ዘፀአት 23:22 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) አንተ ግን ቃሌን ብትሰማ፥ ያልሁህንም ሁሉ ብታደርግ፥ ጠላቶችህን እጥላቸዋለሁ፤ የሚቃወሙህንም እቃወማለሁ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም የሚናገረውን በጥንቃቄ ብታደምጥና ያልኩህን ሁሉ ብታደርግ ለጠላቶችህ ጠላት እሆናለሁ፤ የሚቃወሙህን እቃወማለሁ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) አንተ ግን ቃሉን ብትሰማ፥ ያልሁህንም ሁሉ ብታደርግ፥ ጠላቶችህን እጠላለሁ፥ የሚቃወሙህንም እቃወማለሁ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ለእርሱ ብትታዘዝና እኔ ያዘዝኩህንም ሁሉ ብትፈጽም ጠላቶችህን እጠላለሁ፤ ተቃዋሚዎችህንም እዋጋለሁ፤ መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) አንተ ግን ቃሉን ብትሰማ፥ ያልሁህንም ሁሉ ብታደርግ፥ ጠላቶችህን እጣላቸዋለሁ፥ የሚያስጨንቁህንም አስጨንቃቸዋልሁ። |
ፍርሀትና ድንጋጤ ወደቀባቸው፤ የክንድህ ብርታትም ከድንጋይ ይልቅ ጸና፤ አቤቱ፥ ሕዝብህ እስኪያልፉ ድረስ፥ የተቤዠሃቸው እኒህ ሕዝብህ እስኪያልፉ ድረስ፤
ልጆቻቸውም እንደ ቀድሞው ይሆናሉ፤ ምስክርነታቸውም በፊቴ ጸንቶ ይኖራል፤ የሚያስጨንቁአቸውንም ሁሉ እቀጣለሁ።
እግዚአብሔር ከግብፅ መርቶ አውጥቶታል፤ አንድ ቀንድ እንዳለው ክብር አለው፤ ጠላቶቹን አሕዛብን ይበላል፤ አጥንቶቻቸውንም ይሰባብራል፤ በፍላጾቹም ጠላቱን ይወጋዋል።
አርፎአል፥ እንደ አንበሳና እንደ አንበሳ ደቦል ተጋድሞአል፤ ማን ያስነሣዋል? የሚመርቁህ ሁሉ የተመረቁ ይሁኑ፤ የሚረግሙህም ሁሉ የተረገሙ ይሁኑ።”
“እንዲህም ይሆናል፤ የአምላክህን የእግዚአብሔርን ቃል ፈጽመህ ብትሰማ፥ ዛሬም ያዘዝሁህን ትእዛዙን ሁሉ ብታደርግ፥ ብትጠብቅም፥ አምላክህ እግዚአብሔር ከምድር አሕዛብ ሁሉ በላይ ከፍ ከፍ ያደርግሃል።
ጌታ ኢየሱስ ከኀያላን መላእክቱ ጋር ከሰማይ በእሳት ነበልባል ሲገለጥ፥ መከራን ለሚያሳዩአችሁ መከራን፥ መከራንም ለምትቀበሉ ከእኛ ጋር ዕረፍትን ብድራት አድርጎ እንዲመልስ በእግዚአብሔር ፊት በእርግጥ ጽድቅ ነውና።
የእስራኤልም ልጆች ኤዌዎናውያንን፥ “ምናልባት በመካከላችን የምትቀመጡ እንደ ሆነ እንዴትስ ከእናንተ ጋር ቃል ኪዳን እናደርጋለን?” አሉአቸው።