እግዚአብሔር አምላክም አለ፥ “ሰው ብቻውን ይኖር ዘንድ መልካም አይደለም፤ የሚረዳውን ጓደኛ እንፍጠርለት እንጂ።”
መክብብ 4:8 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) አንድ ሰው ብቻውን አለ፥ ሁለተኛም የለውም፥ ልጅም ሆነ ወንድም የለውም፤ ለድካሙ ግን መጨረሻ የለውም፥ ዐይኖቹም ከባለጠግነት አይጠግቡም። ለማን እደክማለሁ? ሰውነቴንስ ከደስታ ለምን እነፍጋታለሁ? ይላል። ይህም ደግሞ ከንቱ ነገር፥ ክፉም ጥረት ነው። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ልጅም ሆነ ወንድም የሌለው፣ ብቸኛ ሰው አለ፤ ጥረቱ ማለቂያ የለውም፤ ዐይኑም ባለው ሀብት ገና አልረካም፤ እርሱም፣ “ለማን ብዬ ነው የምደክመው? ራሴን ከማስደሰትስ የምቈጠበው ለምንድን ነው?” ብሎ ጠየቀ፤ ይህም ደግሞ ከንቱ፣ የጭንቅ ኑሮ ነው። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) አንድ ሰው ብቻውን ይኖራል፥ ማንም አብሮት የለም፥ ልጅም ሆነ ወንድም የለውም፥ ለድካሙም መጨረሻ የለውም፥ ዐይኖቹም ሳይቀሩ ሀብትን አይጠግቡም። እንግዲህ ለማን እደክማለሁ፥ ሰውነቴንስ መልካሙን ነገር ለምን እነፍጋታለሁ? ይላል። ይህም ደግሞ ከንቱ ነገር ክፉም ጥረት ነው። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም እነሆ፥ ብቻውን የሚኖር አንድ ሰው አለ፤ ልጅም ሆነ ወንድም የለውም፤ ይሁን እንጂ ዘወትር በሥራ ከመድከም አይቦዝንም፤ ባገኘውም ሀብት በቃኝ ማለትን አላወቀም፤ “እርሱም የምደክመው ለማን ነው? ለራሴስ ደስታን የምነፍገው ለምንድን ነው?” ብሎ ራሱን ይጠይቃል፤ ይህ ሁሉ የባሰ ከንቱና የሥቃይ ሕይወት ነው። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) አንድ ሰው ብቻውን አለ፥ ሁለተኛም የለውም፥ ልጅም ሆነ ወንድም የለውም፥ ለድካሙ ግን መጨረሻ የለውም፥ ዓይኖቹም ከባለጠግነት አይጠግቡም። ለማን እደክማለሁ፥ ሰውነቴንስ መልካሙን ነገር ለምን እነፍጋታለሁ? ይላል። ይህም ደግሞ ከንቱ ነገር ክፉም ጥረት ነው። |
እግዚአብሔር አምላክም አለ፥ “ሰው ብቻውን ይኖር ዘንድ መልካም አይደለም፤ የሚረዳውን ጓደኛ እንፍጠርለት እንጂ።”
መሥዋዕትንና ቍርባንን አልወደድሁም፤ ሥጋህን አንጻልኝ፤ የሚቃጠለውንና ስለ ኀጢአት የሚቀርበውን መሥዋዕት አልወደድሁም።
ከሰማይም በታች ስለተደረገው ሁሉ በጥበብ ለመመርመርና ለመፈተን ልቤን አተጋሁ፤ እግዚአብሔር ይደክሙበት ዘንድ ክፉ ድካምን ለሰው ልጆች ሰጥትዋልና።
ሰው በጥበብና በዕውቀት በብርታትም ከደከመ በኋላ ለሌላ ላልደከመበት ሰው ዕድሉን ያወርሳልና፤ ይህም ደግሞ ከንቱ ትልቅም መከራ ነው።
ከጎረቤቶቻቸው እርሻ ይወስዱ ዘንድ፥ ምድርንም ለብቻቸው ይይዟት ዘንድ፥ ቤትን ከቤት ጋር ለሚያያይዙ፥ እርሻንም ከእርሻ ጋር ለሚያቀራርቡ ወዮላቸው!
ገንዘብን እንጀራ ላይደለ፥ የድካማችሁንም ዋጋ ለማያጠግብ ነገር ለምን ትመዝናላችሁ? አድምጡኝ፤ በረከትንም ብሉ፤ ሰውነታችሁም በበረከት ደስ ይበለው።
እግዚአብሔርም፦ አንተ ሰነፍ! በዚች ሌሊት ነፍስህን ከሥጋህ ለይተው ይወስዷታል፤ እንግዲህ ያጠራቀምኸው ለማን ይሆናል? አለው።