Biblia Todo Logo
La Biblia Online

- Anuncios -




ዘሌዋውያን 24:4 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

4 በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ፊት በጥሩ መቅ​ረዝ ላይ መብ​ራ​ቶ​ቹን ሁል ጊዜ እስ​ኪ​ነጋ አብ​ሩ​አ​ቸው።

Ver Capítulo Copiar

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

4 በእግዚአብሔር ፊት በንጹሕ የወርቅ መቅረዝ ላይ ያሉት መብራቶች ያለ ማቋረጥ መሰናዳት አለባቸው።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

4 በጌታ ፊት በንጹሕ የወርቅ መቅረዝ ላይ መብራቶቹን ሁልጊዜ ያዘጋጃል።

Ver Capítulo Copiar

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

4 አሮን መብራቶቹን በንጹሕ የወርቅ መቅረዝ ላይ በእግዚአብሔር ፊት ባለሟቋረጥ የሚበሩ መሆናቸውንም ይቈጣጠራል።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

4 በእግዚአብሔር ፊት በጥሩ መቅረዝ ላይ መብራቶቹን ሁልጊዜ ያሰናዳቸው።

Ver Capítulo Copiar




ዘሌዋውያን 24:4
19 Referencias Cruzadas  

የዕ​ጣን መሠ​ዊ​ያ​ውን፥ ገበ​ታ​ው​ንም፥ ዕቃ​ው​ንም፥ ከዕ​ቃው ሁሉ የነ​ጻ​ውን መቅ​ረዝ፥


ጥሩ​ው​ንም መቅ​ረዝ፥ መብ​ራ​ቶ​ቹ​ንም፥ በተራ የሚ​ሆ​ኑ​ት​ንም ቀን​ዲ​ሎች፥ ዕቃ​ው​ንም ሁሉ፥ የመ​ብ​ራ​ቱ​ንም ዘይት፤


እነዚህ በምድር ጌታ ፊት የሚቆሙ ሁለቱ ወይራዎችና ሁለቱ መቅረዞች ናቸው።


እንግዲህ ከወዴት እንደ ወደቅህ አስብ፤ ንስሓም ግባ የቀደመውንም ሥራህን አድርግ፤ አለዚያ እመጣብሃለሁ ንስሓም ባትገባ መቅረዝህን ከስፍራው እወስዳለሁ።


በቀኝ እጄ ያየሃቸው የሰባቱ ከዋክብትና የሰባቱ የወርቅ መቅረዞች ምሥጢር ይህ ነው፤ ሰባቱ ከዋክብት የሰባቱ አብያተ ክርስቲያናት መላእክት ናቸው፤ ሰባቱም መቅረዞች ሰባቱ አብያተ ክርስቲያናት ናቸው።


የመ​ጀ​መ​ሪ​ያ​ዪ​ቱም ድን​ኳን ተዘ​ጋ​ጅታ ነበ​ርና፥ በእ​ር​ስ​ዋም ቅድ​ስት በም​ት​ባ​ለው ውስጥ መቅ​ረ​ዙና ጠረ​ጴ​ዛው፥ የመ​ሥ​ዋ​ዕ​ቱም ኅብ​ስት ነበ​ረ​ባት።


የአ​ዛ​ዦ​ችም አለቃ ጽዋ​ዎ​ቹን፥ ማን​ደ​ጃ​ዎ​ቹን፥ ድስ​ቶ​ቹ​ንና ምን​ቸ​ቶ​ቹን፥ መቅ​ረ​ዞ​ቹ​ንና ጭል​ፋ​ዎ​ቹን፥ መን​ቀ​ሎ​ች​ንም፥ የወ​ር​ቁን ዕቃ በወ​ርቅ፥ የብ​ሩ​ንም ዕቃ በብር አድ​ርጎ፥ ወሰደ።


ለወ​ር​ቁም መቅ​ረ​ዞ​ችና ለቀ​ን​ዲ​ሎ​ችም ወር​ቁን በየ​መ​ቅ​ረ​ዙና በየ​ቀ​ን​ዲሉ በሚ​ዛን ሰጠው፤ ለብ​ሩም መቅ​ረ​ዞች እንደ መቅ​ረዙ ሁሉ ሥራ ብሩን በየ​መ​ቅ​ረ​ዙና በየ​ቀ​ን​ዲሉ በሚ​ዛን ሰጠው፤


በቅ​ድ​ስተ ቅዱ​ሳኑ ፊት አም​ስቱ በቀኝ፥ አም​ስ​ቱም በግራ የሚ​ቀ​መ​ጡ​ትን ከጥሩ ወርቅ የተ​ሠ​ሩ​ት​ንም መቅ​ረ​ዞች፥ የወ​ር​ቁ​ንም አበ​ባ​ዎ​ችና ቀን​ዲ​ሎች፥ መኮ​ስ​ተ​ሪ​ያ​ዎ​ች​ንም፥


ሰማ​ያ​ዊ​ው​ንም መጐ​ና​ጸ​ፊያ ይው​ሰዱ፤ የሚ​ያ​በ​ሩ​ባ​ት​ንም መቅ​ረዝ፥ ቀን​ዲ​ሎ​ች​ዋ​ንም፥ መኰ​ስ​ተ​ሪ​ያ​ዎ​ች​ዋ​ንም፥ የኵ​ስ​ታሪ ማድ​ረ​ጊ​ያ​ዎ​ች​ዋ​ንም፥ እር​ስ​ዋ​ንም ለማ​ገ​ል​ገል የዘ​ይ​ቱን ማሰ​ሮ​ዎች ሁሉ ይሸ​ፍኑ፤


ታቦ​ቱ​ንም፥ ገበ​ታ​ው​ንም፥ መቅ​ረ​ዙ​ንም፥ መሠ​ዊ​ያ​ዎ​ቹ​ንም፥ የሚ​ያ​ገ​ለ​ግ​ሉ​በ​ት​ንም የመ​ቅ​ደ​ሱን ዕቃ፥ መጋ​ረ​ጃ​ው​ንም፥ ማገ​ል​ገ​ያ​ው​ንም ሁሉ ይጠ​ብ​ቃሉ።


በም​ስ​ክሩ ድን​ኳን ከመ​ጋ​ረ​ጃው ውጭ አሮ​ንና ልጆቹ ከማታ እስከ ማለዳ ድረስ በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ፊት ሁል ጊዜ ያበ​ሩ​ታል፤ ለዘ​ለ​ዓ​ለም ለልጅ ልጃ​ችሁ ሥር​ዐት ይሁን።


“መብ​ራ​ቶ​ቹን ስታ​በራ ሰባቱ መብ​ራ​ቶች በመ​ቅ​ረዙ ፊት ያበ​ራሉ ብለህ ለአ​ሮን ንገ​ረው።”


ደግ​ሞም የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ቤት ደጆች ዘግ​ተ​ዋል፤ መብ​ራ​ቶ​ቹ​ንም አጥ​ፍ​ተ​ዋል፤ በመ​ቅ​ደ​ሱም ውስጥ ለእ​ስ​ራ​ኤል አም​ላክ አላ​ጠ​ኑም፤ የሚ​ቃ​ጠ​ለ​ው​ንም መሥ​ዋ​ዕት አላ​ቀ​ረ​ቡም።


Síguenos en:

Anuncios


Anuncios