ለወርቁም መቅረዞችና ለቀንዲሎችም ወርቁን በየመቅረዙና በየቀንዲሉ በሚዛን ሰጠው፤ ለብሩም መቅረዞች እንደ መቅረዙ ሁሉ ሥራ ብሩን በየመቅረዙና በየቀንዲሉ በሚዛን ሰጠው፤
ዘፀአት 37:17 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) መቅረዝዋንም ከጥሩ ወርቅ አደረገ፤ መቅረዝዋንም ከእግርዋና ከአገዳዋ ጋር በተቀረጸ ሥራ አደረገ፤ ጽዋዎችዋን፥ ጕብጕቦችዋን፥ አበቦችዋን ከዚያው በአንድነት አደረገ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም መቅረዙን ከንጹሕ ወርቅ ሠሩት፤ መቆሚያውንና ዘንጉን ቀጥቅጠው አበጁት፤ የአበባ ቅርጽ ያላቸው ጽዋዎች፣ እንቡጦችና የፈኩ አበቦች ከርሱ ጋራ አንድ ወጥ ሆነው ተሠርተው ነበር። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) መቅረዙን ከንጹሕ ወርቅ ሠራ፤ መቅረዙንም ከእግሩና ከአገዳው ጋር በተቀረጸ ሥራ አደረገ፤ ጽዋዎቹን፥ ጉብጉቦቹን፥ አበቦቹን ከዚያው በአንድነት አደረገ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም መቅረዙንም ከንጹሕ ወርቅ ሠራ፤ ማቆሚያውንና ዘንጉንም ከተቀጠቀጠ ወርቅ አበጀ፤ ለጌጥ የሚሆኑትንም የአበባዎች ቅርጽ ከነእንቡጣቸውና ከነቀንበጣቸው አንድ ወጥ አድርጎ ሠራቸው። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) መቅረዙንም ከጥሩ ወርቅ አደረገ፤ መቅረዙንም ከእግሩና ከአገዳው ጋር በተቀረጸ ሥራ አደረገ፤ ጽዋዎቹን፥ ጉብጉቦቹን፥ አበቦቹን ከዚያው በአንድነት አደረገ። |
ለወርቁም መቅረዞችና ለቀንዲሎችም ወርቁን በየመቅረዙና በየቀንዲሉ በሚዛን ሰጠው፤ ለብሩም መቅረዞች እንደ መቅረዙ ሁሉ ሥራ ብሩን በየመቅረዙና በየቀንዲሉ በሚዛን ሰጠው፤
በየጥዋቱና በየማታውም ለእግዚአብሔር የሚቃጠለውን መሥዋዕትና ጣፋጩን ዕጣን ያሳርጋሉ፤ የገጹንም ኅብስት በንጹሕ ገበታ ላይ፥ የወርቁን መቅረዝና ቀንዲሎቹንም ማታ ማታ እንዲያበሩ ያዘጋጃሉ፤ እኛም የአምላካችንን የእግዚአብሔርን ትእዛዝ እንጠብቃለን፤ እናንተ ግን ትታችሁታል።
ለማፍሰሻም ይሆኑ ዘንድ በገበታው ላይ የሚኖሩትን ዕቃዎች፥ ወጭቶቹንና ጭልፋዎቹን፥ ጽዋዎቹንም፥ መቅጃዎቹንም ከጥሩ ወርቅ አደረጋቸው።
በስተጎንዋ ስድስት ቅርንጫፎች ወጡላት፤ ሦስቱ የመቅረዝዋ ቅርንጫፎች በአንድ ወገን፥ ሦስቱም የመቅረዝዋ ቅርንጫፎች በሁለተኛው ወገን ወጡ።
እርሱም፦ የምታየው ምንድር ነው? አለኝ። እኔም፦እነሆ፥ ሁለንተናው ወርቅ የሆነውን መቅረዝ አየሁ፣ የዘይትም ማሰሮ በራሱ ላይ ነበረ፥ ሰባትም መብራቶች ነበሩበት፣ በራሱም ላይ ለነበሩት መብራቶች ሰባት ቧንቧዎች ነበሩአቸው።
የመቅረዝዋም ሥራዋ እንዲህ ነበረ። ሁለንተናቸው ወርቅ የሆነ አፅቆችዋ ሥረ-ወጥ ነበሩ፤ አበቦችዋም ሁለንተናቸው ሥረ-ወጥ ነበሩ። እግዚአብሔር ሙሴን እንዳሳየው ምሳሌ መቅረዝዋን እንዲሁ አደረገ።
እንደ እግዚአብሔር ልጆች ንጹሓንና የዋሃን ትሆኑ ዘንድ፥ በማያምኑና በጠማሞች ልጆች መካከል ነውር ሳይኖርባችሁ በዓለም እንደ ብርሃን ትታያላችሁ፤
የመጀመሪያዪቱም ድንኳን ተዘጋጅታ ነበርና፥ በእርስዋም ቅድስት በምትባለው ውስጥ መቅረዙና ጠረጴዛው፥ የመሥዋዕቱም ኅብስት ነበረባት።