Biblia Todo Logo
La Biblia Online

- Anuncios -




ዘፀአት 15:22 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

22 ሙሴም የእ​ስ​ራ​ኤ​ልን ልጆች ከኤ​ር​ትራ ባሕር አው​ጥቶ ወደ ሱር ምድረ በዳ ወሰ​ዳ​ቸው። በም​ድረ በዳም ሦስት ቀን ተጓዙ፤ ይጠ​ጡም ዘንድ ውኃ አላ​ገ​ኙም።

Ver Capítulo Copiar

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

22 ከዚያም ሙሴ እስራኤልን ከቀይ ባሕር እየመራቸው ወደ ሱር ምድረ በዳ ሄዱ፤ ለሦስት ቀናት ውሃ ሳያገኙም በምድረ በዳ ተጓዙ።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

22 ሙሴም እስራኤልን ከቀይ ባሕር መራ፥ ወደ ሹር ምድረ በዳም ሄዱ፤ በምድረ በዳም ሦስት ቀን ሄዱ፥ ውኃም አላገኙም።

Ver Capítulo Copiar

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

22 ከዚህ በኋላ ሙሴ የእስራኤልን ሕዝብ ከቀይ ባሕር አሳልፎ ወደ ሱር በረሓ መራቸው፤ ሦስት ቀን ሙሉ በበረሓ ተጓዙ፤ ነገር ግን ምንም ውሃ አላገኙም።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

22 ሙሴም እስራኤልን ከኤርትራ ባሕር አስጓዘ፥ ወደ ሱርም ምድረ በዳ ወጡ፤ በምድረ በዳም ሦስት ቀን ሄዱ፥ ውኃም አላገኙም።

Ver Capítulo Copiar




ዘፀአት 15:22
12 Referencias Cruzadas  

የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር መል​አ​ክም በውኃ ምንጭ አጠ​ገብ በሱር በረሃ በመ​ን​ገድ አገ​ኛት።


ሳኦ​ልም አማ​ሌ​ቃ​ው​ያ​ንን ከኤ​ው​ላጥ ጀምሮ በግ​ብፅ ፊት እስ​ካ​ለ​ችው እስከ ሱር ድረስ መታ​ቸው።


ይስ​ማ​ኤ​ልም የኖ​ረ​በት የዕ​ድ​ሜው ዘመን መቶ ሠላሳ ሰባት ዓመት ነው ፤ ሸም​ግሎ ሞተ፤ ወደ ወገ​ኖ​ቹም ተጨ​መረ።


እነ​ር​ሱም ቃል​ህን ይሰ​ማሉ፤ አን​ተና የእ​ስ​ራ​ኤል ሽማ​ግ​ሌ​ዎች ወደ ግብፅ ንጉሥ ትገ​ባ​ላ​ችሁ፦ የዕ​ብ​ራ​ው​ያን አም​ላክ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ጠር​ቶ​ናል፤ አሁ​ንም ለአ​ም​ላ​ካ​ችን ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እን​ሠዋ ዘንድ የሦ​ስት ቀን መን​ገድ ወደ ምድረ በዳ እን​ሄ​ዳ​ለን ትሉ​ታ​ላ​ችሁ።


አብ​ር​ሃ​ምም ከዚያ ተነ​ሥቶ ወደ አዜብ ምድር አቅ​ጣጫ ሄደ፤ በቃ​ዴ​ስና በሱር መካ​ከ​ልም ኖረ፤ በጌ​ራ​ራም በእ​ን​ግ​ድ​ነት ተቀ​መጠ።


ከኤ​ሮ​ትም ፊት ለፊት ተጕ​ዘው በባ​ሕሩ መካ​ከል ወደ ምድረ በዳ ተሻ​ገሩ፤ በኤ​ታ​ምም በረሃ የሦ​ስት ቀን መን​ገድ ሄደው በም​ረት ሰፈሩ።


ዳዊ​ትና ሰዎ​ቹም ወጥ​ተው በጌ​ሴ​ራ​ው​ያ​ንና በአ​ማ​ሌ​ቃ​ው​ያን ላይ አደጋ ጣሉ፤ እነ​ዚ​ህ​ንም ቅጽር ባላ​ቸው በጌ​ላ​ም​ሱ​ርና በአ​ኔ​ቆ​ን​ጦን እስከ ግብፅ ምድር ድረስ ተቀ​ም​ጠው አገ​ኙ​አ​ቸው።


ዓለ​ቱን ይመታ ዘንድ ውኃ​ንም ያፈስ ዘንድ ይች​ላ​ልን? እን​ጀ​ራን መስ​ጠ​ትና ለሕ​ዝ​ቡስ ማዕ​ድን መሥ​ራት ይች​ላ​ልን?”


የእ​ስ​ራ​ኤል ልጆች ማኅ​በር ሁሉ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እን​ዳ​ዘዘ ከሲን ምድረ በዳ ሊጓዙ ተነሡ፤ በራ​ፊ​ድም ሰፈሩ፤ በዚ​ያም ሕዝቡ የሚ​ጠ​ጡት ውኃ አል​ነ​በ​ረም።


Síguenos en:

Anuncios


Anuncios