Biblia Todo Logo
La Biblia Online

- Anuncios -




ዘፀአት 40:10 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

10 ለሚ​ቃ​ጠል መሥ​ዋ​ዕ​ትም የሚ​ሆ​ነ​ውን መሠ​ዊያ፥ ዕቃ​ው​ንም ሁሉ ትቀ​ባ​ዋ​ለህ፤ መሠ​ዊ​ያ​ው​ንም ትቀ​ድ​ሳ​ለህ፤ መሠ​ዊ​ያ​ውም ቅዱሰ ቅዱ​ሳን ይሆ​ናል።

Ver Capítulo Copiar

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

10 ከዚያም የሚቃጠል መሥዋዕት መሠዊያውንና ዕቃዎቹን ሁሉ ቅባ፤ መሠዊያውን ቀድስ፣ እጅግም የተቀደሰ ይሆናል።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

10 የሚቃጠል መሥዋዕት መሠዊያውንና ዕቃዎቹን ሁሉ ትቀባለህ፥ መሠዊያውንም ትቀድሳለህ፤ መሠዊያውም እጅግ የተቀደሰ ይሆናል።

Ver Capítulo Copiar

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

10 ቀጥሎም መሠዊያውን ከመገልገያ ዕቃዎቹ ጋር በመቀባት ለእግዚአብሔር የተለየ አድርገው፤ ፈጽሞም የተቀደሰ ይሆናል።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

10 ለሚቃጠል መሥዋዕት የሚሆነውንም መሠዊያ ዕቃውንም ሁሉ ትቀባዋለህ፥ መሠዊያውንም ትቀድሳለህ፤ መሠዊያውም ቅድስተ ቅዱሳን ይሆናል።

Ver Capítulo Copiar




ዘፀአት 40:10
13 Referencias Cruzadas  

መል​አ​ኩም መልሶ እን​ዲህ አላት፥ “መን​ፈስ ቅዱስ ያድ​ር​ብ​ሻል፤ የል​ዑል ኀይ​ልም ይጋ​ር​ድ​ሻል፤ ከአ​ንቺ የሚ​ወ​ለ​ደ​ውም ቅዱስ ነው፤ የል​ዑል እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ልጅም ይባ​ላል።


የጌታ የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር መን​ፈስ በእኔ ላይ ነው፤ ለድ​ሆች የም​ሥ​ራ​ችን እሰ​ብክ ዘንድ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ቀብ​ቶ​ኛ​ልና፤ ልባ​ቸው የተ​ሰ​በ​ረ​ውን እጠ​ግን ዘንድ፥ ለተ​ማ​ረ​ኩ​ትም ነጻ​ነ​ትን፥ ለታ​ሰ​ሩ​ትም መፈ​ታ​ትን፥ ለዕ​ው​ራ​ንም ማየ​ትን እና​ገር ዘንድ ልኮ​ኛል።


ቅዱ​ስና ያለ ተን​ኰል፥ ነው​ርም የሌ​ለ​በት፥ ከኀ​ጢ​አ​ተ​ኞ​ችም የተ​ለየ፥ ከሰ​ማ​ያ​ትም ከፍ ከፍ ያለ፥ እን​ደ​ዚህ ያለ ሊቀ ካህ​ናት ይገ​ባ​ናል።


ኀጢ​አት የሌ​ለ​በት እርሱ እኛን ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ያጸ​ድ​ቀን ዘንድ ስለ እኛ ራሱን እንደ ኃጥእ አድ​ር​ጓ​ልና።


እና​ን​ተም በኢ​የ​ሱስ ክር​ስ​ቶስ ከእ​ርሱ ናችሁ፤ በእ​ር​ሱም ከእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ጥበ​ብ​ንና ጽድ​ቅን፥ ቅድ​ስ​ና​ንና ቤዛ​ነ​ትን አገ​ኘን።


እነ​ር​ሱም በእ​ው​ነት ቅዱ​ሳን ይሆኑ ዘንድ ስለ እነ​ርሱ እኔ ራሴን እቀ​ድ​ሳ​ለሁ።


እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር የላ​ከው የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ቃል ይና​ገ​ራል፤ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር መን​ፈ​ሱን ሰፍሮ አይ​ሰ​ጥ​ምና።


የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር መን​ፈስ፥ የጥ​በ​ብና የማ​ስ​ተ​ዋል መን​ፈስ፥ የም​ክ​ርና የኀ​ይል መን​ፈስ፥ የዕ​ው​ቀ​ትና የእ​ው​ነት መን​ፈስ ያር​ፍ​በ​ታል።


ይቀ​ድ​ሳ​ቸ​ውም ዘንድ መሠ​ዊ​ያ​ው​ንና ዕቃ​ውን ሁሉ፥ የመ​ታ​ጠ​ቢ​ያ​ውን ሰንና መቀ​መ​ጫ​ውን ቀባ፤ ድን​ኳ​ኒ​ቱ​ንና ዕቃ​ዋን ሁሉ ቀብቶ ቀደ​ሳ​ቸው።


የመ​ታ​ጠ​ቢ​ያ​ውን ሰንና መቀ​መ​ጫ​ው​ንም ቀብ​ተህ ትቀ​ድ​ሳ​ለህ።


በእ​ርሾ ቦክቶ አይ​ጋ​ገ​ርም። ከእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር መሥ​ዋ​ዕት የሰ​ጠ​ኋ​ቸው ዕድል ፈንታ ይህ ነው፤ እር​ሱም እንደ ኀጢ​አ​ትና እንደ በደል መሥ​ዋ​ዕት ቅዱሰ ቅዱ​ሳን ነው።


ሁሉ​ንም ትቀ​ድ​ሳ​ቸ​ዋ​ለህ፤ ቅዱሰ ቅዱ​ሳ​ንም ይሆ​ናሉ፤ የሚ​ነ​ካ​ቸ​ውም ሁሉ ቅዱስ ይሆ​ናል።


Síguenos en:

Anuncios


Anuncios