ከቀይ ግም​ጃም ከተ​ፈ​ተለ ከጥሩ በፍ​ም​ታም በጥ​ልፍ አሠ​ራር የተ​ሠራ መጋ​ረጃ አድ​ር​ግ​ለት።


መጋ​ረ​ጃ​ው​ንም ከሰ​ማ​ያ​ዊና ከሐ​ም​ራዊ፥ ከቀ​ይም ግምጃ፥ ከተ​ፈ​ተ​ለም ከጥሩ በፍታ አደ​ረጉ፤ ኪሩ​ቤ​ል​ንም በጥ​ልፍ ሥራ በእ​ርሱ ላይ አደ​ረጉ።


“መጋ​ረ​ጃ​ው​ንም ከሰ​ማ​ያዊ፥ ከሐ​ም​ራ​ዊም፥ ከቀ​ይም ግምጃ ከተ​ፈ​ተለ ከጥሩ በፍ​ታም አድ​ርግ፤ በሽ​መና ሥራም ኪሩ​ቤ​ልን ሥራ።


ሁለት ኪሩ​ቤል ከተ​ቀ​ጠ​ቀጠ ወርቅ ሥራ፤ በስ​ር​የት መክ​ደ​ኛ​ውም ላይ በሁ​ለት ወገን ታደ​ር​ጋ​ቸ​ዋ​ለህ።


ታላቅም ድምፅ ከሰማይ “እነሆ የእግዚአብሔር ድንኳን በሰዎች መካከል ነው፤ ከእነርሱም ጋር ያድራል፤ እነርሱም ሕዝቡ ይሆናሉ፤ እግዚአብሔርም እርሱ ራሱ ከእነርሱ ጋር ሆኖ አምላካቸው ይሆናል፤


ያጌጠና የተጣራ ቀጭን የተልባ እግር ልብስ እንድትጐናጸፍ ተሰጥቶአታል።” ቀጭኑ የተልባ እግር የቅዱሳን ጽድቅ ሥራ ነውና።


ነገር ግን ለሚ​ያ​ቀ​ር​በው ሰው ግዳጅ መፈ​ጸም የማ​ይ​ቻ​ለ​ውን መባና መሥ​ዋ​ዕት ያቀ​ር​ቡ​በት የነ​በ​ረው ለዚህ ዘመን ምሳሌ ሆነ።


እር​ሱም የመ​ቅ​ደ​ስና የእ​ው​ነ​ተ​ኛ​ይቱ ድን​ኳን አገ​ል​ጋይ ነው፤ እር​ስ​ዋም በሰው ሳይ​ሆን በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር የተ​ተ​ከ​ለች ናት።


እርሱ ግን ይህን የተ​ና​ገ​ረው ቤተ መቅ​ደስ ስለ ተባለ ሰው​ነቱ ነበር።


ያም ቃል ሥጋ ሆነ፤ በእ​ኛም አደረ፤ ለአ​ባቱ አንድ እንደ ሆነ ልጅ ክብር ያለ ክብ​ሩን አየን፤ ጸጋ​ንና እው​ነ​ትን የተ​መላ ነው።


ሙሴም በም​ድረ በዳ የሠ​ራት የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ማደ​ሪ​ያና ለሚ​ቃ​ጠል መሥ​ዋ​ዕት የሚ​ሆ​ነው መሠ​ዊያ በዚ​ያን ጊዜ በገ​ባ​ዖን ባለው በኮ​ረ​ብ​ታው መስ​ገጃ ነበሩ።


እን​ዲ​ህም ሆነ፤ ዳዊት በቤቱ በተ​ቀ​መጠ ጊዜ ዳዊት ነቢዩ ናታ​ንን፥ “እነሆ፥ ከዝ​ግባ በተ​ሠራ ቤት ተቀ​ም​ጫ​ለሁ፤ የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ቃል ኪዳን ታቦት ግን በመ​ጋ​ረ​ጃ​ዎች ውስጥ ተቀ​ም​ጣ​ለች” አለው።


“በመ​ጀ​መ​ሪ​ያው ወር በፊ​ተ​ኛው ቀን የም​ስ​ክ​ሩን ድን​ኳን ትተ​ክ​ላ​ለህ።


በአ​ን​ጥ​ረኛ፥ በብ​ልህ ሠራ​ተ​ኛም፥ በሰ​ማ​ያ​ዊና በሐ​ም​ራዊ፥ በቀ​ይም ግምጃ፥ በጥሩ በፍ​ታም በሚ​ሠራ ጠላፊ፥ በሸ​ማ​ኔም ሥራ የሚ​ሠ​ራ​ውን፥ ማና​ቸ​ው​ንም ሥራና በብ​ል​ሃት የሚ​ሠ​ራ​ውን ሁሉ ያደ​ርጉ ዘንድ በእ​ነ​ርሱ ልብ ጥበ​ብን ሞላ።


ሰማ​ያ​ዊም፥ ሐም​ራ​ዊም፥ ድርብ ቀይ ግም​ጃም፥ የተ​ፈ​ተለ በፍ​ታም፥ የፍ​የል ጠጕ​ርም፤


መቅ​ደስ ትሠ​ራ​ል​ኛ​ለህ፤ በመ​ካ​ከ​ላ​ቸ​ውም አድ​ራ​ለሁ።


ሰማ​ያ​ዊና ሐም​ራዊ፥ ቀይም ድርብ ግምጃ፥ ጥሩ በፍ​ታም፥


የመ​ጀ​መ​ሪ​ያ​ዪ​ቱም ድን​ኳን ተዘ​ጋ​ጅታ ነበ​ርና፥ በእ​ር​ስ​ዋም ቅድ​ስት በም​ት​ባ​ለው ውስጥ መቅ​ረ​ዙና ጠረ​ጴ​ዛው፥ የመ​ሥ​ዋ​ዕ​ቱም ኅብ​ስት ነበ​ረ​ባት።


የእ​ያ​ን​ዳ​ንዱ መጋ​ረጃ ርዝ​መት ሃያ ስም​ንት ክንድ፥ ወር​ዱም አራት ክንድ ይሁን፤ የመ​ጋ​ረ​ጆ​ችም ሁሉ መጠን ትክ​ክል ይሁን።


ድን​ኳ​ኑ​ንም፥ አደ​ባ​ባ​ዩ​ንም፥ መደ​ረ​ቢ​ያ​ው​ንም፥ መያ​ዣ​ዎ​ቹ​ንም፥ ሳን​ቆ​ቹ​ንም፥ መወ​ር​ወ​ሪ​ያ​ዎ​ቹ​ንም፥ ምሰ​ሶ​ዎ​ች​ንና እግ​ሮ​ቻ​ቸ​ውን፤


የጌ​ድ​ሶን ልጆች በም​ስ​ክሩ ድን​ኳን የሚ​ጠ​ብ​ቁት ማደ​ሪ​ያ​ውና ድን​ኳኑ፥ መደ​ረ​ቢ​ያ​ውም፥ የም​ስ​ክሩ ድን​ኳን ደጃፍ መጋ​ረጃ፥


ንጉሡ ነቢዩ ናታ​ንን፥ “እኔ ከዝ​ግባ በተ​ሠራ ቤት ተቀ​ም​ጬ​አ​ለሁ፤ የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ታቦት ግን በድ​ን​ኳን ውስጥ ተቀ​ም​ጣ​ለች” አለው።


የም​ስ​ክ​ሩን ድን​ኳን፥ የቃል ኪዳ​ኑ​ንም ታቦት፥ በእ​ር​ሱም ላይ ያለ​ውን የስ​ር​የት መክ​ደ​ኛ​ውን፥ የድ​ን​ኳ​ኑ​ንም ዕቃ ሁሉ፤


ወር​ቁ​ንም ቀጥ​ቅ​ጠው እንደ ቅጠል ስስ አደ​ረ​ጉት፤ እንደ ፈት​ልም ቈረ​ጡት። ብልህ ሠራ​ተ​ኛም እን​ደ​ሚ​ሠራ ሰማ​ያዊ፥ ሐም​ራ​ዊም፥ ቀይ ግም​ጃም፥ የተ​ፈ​ተ​ለም ጥሩ በፍታ፥ ከእ​ርሱ ጠለፉ።


የድ​ን​ኳ​ኑን መጋ​ረ​ጃ​ዎች፥ የም​ስ​ክ​ሩ​ንም ድን​ኳን፥ መደ​ረ​ቢ​ያ​ውን፥ በላ​ዩም ያለ​ውን የአ​ቆ​ስ​ጣ​ውን ቍር​በት መደ​ረ​ቢያ፥ የም​ስ​ክ​ሩ​ንም ድን​ኳን ደጃፍ መጋ​ረጃ፥ የአ​ደ​ባ​ባ​ዩ​ንም መጋ​ረጃ፥


በቤ​ቱም ግንብ ሁሉ ዙሪያ በው​ስ​ጥና በውጭ የኪ​ሩ​ቤ​ልና የዘ​ን​ባባ ዛፍ፥ የፈ​ነ​ዳም አበባ ሥዕል ቀረጸ።


Síguenos en:

Anuncios


Anuncios