አብርሃምም ዐይኖቹን አቅንቶ በተመለከተ ጊዜ፥ በኋላው እነሆ፥ አንድ በግ ቀንዶቹ በዕፀ ሳቤቅ ተይዞ አየ፤ አብርሃምም ሄዶ በጉን ወሰደው፤ በልጁ በይስሐቅ ፈንታም ሠዋው።
ዘፀአት 29:18 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) አውራንም በግ በሞላው በመሠዊያው ላይ ታቃጥላለህ፤ ስለ ጣፋጭ ሽታ ለእግዚአብሔር የሚቃጠል መሥዋዕት ነው፤ ለእግዚአብሔር የቀረበ የእሳት ቍርባን ነው። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ከዚያም አውራ በጉን በሙሉ በመሠዊያው ላይ አቃጥለው፤ ለእግዚአብሔር የሚቃጠል መሥዋዕት ጣፋጭ መዐዛና ለእግዚአብሔር በእሳት የሚቀርብ መሥዋዕት ነው። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) አውራውን በግ በሙሉ በመሠዊያው ላይ ታቃጥለዋለህ፤ ለጌታ የሚቃጠል መሥዋዕት ነው፤ ጣፋጭ ሽቱ ነው፤ ለጌታ የቀረበ የእሳት ቁርባን ነው። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ከዚያም በኋላ የአውራውን በግ ሥጋ በሙሉ ለእኔ ለእግዚአብሔር የምግብ መሥዋዕት አድርገህ አቃጥለው፤ ይህም መባ ሽታው እኔን ደስ የሚያሰኝ ይሆናል። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) አውራውንም በግ በሞላው በመሠዊያው ላይ ታቃጥላለህ፤ ለእግዚአብሔር የሚቃጠል መሥዋዕት ነው፤ ጣፋጭ ሽቱ ነው። ለእግዚአብሔር የቀረበ የእሳት ቍርባን ነው። |
አብርሃምም ዐይኖቹን አቅንቶ በተመለከተ ጊዜ፥ በኋላው እነሆ፥ አንድ በግ ቀንዶቹ በዕፀ ሳቤቅ ተይዞ አየ፤ አብርሃምም ሄዶ በጉን ወሰደው፤ በልጁ በይስሐቅ ፈንታም ሠዋው።
“የምትወድደውን አንድ ልጅህን ይስሐቅን ይዘህ ወደ ከፍተኛው ተራራ ሂድ፤ እኔም በምነግርህ በአንድ ተራራ ላይ በዚያ መሥዋዕት አድርገህ ሠዋው” አለው።
ይስሐቅም አባቱን አብርሃምን ተናገረው፥ “አባቴ ሆይ፥” አለ፤ እርሱም፥ “ልጄ፥ ምንድን ነው?” አለው። “እሳቱና ዕንጨቱ ይኸው አለ፤ የመሥዋዕቱ በግ ግን ወዴት አለ?” አለው።
ኖኅም ለእግዚአብሔር መሠውያዉን ሠራ፥ ከንጹሕም እንስሳ ሁሉ፥ ከንጹሓን ወፎችም ሁሉ ወሰደ፤ በመሠውያውም ላይ መሥዋዕትን አቀረበ።
እግዚአብሔር አምላክም መልካሙን መዓዛ አሸተተ፤ እግዚአብሔርም በልቡ አለ፥ “ምድርን ዳግመኛ ስለ ሰዎች ሥራ አልረግምም፤ በሰው ልብ ከታናሽነቱ ጀምሮ ክፋት ሁል ጊዜ ይኖራል፤ ደግሞም ከዚህ ቀደም እንዳደረግሁት ሕያዋንን ሁሉ እንደገና አልመታም።
እሳትም ከሰማይ ከእግዚአብሔር ዘንድ ወረደች፤ የሚቃጠለውን መሥዋዕት፥ እንጨቱንም፥ ድንጋዮቹንም በላች፤ በጕድጓዱም ውስጥ ያለውን ውኃ፥ አፈሩንም ላሰች።
ገባዖን ፈጽማ ትሰፋ ነበርና በዚያ መሥዋዕት ይሠዋ ዘንድ ተነሥቶ ሄደ፤ ሰሎሞንም በዚያ መሠዊያ ላይ በገባዖን አንድ ሺህ የሚቃጠል መሥዋዕት ሠዋ።
አውራውንም በግ በየብልቱ ትቈርጠዋለህ፤ የሆድ ዕቃውንና እግሮቹንም በውኃ ታጥባለህ፤ ከብልቱና ከራሱም ጋር ታኖረዋለህ።
ከእጃቸውም ትቀበለዋለህ፤ በመሥዊያውም ላይ ከሚቃጠል መሥዋዕት ጋር በእግዚአብሔር ፊት በጎ መዓዛ እንዲሆን ታቃጥለዋለህ፤ እርሱ ለእግዚአብሔር መሥዋዕት ነው።
“የመሥዋዕታችሁ ብዛት ለእኔ ምንድን ነው?” ይላል እግዚአብሔር፤ “የሚቃጠለውን የአውራ በግ መሥዋዕትንና የፍሪዳን ስብ ጠግቤአለሁ፤ የበሬና የአውራ ፍየልም ደም ደስ አያሰኘኝም።
ስለ ምንስ ከሳባ ዕጣንን፥ ከሩቅም ሀገር ቀረፋን ታቀርቡልኛላችሁ? የሚቃጠለውን መሥዋዕታችሁን አልቀበለውም፤ ቍርባናችሁም ደስ አያሰኘኝም።
ከክንፎቹም ይሰብረዋል፤ ነገር ግን አይለየውም። ካህኑም በመሠዊያው ላይ በእሳቱ ላይ ባለው በዕንጨቱ ላይ ያኖረዋል፤ መሥዋዕቱ ለእግዚአብሔር በጎ መዓዛ ያለው ቍርባን ነው።
የሆድ ዕቃውንና እግሮቹን ግን በውኃ ያጥባሉ፤ ካህኑም ሁሉን የሚቃጠል መሥዋዕት በእግዚአብሔር ዘንድ በጎ መዓዛ እንዲሆን በመሠዊያው ላይ ያቀርበዋል።
ስቡም ሁሉ ከደኅንነት መሥዋዕት ላይ እንደሚወሰድ፥ ስብዋን ሁሉ ይወስዳል፤ ካህኑም ለእግዚአብሔር በጎ መዓዛ እንዲሆን በመሠዊያው ላይ ይጨምረዋል፤ ካህኑም ስለ እርሱ ያስተሰርያል፤ ኀጢአቱም ይሰረይለታል።
የሆድ ዕቃውንና እግሮቹንም በውኃ አጠበ፤ ሙሴም አውራውን በግ ሁሉ በመሠዊያው ላይ ጨመረ፤ ይህ በጎ መዓዛ እንዲሆን የሚቃጠል መሥዋዕት ነበረ፤ እግዚአብሔር ሙሴን እንዳዘዘው ለእግዚአብሔር የእሳት ቍርባን ነበረ።
እሳትም ከእግዚአብሔር ዘንድ ወጣ፤ በመሠዊያውም ላይ የሚቃጠለውን መሥዋዕት፥ ስቡንም በላ፤ ሕዝቡም ሁሉ አይተው ተደነቁ፤ በግምባራቸውም ወደቁ።
በፍጹም ልብ በፍጹም አእምሮም በፍጹም ነፍስም በፍጹም ኀይልም እርሱን መውደድ፥ ባልንጀራንም እንደ ራስ መውደድ በሙሉ ከሚቃጠል መሥዋዕትና ከሌላው መሥዋዕት ሁሉ የሚበልጥ ነው፡” አለው።
ክርስቶስ እንደ ወደዳችሁ፥ ራሱንም ለእግዚአብሔር በጎ መዓዛ የሚሆን መሥዋዕትና ቍርባን አድርጎ እንደ ሰጠላችሁ በፍቅር ተመላለሱ።
ነገር ግን ሁሉ አለኝ፤ ይበዛልኝማል፤ የመዓዛ ሽታና የተወደደ መሥዋዕት የሚሆነውን፥ ለእግዚአብሔርም ደስ የሚያሰኘውን ስጦታችሁን ከአፍሮዲጡ ተቀብዬ አሟልቻለሁ።
ሳሙኤልም አንድ የበግ ጠቦት ወስዶ ለእግዚአብሔር ፈጽሞ የሚቃጠል መሥዋዕት አድርጎ ከሕዝቡ ጋር አቀረበው፤ ሳሙኤልም ስለ እስራኤል ወደ እግዚአብሔር ጮኸ፥ እግዚአብሔርም ሰማው።