ዘፀአት 37:17 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም17 መቅረዙንም ከንጹሕ ወርቅ ሠራ፤ ማቆሚያውንና ዘንጉንም ከተቀጠቀጠ ወርቅ አበጀ፤ ለጌጥ የሚሆኑትንም የአበባዎች ቅርጽ ከነእንቡጣቸውና ከነቀንበጣቸው አንድ ወጥ አድርጎ ሠራቸው። Ver Capítuloአዲሱ መደበኛ ትርጒም17 መቅረዙን ከንጹሕ ወርቅ ሠሩት፤ መቆሚያውንና ዘንጉን ቀጥቅጠው አበጁት፤ የአበባ ቅርጽ ያላቸው ጽዋዎች፣ እንቡጦችና የፈኩ አበቦች ከርሱ ጋራ አንድ ወጥ ሆነው ተሠርተው ነበር። Ver Capítuloመጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)17 መቅረዙን ከንጹሕ ወርቅ ሠራ፤ መቅረዙንም ከእግሩና ከአገዳው ጋር በተቀረጸ ሥራ አደረገ፤ ጽዋዎቹን፥ ጉብጉቦቹን፥ አበቦቹን ከዚያው በአንድነት አደረገ። Ver Capítuloየአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)17 መቅረዝዋንም ከጥሩ ወርቅ አደረገ፤ መቅረዝዋንም ከእግርዋና ከአገዳዋ ጋር በተቀረጸ ሥራ አደረገ፤ ጽዋዎችዋን፥ ጕብጕቦችዋን፥ አበቦችዋን ከዚያው በአንድነት አደረገ። Ver Capítuloመጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)17 መቅረዙንም ከጥሩ ወርቅ አደረገ፤ መቅረዙንም ከእግሩና ከአገዳው ጋር በተቀረጸ ሥራ አደረገ፤ ጽዋዎቹን፥ ጉብጉቦቹን፥ አበቦቹን ከዚያው በአንድነት አደረገ። Ver Capítulo |