Biblia Todo Logo
La Biblia Online
- Anuncios -




ዘፀአት 40:29 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

29 ለሚ​ቃ​ጠል መሥ​ዋ​ዕት የሚ​ሆ​ነ​ውን መሠ​ዊ​ያም በም​ስ​ክሩ ድን​ኳን ደጅ አኖረ፤ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ሙሴን እን​ዳ​ዘ​ዘው በላዩ መሥ​ዋ​ዕ​ቱ​ንና ቍር​ባ​ኑን አቀ​ረበ።

Ver Capítulo Copiar

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

29 የሚቃጠል መሥዋዕት መሠዊያውንም በማደሪያው፣ በመገናኛው ድንኳን መግቢያ ላይ አኖረው፤ እግዚአብሔር እንዳዘዘውም የሚቃጠለውን መሥዋዕትና የእህሉን መሥዋዕት በላዩ ላይ አቀረበ።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

29 ጌታ ሙሴን እንዳዘዘው የሚቃጠል መሥዋዕት መሠዊያውን በመገናኛው ድንኳን በማደሪያው መግቢያ ፊት አኖረ፥ የሚቃጠልና የእህልን መሥዋዕት ሠዋበት።

Ver Capítulo Copiar

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

29 እዚያም በድንኳኑ መግቢያ ፊት ለፊት የሚቃጠል መሥዋዕት የሚቀርብበትን መሠዊያ አኖረ፤ የሚቃጠለውን መሥዋዕትና የእህሉን ቊርባን እግዚአብሔር ባዘዘው መሠረት በእርሱ ላይ አቀረበ፤

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

29 ለሚቃጠል መሥዋዕት የሚሆነውን መሠዊያ በመገናኛው ድንኳን በማደሪያው ደጅ ፊት አኖረ፥ የሚቃጠለውንና የእህልን መሥዋዕት ሠዋበት።

Ver Capítulo Copiar




ዘፀአት 40:29
15 Referencias Cruzadas  

በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ፊት የነ​በ​ረ​ውን የና​ሱን መሠ​ዊያ ከእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ቤት ፊት ከመ​ሠ​ዊ​ያ​ውና ከእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ቤት መካ​ከል ፈቀቅ አድ​ርጎ በመ​ሠ​ዊ​ያው አጠ​ገብ በሰ​ሜን በኩል አኖ​ረው።


ሙሴም እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እንደ አዘ​ዘው በድ​ን​ኳኑ ደጅ ፊት መጋ​ረ​ጃ​ውን ዘረጋ።


የመ​ታ​ጠ​ቢ​ያ​ው​ንም ሰን በም​ስ​ክሩ ድን​ኳ​ንና በመ​ሠ​ዊ​ያው መካ​ከል አኖረ፤ ለመ​ታ​ጠ​ቢ​ያም ውኃን ጨመ​ረ​በት።


ለሚ​ቃ​ጠል መሥ​ዋ​ዕት የሚ​ሆ​ነ​ው​ንም መሠ​ዊያ በም​ስ​ክሩ ድን​ኳን ደጅ ፊት ታኖ​ረ​ዋ​ለህ።


አደ​ባ​ባ​ዩ​ንም በአ​ራት ማዕ​ዘኑ ርዝ​መ​ቱን መቶ ክንድ፥ ወር​ዱ​ንም መቶ ክንድ አድ​ርጎ ለካ፤ መሠ​ዊ​ያ​ውም በቤቱ ፊት ነበረ።


እን​ዲ​ህም አለኝ፥ “የሰው ልጅ ሆይ! ጌታ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እን​ዲህ ይላል፦ የሚ​ቃ​ጠ​ለ​ውን መሥ​ዋ​ዕት ያቀ​ር​ቡ​በት ዘንድ፥ ደሙ​ንም ይረ​ጩ​በት ዘንድ በሚ​ሠ​ሩ​በት ቀን የመ​ሠ​ዊ​ያው ሕግ ይህ ነው።


እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ከም​ስ​ክሩ ድን​ኳን ውስጥ ሙሴን ጠርቶ እን​ዲህ ሲል ተና​ገ​ረው፦


እናንተ ደንቆሮዎችና ዕውሮች! ማናቸው ይበልጣል? መባው ነውን? ወይስ መባውን የሚቀድሰው መሠዊያው?


ድን​ኳ​ኒ​ቱን ሲያ​ገ​ለ​ግሉ የነ​በሩ ካህ​ናት ከእ​ርሱ ሊበሉ የማ​ይ​ቻ​ላ​ቸው መሠ​ዊያ አለን፤


የዘ​ለ​ዓ​ለም መድ​ኀ​ኒ​ትን ገን​ዘብ አድ​ርጎ፥ በገዛ ደሙ አንድ ጊዜ ወደ መቅ​ደስ ገባ እንጂ በላ​ምና በፍ​የል ደም አይ​ደ​ለም።


Síguenos en:

Anuncios


Anuncios


¡Síguenos en WhatsApp! Síguenos