Biblia Todo Logo
La Biblia Online
- Anuncios -




ዘካርያስ 4:2 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

2 እርሱም፦ የምታየው ምንድር ነው? አለኝ። እኔም፦እነሆ፥ ሁለንተናው ወርቅ የሆነውን መቅረዝ አየሁ፣ የዘይትም ማሰሮ በራሱ ላይ ነበረ፥ ሰባትም መብራቶች ነበሩበት፣ በራሱም ላይ ለነበሩት መብራቶች ሰባት ቧንቧዎች ነበሩአቸው።

Ver Capítulo Copiar

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

2 እርሱም፣ “ምን ታያለህ?” አለኝ። እኔም እንዲህ አልሁ፤ “እነሆ፤ በዐናቱ ላይ የዘይት ማሰሮ ያለበት ሁለንተናው ወርቅ የሆነ መቅረዝ አየሁ፤ በመቅረዙም ላይ ሰባት ቧንቧዎች ያሏቸው ሰባት መብራቶች ነበሩ።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

2 እርሱም፦ “የምታየው ምንድነው?” አለኝ። እኔም፦ “እነሆ፥ ሁለንተናው ወርቅ የሆነ መቅረዝ ይታየኛል፤ የዘይት ማሰሮም በላዩ ላይ ነበረ። በመቅረዙም ላይ ሰባት ቧንቧዎች ያሏቸው ሰባት መብራቶች ነበሩ።

Ver Capítulo Copiar

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

2 “ይህ የምታየው ምንድን ነው?” ብሎም ጠየቀኝ። እኔም እንዲህ ብዬ መለስኩለት፦ “ሰባት መብራቶች ያሉበት አንድ የወርቅ መቅረዝ አያለሁ፤ በአናቱም ላይ የዘይት ማሰሮ አለ፤ ሰባቱም መብራቶች የክር ማስተላለፊያ ቧንቧ አላቸው።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

2 እርሱም፦ የምታየው ምንድር ነው? አለኝ። እኔም፦ እነሆ፥ ሁለንተናው ወርቅ የሆነውን መቅረዝ አየሁ፥ የዘይትም ማሰሮ በራሱ ላይ ነበረ፥ ሰባትም መብራቶች ነበሩበት፥ በራሱም ላይ ለነበሩት መብራቶች ሰባት ቧንቧዎች ነበሩአቸው።

Ver Capítulo Copiar




ዘካርያስ 4:2
19 Referencias Cruzadas  

ለወ​ር​ቁም መቅ​ረ​ዞ​ችና ለቀ​ን​ዲ​ሎ​ችም ወር​ቁን በየ​መ​ቅ​ረ​ዙና በየ​ቀ​ን​ዲሉ በሚ​ዛን ሰጠው፤ ለብ​ሩም መቅ​ረ​ዞች እንደ መቅ​ረዙ ሁሉ ሥራ ብሩን በየ​መ​ቅ​ረ​ዙና በየ​ቀ​ን​ዲሉ በሚ​ዛን ሰጠው፤


በየ​ጥ​ዋ​ቱና በየ​ማ​ታ​ውም ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር የሚ​ቃ​ጠ​ለ​ውን መሥ​ዋ​ዕ​ትና ጣፋ​ጩን ዕጣን ያሳ​ር​ጋሉ፤ የገ​ጹ​ንም ኅብ​ስት በን​ጹሕ ገበታ ላይ፥ የወ​ር​ቁን መቅ​ረ​ዝና ቀን​ዲ​ሎ​ቹ​ንም ማታ ማታ እን​ዲ​ያ​በሩ ያዘ​ጋ​ጃሉ፤ እኛም የአ​ም​ላ​ካ​ች​ንን የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ትእ​ዛዝ እን​ጠ​ብ​ቃ​ለን፤ እና​ንተ ግን ትታ​ች​ሁ​ታል።


ዐሥ​ሩ​ንም የወ​ርቅ መቅ​ረ​ዞች እንደ ሥር​ዐ​ታ​ቸው ሠራ፤ አም​ስ​ቱን በቀኝ፥ አም​ስ​ቱ​ንም በግራ በመ​ቅ​ደሱ ውስጥ አኖ​ራ​ቸው።


የብር ድሪ ሳይ​በ​ጠስ፥ የወ​ር​ቅም ኵስ​ኵ​ስት ሳይ​ሰ​በር፥ ማድ​ጋ​ውም በም​ንጭ አጠ​ገብ ሳይ​ከ​ሰ​ከስ፥ ወደ መስ​ኮት የሚ​ያዩ ዐይ​ኖች ሳይ​ጠፉ፥ የአ​ደ​ባ​ባይ ደጆች ሳይ​ዘጉ፥ ስለ ቃላት ድን​ጋጤ ከጠ​ላት ቃል የተ​ነሣ የሚ​ጮኹ ሳይ​ነሡ፥ በአ​ዳም ልጆች ሁሉ ወዮታ ሳይ​ሆን፥ ወደ ላይም ሳይ​መ​ለ​ከቱ፥ በመ​ን​ገ​ድም ፍር​ሀት ሳይ​መጣ፥ እሳ​ትም ወደ ላይ ከፍ ማለ​ትን በወ​ደደ ጊዜ ሳይ​ታይ፥ በአ​ደ​ባ​ባይ ልቅሶ ሳይ​ሰማ፥ የብር መልኩ ሳይ​ለ​ወጥ፥ የወ​ር​ቅም መልኩ ሳይ​ጠፋ፥ መን​ኰ​ራ​ኵ​ሩም በጕ​ድ​ጓድ ላይ ሳይ​ሰ​በር፥


እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም፥ “ኤር​ም​ያስ ሆይ! የም​ታ​የው ምን​ድን ነው?” አለኝ። እኔም፥ “በለ​ስን አያ​ለሁ፤ እጅግ መል​ካም የሆነ መል​ካም በለስ፥ ከክ​ፋ​ቱም የተ​ነሣ ይበላ ዘንድ የማ​ይ​ቻል እጅግ ክፉ የሆነ ክፉ በለስ ነው” አልሁ።


የአ​ዛ​ዦ​ችም አለቃ ጽዋ​ዎ​ቹን፥ ማን​ደ​ጃ​ዎ​ቹን፥ ድስ​ቶ​ቹ​ንና ምን​ቸ​ቶ​ቹን፥ መቅ​ረ​ዞ​ቹ​ንና ጭል​ፋ​ዎ​ቹን፥ መን​ቀ​ሎ​ች​ንም፥ የወ​ር​ቁን ዕቃ በወ​ርቅ፥ የብ​ሩ​ንም ዕቃ በብር አድ​ርጎ፥ ወሰደ።


እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም፥ “አሞጽ ሆይ! የም​ታ​የው ምን​ድን ነው?” አለኝ። እኔም፥ “ቱንቢ ነው” አልሁ። ጌታም፥ “እነሆ! በሕ​ዝቤ በእ​ስ​ራ​ኤል መካ​ከል ቱንቢ አደ​ር​ጋ​ለሁ፤ ከእ​ን​ግ​ዲ​ህም ወዲህ ደግሞ ይቅር አል​ላ​ቸ​ውም።


እርሱም፦ የምታየው ምንድር ነው? አለኝ። እኔም፦ በራሪ የመጽሐፍ ጥቅልል አያለሁ፣ ርዝመቱ ሀያ ክንድ ወርዱም አሥር ክንድ ነው አልሁ።


የሚናገረኝንም ድምፅ ለማየት ዘወር አልሁ፤ ዘወርም ብዬ ሰባት የወርቅ መቅረዞች አየሁ፤


በቀኝ እጄ ያየሃቸው የሰባቱ ከዋክብትና የሰባቱ የወርቅ መቅረዞች ምሥጢር ይህ ነው፤ ሰባቱ ከዋክብት የሰባቱ አብያተ ክርስቲያናት መላእክት ናቸው፤ ሰባቱም መቅረዞች ሰባቱ አብያተ ክርስቲያናት ናቸው።


ከዙፋኑም መብረቅና ድምፅ ነጐድጓድም ይወጣል፤ በዙፋኑም ፊት ሰባት የእሳት መብራቶች ይበሩ ነበር፤ እነርሱም ሰባቱ የእግዚአብሔር መናፍስት ናቸው።


Síguenos en:

Anuncios


Anuncios


¡Síguenos en WhatsApp! Síguenos