Biblia Todo Logo
La Biblia Online

- Anuncios -




ዘፀአት 26:7 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

7 “ከማ​ደ​ሪ​ያ​ውም በላይ ለድ​ን​ኳን የሚ​ሆኑ መጋ​ረ​ጃ​ዎች ከፍ​የል ጠጕር አድ​ርግ፤ ዐሥራ አንድ መጋ​ረ​ጃ​ዎች ታደ​ር​ጋ​ለህ።

Ver Capítulo Copiar

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

7 “ማደሪያ ድንኳኑን ከላይ ሆነው የሚሸፍኑ በጠቅላላ ዐሥራ አንድ የፍየል ጠጕር መጋረጃዎች ሥራ።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

7 ከማደሪያውም በላይ ለመሸፈኛ የሚሆኑ መጋረጆች ከፍየል ጠጉር ሥራ፤ ዐሥራ አንድ መጋረጆች ትሠራለህ።

Ver Capítulo Copiar

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

7 “ከፍየል ጠጒር የተሠሩ ዐሥራ አንድ መጋረጃዎችን ለድንኳኑ ክዳን አድርግ።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

7 ከማደሪያውም በላይ ለድንኳን የሚሆኑ መጋረጆች ከፍየል ጠጉር አድርግ፤ አሥራ አንድ መጋረጆች ታደርጋለህ።

Ver Capítulo Copiar




ዘፀአት 26:7
18 Referencias Cruzadas  

እንዲሁም ጐበዞች ሆይ! ለሽማግሌዎች ተገዙ፤ ሁላችሁም እርስ በርሳችሁ እየተዋረዳችሁ ትሕትናን እንደ ልብስ ልበሱ፤ እግዚአብሔር ትዕቢተኞችን ይቃወማልና፤ ለትሑታኑ ግን ጸጋን ይሰጣል።


ነገር ግን በእግዚአብሔር ፊት ዋጋው እጅግ የከበረ የዋህና ዝግተኛ መንፈስ ያለውን የማይጠፋውን ልብስ ለብሶ የተሰወረ የልብ ሰው ይሁንላችሁ።


እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ይመ​ጣል፤ በጽ​ዮን ተራራ ላይ ባለ ቦታ ሁሉ፥ በዙ​ሪ​ያ​ውም ላይ ደመና በቀን እንደ ጢስ፥ በሌ​ሊ​ትም እን​ደ​ሚ​ቃ​ጠል የእ​ሳት ብር​ሃን ይጋ​ር​ዳል፤ በክ​ብ​ርም ሁሉ ላይ መጋ​ረጃ ይሆ​ናል።


ልብ​ስ​ንም፥ ከቁ​ር​በ​ትም የተ​ዘ​ጋ​ጀ​ውን ሁሉ፥ ከፍ​የ​ልም ጠጕር፥ ከዕ​ን​ጨ​ትም የተ​ሠ​ራ​ውን ሁሉ ንጹሕ አድ​ርጉ።”


የድ​ን​ኳ​ኑን መጋ​ረ​ጃ​ዎች፥ የም​ስ​ክ​ሩ​ንም ድን​ኳን፥ መደ​ረ​ቢ​ያ​ውን፥ በላ​ዩም ያለ​ውን የአ​ቆ​ስ​ጣ​ውን ቍር​በት መደ​ረ​ቢያ፥ የም​ስ​ክ​ሩ​ንም ድን​ኳን ደጃፍ መጋ​ረጃ፥ የአ​ደ​ባ​ባ​ዩ​ንም መጋ​ረጃ፥


ልባ​ቸ​ውም በጥ​በብ ያስ​ነ​ሣ​ቸው ሴቶች ሁሉ የፍ​የ​ልን ጠጕር ፈተሉ።


ሰማ​ያ​ዊም፥ ሐም​ራ​ዊም፥ ቀይ ግም​ጃም፥ የተ​ፈ​ተለ በፍ​ታም፥ የፍ​የል ጠጕ​ርም፥ ቀይ የአ​ውራ በግ ቍር​በ​ትም፥ የአ​ቆ​ስጣ ቍር​በ​ትም ያላ​ቸው ሰዎች ሁሉ አመጡ።


ሰማ​ያ​ዊም፥ ሐም​ራ​ዊም፥ ድርብ ቀይ ግም​ጃም፥ የተ​ፈ​ተለ በፍ​ታም፥ የፍ​የል ጠጕ​ርም፤


ለድ​ን​ኳ​ኑም መደ​ረ​ቢያ ከቀይ አውራ በግ ቍር​በት፥ ከዚ​ያም በላይ ሌላ መደ​ረ​ቢያ ከአ​ቆ​ስጣ ቍር​በት አድ​ርግ።


ከድ​ን​ኳኑ መጋ​ረ​ጃ​ዎች የቀረ ትርፍ ግማሽ መጋ​ረጃ በድ​ን​ኳኑ ጀርባ ይጋ​ረድ።


አም​ስቱ መጋ​ረ​ጃ​ዎች እርስ በር​ሳ​ቸው አንድ ሆነው ይጋ​ጠሙ፤ ስድ​ስ​ቱም መጋ​ረ​ጃ​ዎች እርስ በር​ሳ​ቸው አንድ ሆነው ይጋ​ጠሙ፤ ስድ​ስ​ተ​ኛ​ውም መጋ​ረጃ በድ​ን​ኳኑ ፊት ይደ​ረብ።


“ለድ​ን​ኳ​ኑም ከተ​ፈ​ተለ ከጥሩ በፍታ፥ ከሰ​ማ​ያዊ፥ ከሐ​ም​ራ​ዊም፥ ከቀ​ይም ግምጃ ዐሥር መጋ​ረ​ጆ​ችን ሥራ፤ ኪሩ​ቤ​ልም በእ​ነ​ርሱ ላይ ይሁኑ፤ እንደ ሽመና ሥራም በብ​ል​ሃት ትሠ​ራ​ቸ​ዋ​ለህ።


ሰማ​ያ​ዊና ሐም​ራዊ፥ ቀይም ድርብ ግምጃ፥ ጥሩ በፍ​ታም፥


አምሳ የወ​ርቅ መያ​ዣ​ዎች ሥራ፤ መጋ​ረ​ጃ​ዎ​ችን እርስ በር​ሳ​ቸው በመ​ያ​ዣ​ዎች አጋ​ጥ​ማ​ቸው፤ ድን​ኳ​ኑም አንድ ይሆ​ናል።


እያ​ን​ዳ​ን​ዱም መጋ​ረጃ ርዝ​መቱ ሠላሳ ክንድ፥ እያ​ን​ዳ​ን​ዱም መጋ​ረጃ ወርዱ አራት ክንድ ይሁን፤ የዐ​ሥራ አን​ዱም መጋ​ረ​ጃ​ዎች መጠ​ና​ቸው ትክ​ክል ይሁን።


የጌ​ድ​ሶን ልጆች በም​ስ​ክሩ ድን​ኳን የሚ​ጠ​ብ​ቁት ማደ​ሪ​ያ​ውና ድን​ኳኑ፥ መደ​ረ​ቢ​ያ​ውም፥ የም​ስ​ክሩ ድን​ኳን ደጃፍ መጋ​ረጃ፥


Síguenos en:

Anuncios


Anuncios