መክብብ 7:7 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ግፍ ጠቢብን ያሳብደዋል፥ የልቡንም ትዕግሥት ያጠፋዋል። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ግፍ ጠቢብን ሞኝ ያደርጋል፤ ጕቦም ልብን ያበላሻል። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ግፍ ጠቢቡን ያሳብደዋል፥ ጉቦም ልቡን ያጠፋዋል። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ግፍን መፈጸም ጥበበኛን ሰው እንደ ሞኝ ያደርገዋል፤ ጉቦ መቀበልም መልካም ጠባይን ያበላሻል። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ግፍ ጠቢቡን ያሳብደዋል፥ ጉቦም ልቡን ያጠፋዋል። |
እኔም ተመለስሁ፥ ከፀሓይ በታችም የሚደረገውን ግፍ ሁሉ አየሁ፤ እነሆም፥ የተገፉት ሰዎች እንባ ነበረ፤ የሚያጽናናቸውም አልነበረም፤ በሚገፉአቸውም እጅ ኀይል ነበረ። እነርሱን ግን የሚያጽናናቸው አልነበረም።
ከፍ ካለው በላይ ከፍ ያለ ይጠብቅሃልና፥ ከእነርሱም በላይ ደግሞ ሌሎች ከፍ ይላሉና በሀገሩ ድሃ ሲበደል፥ ፍርድና ጽድቅም ሲነጠቅ ብታይ በሥራው አታድንቅ።
ይህን ሁሉ በአንድነት አየሁ፥ ከፀሓይም በታች ወደ ተደረገው ሥራ ሁሉ ልቤን ሰጠሁ፤ ሰውም ሰውን ለመጕዳት ገዥ የሚሆንበት ጊዜ አለ።
አለቆችሽ ዐመፀኞችና የሌቦች ባልንጀሮች ሆኑ፤ ሁሉ ጉቦ ይወድዳሉ፤ ፍርድንም ሊያጣምሙ ይፈልጋሉ፤ ለሙት ልጅ አይፈርዱም፤ የመበለቲቱንም አቤቱታ አያዳምጡም።
በጽድቅ የሚሄድ፥ ቅን ነገርንም የሚናገር፥ በደልንና ኀጢአትን የሚጠላ፥ መማለጃን ከመጨበጥ እጁን የሚያራግፍ፥ ደም ማፍሰስን ከመስማት ጆሮቹን የሚደፍን፥ ክፋትንም ከማየት ዐይኖቹን የሚጨፍን ነው።
ፍርድን አታጣምም፤ ፊት አይተህም አታድላ፤ ጉቦን አትቀበል፥ ጉቦ የጥበበኞችን ዐይን ያሳውራልና፥ የእውነትንም ቃል ያጣምማልና ጉቦ አትቀበል።
በእነዚያም አሕዛብ መካከል ዕረፍት አታገኝም፤ ለእግርህም ጫማ ማረፊያ አይሆንም፤ በዚያም እግዚአብሔር ተንቀጥቃጭ ልብ ፥ ፈዛዛ ዐይን፥ ደካማም ነፍስ ያመጣብሃል።
እነሆኝ፥ በእግዚአብሔርና እርሱ በቀባው ፊት መስክሩብኝ፤ የማንን በሬ ወሰድሁ? የማንንስ አህያ ወሰድሁ? ማንንስ ሸነገልሁ? በማንስ ላይ ግፍ አደረግሁ? ነጠላ ጫማ እንኳን ቢሆን ከማን እጅ መማለጃ ተቀበልሁ? መስክሩብኝ፤ እኔ እመልስላችኋለሁ።”