Biblia Todo Logo
La Biblia Online

- Anuncios -




መክብብ 2:21 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

21 ሰው በጥ​በ​ብና በዕ​ው​ቀት በብ​ር​ታ​ትም ከደ​ከመ በኋላ ለሌላ ላል​ደ​ከ​መ​በት ሰው ዕድ​ሉን ያወ​ር​ሳ​ልና፤ ይህም ደግሞ ከንቱ ትል​ቅም መከራ ነው።

Ver Capítulo Copiar

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

21 ምክንያቱም ሰው ሥራውን በጥበብ፣ በዕውቀትና በብልኀት ሠርቶ፣ ከዚያ ያለውን ሁሉ ለሌላ ላልለፋበት ሰው ይተውለታል። ይህም ደግሞ ከንቱና ትልቅ ጕዳት ነው።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

21 ሰው በጥበብና በእውቀት በብልሃትም ከደከመ በኋላ ለሌላ ላልደከመበት ሰው ያወርሰዋልና፥ ይህም ደግሞ ከንቱ ትልቅም ጉዳት ነው።

Ver Capítulo Copiar

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

21 ባለህ ጥበብ፥ በቀሰምከውም ዕውቀትና ብልኀት የለፋህበትን ሁሉ ምንም ላልደከመበት ሰው ትተህለት ታልፋለህ፤ ይህም ከንቱ ስለ ሆነ ታላቅ መከራ ነው።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

21 ሰው በጥበብና በእውቀት በብልሃትም ከደከመ በኋላ ለሌላ ላልደከመበት ሰው ያወርሰዋልና፥ ይህም ደግሞ ከንቱ ትልቅም መከራ ነው።

Ver Capítulo Copiar




መክብብ 2:21
15 Referencias Cruzadas  

እነሆ ዐይ​ን​ህና ልብህ መል​ካም አይ​ደ​ለም፤ ነገር ግን ለቅ​ሚያ፥ ንጹሕ ደም​ንም ለማ​ፍ​ሰስ፥ ግድ​ያ​ንና ግፍ​ንም ለመ​ሥ​ራት ብቻ ነው።”


በአ​ባ​ትህ ዝግባ አዳ​ራሽ ስለ ሠራህ በውኑ ትነ​ግ​ሣ​ለ​ህን? በውኑ አባ​ትህ አይ​በ​ላና አይ​ጠ​ጣም ነበ​ርን? ፍር​ድ​ንና ጽድ​ቅ​ንስ አያ​ደ​ር​ግም ነበ​ርን? በዚ​ያም ጊዜ መል​ካም ሆኖ​ለት ነበር።


ከጦር መሣ​ሪ​ያ​ዎች ይልቅ ጥበብ ትሻ​ላ​ለች፤ አንድ ኀጢ​አ​ተኛ ግን ብዙ መል​ካ​ምን ያጠ​ፋል።


ከነ​ቢ​ዩም ከሳ​ሙ​ኤል ዘመን ጀምሮ እን​ደ​ዚህ ያለ ፋሲካ በእ​ስ​ራ​ኤል ዘንድ ከቶ አል​ተ​ደ​ረ​ገም፤ ከእ​ስ​ራ​ኤ​ልም ነገ​ሥ​ታት ሁሉ ኢዮ​ስ​ያ​ስና ካህ​ናቱ፥ ሌዋ​ው​ያ​ኑም፥ በዚ​ያም የተ​ገኙ የይ​ሁ​ዳና የእ​ስ​ራ​ኤል ሰዎች ሁሉ፥ በኢ​የ​ሩ​ሳ​ሌ​ምም የሚ​ኖ​ሩት እን​ዳ​ደ​ረ​ጉት ያለ ፋሲካ ያደ​ረገ የለም።


በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ፊት ቅን ነገር አደ​ረገ፤ በአ​ባ​ቱም በዳ​ዊት መን​ገድ ሄደ፤ ወደ ቀኝም ወደ ግራም አላ​ለም።


የዱር አራ​ዊት ሁሉ፥ የም​ድረ በዳ እን​ስ​ሶ​ችና ላሞች ሁሉ የእኔ ናቸ​ውና።


እኔም ተመ​ልሼ ልቤን ከፀ​ሐይ በታች በደ​ከ​ም​ሁ​በት ድካም ሁሉ ተስፋ አስ​ቈ​ረ​ጥ​ሁት።


እኔ ድካ​ምን ሁሉና የብ​ል​ሃት ሥራ​ውን ተመ​ለ​ከ​ትሁ፥ ለሰ​ውም በባ​ል​ን​ጀ​ራው ዘንድ ቅን​አ​ትን እን​ዲ​ያ​ስ​ነሣ አየሁ፤ ይህም ደግሞ ከንቱ ነፋ​ስ​ንም እንደ መከ​ተል ነው።


አንድ ሰው ብቻ​ውን አለ፥ ሁለ​ተ​ኛም የለ​ውም፥ ልጅም ሆነ ወን​ድም የለ​ውም፤ ለድ​ካሙ ግን መጨ​ረሻ የለ​ውም፥ ዐይ​ኖ​ቹም ከባ​ለ​ጠ​ግ​ነት አይ​ጠ​ግ​ቡም። ለማን እደ​ክ​ማ​ለሁ? ሰው​ነ​ቴ​ንስ ከደ​ስታ ለምን እነ​ፍ​ጋ​ታ​ለሁ? ይላል። ይህም ደግሞ ከንቱ ነገር፥ ክፉም ጥረት ነው።


በዚ​ያን ጊዜ አልሁ፥ “እነሆ፥ መጣሁ፤ ስለ እኔ በመ​ጽ​ሐፍ ራስ ተጽ​ፎ​አል፤


የሰ​ማ​ይን አዕ​ዋፍ ሁሉ አው​ቃ​ለሁ፥ የዱር ውበ​ትም በእኔ ዘንድ አለ።


Síguenos en:

Anuncios


Anuncios