ዘፀአት 20:9 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ስድስት ቀን ሥራህን ሥራ፤ ተግባርህንም ሁሉ አድርግ፤ አዲሱ መደበኛ ትርጒም ስድስት ቀን ሥራ፤ ተግባርህንም ሁሉ አከናውን። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ስድስት ቀን ሥራህን ሥራ፥ ተግባርህንም ሁሉ ፈጽም፤ አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ሥራህን ሁሉ የምታከናውንባቸው ስድስት ቀኖች አሉልህ፤ መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ስድስት ቀን ሥራ ተግባርህንም ሁሉ አድርግ፤ |
ስድስት ቀን ሥራህን ሁሉ ሥራ፤ በሬህና አህያህ ያርፉ ዘንድ ለባሪያህም ልጅ ለመጻተኛውም ዕረፍት ይሆን ዘንድ በሰባተኛው ቀን ዕረፍ።
ስድስት ቀን ሥራህን ሥራ፤ ሰባተኛዋ ቀን ግን ለእግዚአብሔር የተቀደስች የዕረፍት ሰንበት ናት፤ በሰንበት ቀን የሚሠራ ሁሉ ፈጽሞ ይገደል።
“ስድስት ቀን ሥራህን ትሠራለህ፤ በሰባተኛውም ቀን ታርፋለህ። በምትዘራበትና በምታጭድበት ዘመን ታርፋለህ።
ስድስት ቀን ሥራህን ትሠራለህ፤ በሰባተኛው ቀን ታርፋለህ፤ ለእግዚአብሔር የተቀደሰ የዕረፍት ሰንበት ነው፤ የሚሠራበትም ሁሉ ይሙት።
ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፥ “በውስጠኛው አደባባይ ወደ ምሥራቅ የሚመለከተው በር ሥራ በሚሠራበት በስድስቱ ቀን ተዘግቶ ይቈይ፤ ነገር ግን በሰንበት ቀን ይከፈት፤ በመባቻ ቀንም ይከፈት።
ስድስት ቀን ሥራህን ትሠራለህ፤ በሰባተኛው ቀን ግን የዕረፍት ሰንበት ነው፤ ለእግዚአብሔር ቅዱስ ጉባኤ ይሆንበታል፤ ምንም ሥራ አትሠሩም፤ በምትኖሩበት ሁሉ ለእግዚአብሔር ሰንበት ነው።
የምኵራቡ ሹምም ጌታ ኢየሱስ በሰንበት ፈውሶአልና፤ እየተቈጣ መልሶ ሕዝቡን እንዲህ አላቸው፥ “ሥራችሁን የምትሠሩባቸው ስድስት ቀኖች ያሉ አይደለምን? ያንጊዜ ኑና ተፈወሱ፤ በሰንበት ቀን ግን አይሆንም።”