ዘፀአት 2:25 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) እግዚአብሔርም የእስራኤልን ልጆች ጐበኛቸው፤ ታወቀላቸውም። አዲሱ መደበኛ ትርጒም እግዚአብሔርም እስራኤላውያንን ተመለከተ፤ ስለ እነርሱም ገደደው። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) እግዚአብሔርም የእስራኤልን ሕዝቦች አየ፥ እግዚአብሔርም የደረሰባቸውን ነገር አወቀ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም እግዚአብሔር እስራኤላውያን በባርነት መጨነቃቸውን አይቶ ስለ እነርሱ አሰበ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) እግዚአብሔርም የእስራኤልን ልጆች አየ፤ እግዚአብሔርም በእነርሱ ያለውን ነገር አወቀ። |
ሙሴም እግዚአብሔር በፈርዖንና በግብፃውያን ላይ ስለ እስራኤል ያደረገውን ሁሉ፥ በመንገድም ያገኛቸውን ድካም ሁሉ፥ እግዚአብሔርም እንደ አዳናቸው ለአማቱ ነገረው።
ሕዝቡም አመኑ፤ ደስም አላቸው፤ እግዚአብሔር የእስራኤልን ልጆች ጐብኝቶአልና፤ ጭንቀታቸውንም አይቶአልና፤ ሕዝቡም ራሳቸውን ዝቅ አድርገው ሰገዱ።
በግብፅ ያሉትን የወገኖችን መከራ ማየትን አይቻለሁ፤ ጩኸታቸውንም ሰምቻለሁ፤ ላድናቸውም ወርጃለሁ፤ አሁንም ና ወደ ግብፅ ሀገር ልላክህ።’
ወደ አባቶቻችንም አምላክ ወደ እግዚአብሔር ጮኽን፤ እግዚአብሔርም ቃላችንን ሰማ፤ ጭንቀታችንንም፥ ድካማችንንም፥ ግፋችንንም አየ፤
እርስዋም፥ “አዶናይ፥ የሠራዊት አምላክ እግዚአብሔር ሆይ! የባርያህን መዋረድ ተመልክተህ ብታስበኝ፥ ለባርያህም ወንድ ልጅ ብትሰጥ ዕድሜውን ሁሉ ለአንተ እሰጠዋለሁ፤ የወይን ጠጅና የሚያሰክር መጠጥም አይጠጣም። ምላጭም በራሱ ላይ አይደርስም” ብላ ስእለት ተሳለች።