ዘፀአት 27:1 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) “ርዝመቱ አምስት ክንድ፥ ወርዱም አምስት ክንድ መሠዊያን ከማይነቅዝ ዕንጨት አድርግ፤ አራት ማዕዘንም ይሁን፤ ከፍታውም ሦስት ክንድ ይሁን። አዲሱ መደበኛ ትርጒም “ከፍታው ሦስት ክንድ የሆነ መሠዊያ ከግራር ዕንጨት ሥራ፤ ርዝመቱ ዐምስት፣ ወርዱም ዐምስት ክንድ ሆኖ ባለአራት ማእዘን ይሁን። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) “ርዝመቱ አምስት ክንድ፥ ወርዱ አምስት ክንድ የሆነ መሠዊያ ከግራር እንጨት ሥራ፤ መሠዊያው አራት ማዕዘን ይሁን፤ ከፍታው ሦስት ክንድ ይሁን። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም “ከግራር እንጨት መሠዊያ ሥራ፤ ርዝመቱ ሁለት ሜትር ከኻያ ሳንቲ ሜትር የጐኑ ስፋት ሁለት ሜትር ከኻያ ሳንቲ ሜትር ቁመቱም አንድ ሜትር ከሠላሳ ሳንቲ ሜትር ይሁን። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ርዝመቱ አምስት ክንድ፥ ወርዱም አምስት ክንድ መሠዊያ ከግራር እንጨት አድርግ፤ አራት ማዕዘንም ይሁን፤ ከፍታውም ሦስት ክንድ ይሁን። |
በእግዚአብሔርም ፊት የነበረውን የናሱን መሠዊያ ከእግዚአብሔር ቤት ፊት ከመሠዊያውና ከእግዚአብሔር ቤት መካከል ፈቀቅ አድርጎ በመሠዊያው አጠገብ በሰሜን በኩል አኖረው።
አሮንና ልጆቹ ግን የእግዚአብሔር አገልጋይ ሙሴ እንዳዘዘው ሁሉ ለቅድስተ ቅዱሳን ሥራ ሁሉ ስለ እስራኤልም ያስተሰርይ ዘንድ ለሚቃጠለው መሥዋዕት በሚሆነው መሠዊያ ላይ ይሠዉ ነበር፥ በዕጣኑም መሠዊያ ላይ ያጥኑ ነበር።
የኢዮሴዴቅም ልጅ ኢያሱ፥ ወንድሞቹም ካህናቱ፥ የሰላትያልም ልጅ ዘሩባቤል፥ ወንድሞቹም ተነሥተው በእግዚአብሔር ሰው በሙሴ ሕግ እንደ ተጻፈ የሚቃጠለውን መሥዋዕት ያቀርቡበት ዘንድ የእስራኤልን አምላክ መሠዊያ ሠሩ።
ሙሴም የእግዚአብሔርን ቃሎች ጻፈ፤ ማለዳም ተነሣ፤ ከተራራውም በታች መሠዊያን ሠራ፤ ዐሥራ ሁለትም ድንጋዮችን ለዐሥራ ሁለቱ የእስራኤል ነገድ አቆመ።
ለሚቃጠል መሥዋዕት የሚሆነውን መሠዊያውን፥ የናሱንም መከታ፥ መሎጊያዎቹንም፥ ዕቃውንም ሁሉ፥ የመታጠቢያውን ሰንም፥ መቀመጫውንም፤
ለሚቃጠል መሥዋዕትም የሚሆነውን መሠዊያ፥ ዕቃውንም ሁሉ ትቀባዋለህ፤ መሠዊያውንም ትቀድሳለህ፤ መሠዊያውም ቅዱሰ ቅዱሳን ይሆናል።
ለሚቃጠል መሥዋዕት የሚሆነውን መሠዊያም በምስክሩ ድንኳን ደጅ አኖረ፤ እግዚአብሔርም ሙሴን እንዳዘዘው በላዩ መሥዋዕቱንና ቍርባኑን አቀረበ።
ታቦቱንም፥ ገበታውንም፥ መቅረዙንም፥ መሠዊያዎቹንም፥ የሚያገለግሉበትንም የመቅደሱን ዕቃ፥ መጋረጃውንም፥ ማገልገያውንም ሁሉ ይጠብቃሉ።
የሚያገለግሉበትን ዕቃውን ሁሉ፥ ማንደጃዎቹን፥ ሜንጦዎቹንም፥ ጽዋዎቹንም፥ ድስቶቹንም፥ መክደኛዎቹንም፥ ያመድ ማፍሰሻዎቹን፥ የመሠዊያውን ዕቃ ሁሉ ያስቀምጡበት፤ በእርሱም የአቆስጣን ቍርበት መሸፈኛ ይዘርጉ፤ መሎጊያዎቹንም ያግቡ። ሐምራዊዉንም መጐናጸፊያ ወስደው ማስታጠቢያውንና ማስቀመጫውን ይሸፍኑት፤ በአቆስጣው ቍርበት መሸፈኛ ውስጥም አድርገው በመሸከሚያዎቹ ላይ ያኑሩት፤