Biblia Todo Logo
La Biblia Online
- Anuncios -




ዘፀአት 31:15 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

15 ስድ​ስት ቀን ሥራ​ህን ሥራ፤ ሰባ​ተ​ኛዋ ቀን ግን ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር የተ​ቀ​ደ​ስች የዕ​ረ​ፍት ሰን​በት ናት፤ በሰ​ን​በት ቀን የሚ​ሠራ ሁሉ ፈጽሞ ይገ​ደል።

Ver Capítulo Copiar

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

15 ስድስት ቀን ሥራ ይሠራል፤ ሰባተኛው ቀን ግን ለእግዚአብሔር የተቀደሰ የዕረፍት ሰንበት ነው፤ በሰንበት ቀን ማንም ቢሠራ በሞት መቀጣት አለበት።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

15 ስድስት ቀን ሥራ ይሠራል፥ ሰባተኛው ቀን ግን ለጌታ የተቀደሰ የዕረፍት ሰንበት ነው፤ በሰንበት ቀን የሚሠራ ሁሉ ፈጽሞ ይገደል።

Ver Capítulo Copiar

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

15 ሥራችሁን ሁሉ የምታከናውኑባቸው ስድስት የሥራ ቀኖች አሉላችሁ፤ ሰባተኛው ቀን ግን ለእኔ ተለይቶ የተቀደሰ የዕረፍት ቀን ነው፤ በዚህ ቀን ሥራ የሚሠራበት ሁሉ በሞት ይቀጣ።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

15 ስድስት ቀን ሥራን ሥራ፤ ሰባተኛው ቀን ግን ለእግዚአብሔር የተቀደሰ የዕረፍት ሰንበት ነው፤ በሰንበት ቀን የሚሠራ ሁሉ ፈጽሞ ይገደል።

Ver Capítulo Copiar




ዘፀአት 31:15
21 Referencias Cruzadas  

እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም የሠ​ራ​ውን ሥራ በስ​ድ​ስ​ተ​ኛው ቀን ፈጸመ፤ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም በሰ​ባ​ተ​ኛው ቀን ከሠ​ራው ሥራ ሁሉ ዐረፈ።


ሙሴም፥ “እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር የተ​ና​ገ​ረው ይህ ነው፦ ነገ ዕረ​ፍት፥ ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም የተ​ቀ​ደሰ ሰን​በት ነው፤ ነገ የም​ት​ጋ​ግ​ሩ​ትን ዛሬ ጋግሩ፤ የም​ት​ቀ​ቅ​ሉ​ት​ንም ቀቅሉ፤ የተ​ረ​ፈ​ው​ንም ሁሉ ለነገ እን​ዲ​ጠ​በቅ አኑሩ” አላ​ቸው።


ስድ​ስት ቀን ልቀ​ሙት፤ ሰባ​ተ​ኛው ቀን ግን ሰን​በት ነው፤ በእ​ርሱ አይ​ገ​ኝም” አለ።


ስድ​ስት ቀን ሥራ​ህን ሁሉ ሥራ፤ በሬ​ህና አህ​ያህ ያርፉ ዘንድ ለባ​ሪ​ያ​ህም ልጅ ለመ​ጻ​ተ​ኛ​ውም ዕረ​ፍት ይሆን ዘንድ በሰ​ባ​ተ​ኛው ቀን ዕረፍ።


ለእ​ና​ንተ በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር የተ​ቀ​ደ​ሰች ናትና ሰን​በ​ቴን ጠብቁ፤ የሚ​ያ​ረ​ክ​ሳ​ትም ሰው ሁሉ ፈጽሞ ይገ​ደል፤ ሥራ​ንም በእ​ር​ስዋ የሠራ ሰው ሁሉ ያች ነፍስ ከሕ​ዝ​ብዋ መካ​ከል ተለ​ይታ ትጥፋ።


የእ​ስ​ራ​ኤ​ልም ልጆች ለልጅ ልጃ​ቸው ለዘ​ለ​ዓ​ለም ቃል ኪዳን ዕረ​ፍት ያደ​ርጉ ዘንድ ሰን​በ​ትን ይጠ​ብቁ።


እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ሰማ​ይ​ንና ምድ​ርን በስ​ድ​ስት ቀን ስለ ፈጠረ፥ በሰ​ባ​ተ​ኛ​ውም ቀን ሥራ​ውን ፈጽሞ ስላ​ረፈ፥ በእ​ኔና በእ​ስ​ራ​ኤል ልጆች ዘንድ የዘ​ለ​ዓ​ለም ምል​ክት ነው።”


“ስድ​ስት ቀን ሥራ​ህን ትሠ​ራ​ለህ፤ በሰ​ባ​ተ​ኛ​ውም ቀን ታር​ፋ​ለህ። በም​ት​ዘ​ራ​በ​ትና በም​ታ​ጭ​ድ​በት ዘመን ታር​ፋ​ለህ።


ስድ​ስት ቀን ሥራ​ህን ትሠ​ራ​ለህ፤ በሰ​ባ​ተ​ኛው ቀን ታር​ፋ​ለህ፤ ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር የተ​ቀ​ደሰ የዕ​ረ​ፍት ሰን​በት ነው፤ የሚ​ሠ​ራ​በ​ትም ሁሉ ይሙት።


በማ​ደ​ሪ​ያ​ዎ​ቻ​ችሁ ውስጥ በሰ​ን​በት ቀን እሳ​ትን አታ​ን​ድዱ፤ እኔ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ነኝ።”


ጌታ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እን​ዲህ ይላል፥ “በው​ስ​ጠ​ኛው አደ​ባ​ባይ ወደ ምሥ​ራቅ የሚ​መ​ለ​ከ​ተው በር ሥራ በሚ​ሠ​ራ​በት በስ​ድ​ስቱ ቀን ተዘ​ግቶ ይቈይ፤ ነገር ግን በሰ​ን​በት ቀን ይከ​ፈት፤ በመ​ባቻ ቀንም ይከ​ፈት።


“ይህም የዘ​ለ​ዓ​ለም ሥር​ዐት ይሁ​ን​ላ​ችሁ።


ስድ​ስት ቀን ሥራ​ህን ትሠ​ራ​ለህ፤ በሰ​ባ​ተ​ኛው ቀን ግን የዕ​ረ​ፍት ሰን​በት ነው፤ ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ቅዱስ ጉባኤ ይሆ​ን​በ​ታል፤ ምንም ሥራ አት​ሠ​ሩም፤ በም​ት​ኖ​ሩ​በት ሁሉ ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ሰን​በት ነው።


የዕ​ረ​ፍት ሰን​በት ትሁ​ን​ላ​ችሁ፤ ሰው​ነ​ታ​ች​ሁ​ንም አዋ​ርዱ፤ በወሩ በዘ​ጠ​ነ​ኛው ቀን ከማታ ጀም​ራ​ችሁ እስከ ዐሥ​ረ​ኛው ቀን ማታ ድረስ፥ ሰን​በ​ታ​ች​ሁን አድ​ርጉ።”


የም​ኵ​ራቡ ሹምም ጌታ ኢየ​ሱስ በሰ​ን​በት ፈው​ሶ​አ​ልና፤ እየ​ተ​ቈጣ መልሶ ሕዝ​ቡን እን​ዲህ አላ​ቸው፥ “ሥራ​ች​ሁን የም​ት​ሠ​ሩ​ባ​ቸው ስድ​ስት ቀኖች ያሉ አይ​ደ​ለ​ምን? ያን​ጊዜ ኑና ተፈ​ወሱ፤ በሰ​ን​በት ቀን ግን አይ​ሆ​ንም።”


“ዕለተ ሰን​በ​ትን ጠብቅ፤ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር አም​ላ​ክህ እን​ዳ​ዘ​ዘ​ህም ቀድ​ሳት።


እን​ኪ​ያስ የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ሕዝብ የሚ​ገ​ቡ​በት ጸንቶ የሚ​ኖር ዕረ​ፍት እን​ዳለ ታወቀ።


Síguenos en:

Anuncios


Anuncios


¡Síguenos en WhatsApp! Síguenos