ሙሴም እንዳዘዘ እንደ ሥርዐታቸው በየቀኑ ሁሉ፥ በየሰንበታቱም፥ በየመባቻዎቹም፥ በየበዓላቱም፥ በየዓመቱ ሦስት ጊዜ በየቂጣው በዓልና በየሰባቱ ሱባዔ በዓል፥ በየዳሱም በዓል ቍርባን ያቀርቡ ነበር።
ዘፀአት 34:22 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) የሰባቱንም ሱባዔ በዓል ታደርጋለህ፤ እርሱም የስንዴ መከር መጀመሪያ ነው፤ በዓመቱም መካከል የመክተቻ በዓል ታደርጋለህ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም “የሰባቱን ሱባዔ የመከር በዓል ከስንዴው መከር በኵራት ጋራ፣ እንዲሁም የመክተቻ በዓልን በዓመቱ መጨረሻ ላይ አክብር። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) የሰባቱን ሱባዔ በዓል ትጠብቃለህ፥ እርሱም የስንዴ መከር በኵራት ነው፤ በዓመቱም መጨረሻ የመክተቻ በዓል ታደርጋለህ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም “የስንዴአችሁን በኲራት በምትሰበስቡበት ጊዜ የመከርን በዓል አክብሩ፤ የዓመቱ መጨረሻ በሆነው በፍሬ መከር ጊዜ የዳስን በዓል አክብሩ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) የሰባቱንም ሱባዔ በዓል ታደርጋለህ፥ እርሱም የስንዴ መከር በኵራት ነው፤ በዓመቱም ፍጻሜ የመክተቻ በዓል ታደርጋለህ። |
ሙሴም እንዳዘዘ እንደ ሥርዐታቸው በየቀኑ ሁሉ፥ በየሰንበታቱም፥ በየመባቻዎቹም፥ በየበዓላቱም፥ በየዓመቱ ሦስት ጊዜ በየቂጣው በዓልና በየሰባቱ ሱባዔ በዓል፥ በየዳሱም በዓል ቍርባን ያቀርቡ ነበር።
በፊቴ ባዶ እጅህን አትታይ። በእርሻም የምትዘራትን የፍሬህን በኵራት የመከር በዓል፥ ዓመቱም ሲያልቅ ፍሬህን ከእርሻ ባከማቸህ ጊዜ የመክተቻውን በዓል ጠብቅ።
እነዚህንም ዐሥራት አድርጋችሁ ለእግዚአብሔር ታቀርባላችሁ፤ ነገር ግን ለእግዚአብሔር ለበጎ መዓዛ በመሠዊያው ላይ አይቀርቡም።
“ለእስራኤል ልጆች እንዲህ ብለህ ንገራቸው፦ በዚህ በሰባተኛው ወር ከዐሥራ አምስተኛው ቀን ጀምሮ ሰባት ቀን ለእግዚአብሔር የዳስ በዓል ይሆናል።
“በሰባተኛውም ወር ከወሩ የመጀመሪያዋ ቀን ለእናንተ ይህች ዕለት የተቀደሰች ናት፤ የተግባርን ሥራ ሁሉ አትሥሩባት፤ ምልክት ያለባት ቀን ትሁንላችሁ።