La Biblia Online

Anuncios


Toda la Biblia A.T. N.T.




ዘፀአት 17:1 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

የእ​ስ​ራ​ኤል ልጆች ማኅ​በር ሁሉ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እን​ዳ​ዘዘ ከሲን ምድረ በዳ ሊጓዙ ተነሡ፤ በራ​ፊ​ድም ሰፈሩ፤ በዚ​ያም ሕዝቡ የሚ​ጠ​ጡት ውኃ አል​ነ​በ​ረም።

Ver Capítulo

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

መላው የእስራኤል ማኅበር ከሲና ምድረ በዳ ተነሥቶ እግዚአብሔር እንዳዘዘው ከስፍራ ወደ ስፍራ ተጕዞ በራፊዲም ሰፈረ፤ ነገር ግን ሕዝቡ የሚጠጡት ውሃ አልነበረም።

Ver Capítulo

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

የእስራኤል ልጆች ማኅበር ሁሉ ጌታ እንዳዘዘ ሊጓዙ ከሲን ምድረ በዳ ተነሡ፥ በረፊዲምም ሰፈሩ፤ ሕዝቡ የሚጠጡት ውኃ አልነበረም።

Ver Capítulo

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

መላው የእስራኤል ሕዝብ በእግዚአብሔር ትእዛዝ ከቦታ ወደ ቦታ በመዘዋወር “ሲን” ተብሎ የሚጠራውን ምድረ በዳ ትተው በረፊዲም ሰፈሩ፤ ነገር ግን በዚያ የሚጠጣ ውሃ አልነበረም።

Ver Capítulo

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

የእስራኤል ልጆች ማኅበር ሁሉ እግዚአብሔር እንዳዘዘ ከሲን ምድረ በዳ ሊጓዙ ተነሡ፥ በራፊዲምም ሰፈሩ፤ ሕዝቡም ይጠጡ ዘንድ ውኃ አልነበረም።

Ver Capítulo



ዘፀአት 17:1
8 Referencias Cruzadas  

ሙሴም የእ​ስ​ራ​ኤ​ልን ልጆች ከኤ​ር​ትራ ባሕር አው​ጥቶ ወደ ሱር ምድረ በዳ ወሰ​ዳ​ቸው። በም​ድረ በዳም ሦስት ቀን ተጓዙ፤ ይጠ​ጡም ዘንድ ውኃ አላ​ገ​ኙም።


የእ​ስ​ራ​ኤ​ልም ልጆች ማኅ​በር ሁሉ ከኤ​ሎም ተጓዙ፤ ከግ​ብፅ ሀገር ከወጡ በኋላ በሁ​ለ​ተ​ኛው ወር ከወ​ሩም በዐ​ሥራ አም​ስ​ተ​ኛው ቀን በኤ​ሎ​ምና በሲና መካ​ከል ወዳ​ለ​ችው ወደ ሲን ምድረ በዳ መጡ።


ዐማ​ሌ​ቅም መጥቶ ከእ​ስ​ራ​ኤል ጋራ በራ​ፊድ ተዋጋ።


ከራ​ፊ​ድም ተነ​ሥ​ተው ወደ ሲና ምድረ በዳ መጡ፤ በዚ​ያም እስ​ራ​ኤል በተ​ራ​ራው ፊት ሰፈሩ።


ለማ​ኅ​በ​ሩም ውኃ አል​ነ​በ​ረም፤ ሕዝ​ቡም በሙ​ሴና በአ​ሮን ላይ ተሰ​በ​ሰቡ።


ደመ​ና​ውም ከድ​ን​ኳኑ ላይ በተ​ነሣ ጊዜ በዚ​ያን ጊዜ የእ​ስ​ራ​ኤል ልጆች ይጓዙ ነበር፤ ደመ​ና​ውም በቆ​መ​በት ስፍራ በዚያ የእ​ስ​ራ​ኤል ልጆች ይሰ​ፍሩ ነበር።


በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ትእ​ዛዝ ይሰ​ፍሩ ነበር፤ በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ትእ​ዛዝ ይጓዙ ነበር፤ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር በሙሴ ቃል እንደ አዘዘ የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ትእ​ዛዝ ይጠ​ብቁ ነበር።