ዘፀአት 15:14 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) አሕዛብ ሰሙ፤ ተቈጡም፤ በፍልስጥኤም የሚኖሩትን ምጥ ያዛቸው። አዲሱ መደበኛ ትርጒም አሕዛብ ይሰማሉ፤ ይንቀጠቀጡማል፤ የፍልስጥኤምን ሕዝብ ሥቃይ ይይዛቸዋል። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ሕዝቦች ሰሙ፥ ተንቀጠቀጡም፤ በፍልስጥኤም የሚኖሩትን ፍርሃት ያዛቸው። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም አሕዛብ ሁሉ ይህን ሰምተው በፍርሃት ተንቀጠቀጡ፤ ፍልስጥኤማውያንም ተሸበሩ፤ መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) አሕዛብ ሰሙ፥ ተንቀጠቀጡም፤ በፍልስጥኤም የሚኖሩትን ምጥ ያዛቸው። |
ፍልስጥኤም ሆይ፥ ከእባቡ ዘር እፉኝት ይወጣልና፥ ፍሬውም የሚበርርና እሳት የሚመስል እባብ ይሆናልና፥ የኀይላችሁ ቀንበር ተሰብሮአልና ሁላችሁም ደስ አይበላችሁ።
እናንተ የከተሞች በሮች ሆይ፥ ወዮ በሉ፤ እናንተም ከተሞች ሆይ፥ ደንግጡ፥ ጩኹም፤ ፍልስጥኤማውያን ሆይ፥ ሁላችሁም ቀልጣችኋል፤ ጢስ ከሰሜን ይወጣልና፥ እንግዲህም አትኖሩምና።
ቆመ፥ ምድርንም አወካት፣ ተመለከተ፥ አሕዛብንም አናወጠ፣ የዘላለምም ተራሮች ተቀጠቀጡ፥ የዘላለምም ኮረብቶች ቀለጡ፣ መንገዱ ከዘላለም ነው።
የዚያች ምድር ሰዎች፥ አንተ እግዚአብሔር በዚህ ሕዝብህ መካከል እንደ ሆንህ ሰምተዋል፤ አንተም፥ አቤቱ፥ ዐይን በዐይን እንደሚተያይ ተገልጠህላቸዋል። ደመናህም በላያቸው ቆመች። በቀንም በደመና ዐምድ ፥ በሌሊትም በእሳት ዐምድ በፊታቸው ትሄዳለህ።
በወንዙም አጠገብ ባለችው በሕዝቡ ልጆች ምድር በፋቱራ ወደ ተቀመጠው ወደ ቢዖር ልጅ ወደ በለዓም፥ “እነሆ፥ ከግብፅ የወጣ ሕዝብ አለ፤
ከሰማይ በታች ባሉ አሕዛብ ሁሉ ላይ ማስደንገጥህንና ማስፈራትህን እሰድድ ዘንድ ዛሬ እጀምራለሁ፤ ስምህን በሰሙ ጊዜ በፊትህ ይንቀጠቀጣሉ፤ ድንጋጤም ይይዛቸዋል።
ገባዖን ከመንግሥታት ከተሞች እንደ አንዲቱ ታላቅ ከተማ ስለሆነች፥ ከጋይም ስለ በለጠች፥ ሰዎችዋም ሁሉ ኀያላን ስለ ነበሩ እጅግ ፈራ።
ይህንም ነገር ሰምተን በልባችን ደነገጥን፤ አምላካችሁም እግዚአብሔር በላይ በሰማይ፥ በታችም በምድር እርሱ አምላክ ነውና ከእናንተ የተነሣ ከእኛ የአንዱም እንኳን ነፍስ አልቀረም።
መልሰውም ኢያሱን፥ “እኛ ባሪያዎችህ ምድሪቱን ሁሉ ይሰጣችሁ ዘንድ፥ በእርስዋም የሚኖሩትን ሁሉ ከፊታችሁ ያጠፋ ዘንድ አምላክህ እግዚአብሔር ባሪያውን ሙሴን እንዳዘዘ በእውነት ሰምተናል፤ ስለዚህም ከእናንተ የተነሣ ስለ ነፍሳችን እጅግ ፈራን፤ ይህንም ነገር አድርገናል፤
እነርሱም አሉት፥ “በአምላክህ በእግዚአብሔር ስም እጅግ ከራቀ ሀገር ባሪያዎችህ መጥተናል፤ ዝናውንም፥ በግብፃውያንም ያደረገውን ሁሉ፥
ፍልስጥኤማውያንም ፈርተው፥ “አማልክት ወደ እነርሱ ወደ ሰፈር መጥተዋል” አሉ። ደግሞም እንዲህ አሉ፥ “ወዮልን! አቤቱ፥ ዛሬ አድነን፤ ከዚህ አስቀድሞ እንዲህ ያለ ነገር አልሆነምና።
ወዮልን! ከእነዚህ ኀያላን አማልክት እጅ ማን ያድነናል? እነዚህ አማልክት ግብፃውያንን በምድረ በዳ በልዩ ልዩ መቅሠፍት የመቱ ናቸው።