Biblia Todo Logo
La Biblia Online

- Anuncios -




መክብብ 2:23 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

23 ዘመኑ ሁሉ መከራ፥ ቍጣም፥ ቅሚ​ያም ነው፤ ልቡም በሌ​ሊት አይ​ተ​ኛም፥ ይህም ደግሞ ከንቱ ነው።

Ver Capítulo Copiar

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

23 በዘመኑ ሁሉ ሥራው ሥቃይና ሐዘን ነው፤ በሌሊትም እንኳ ቢሆን አእምሮው አያርፍም። ይህም ደግሞ ከንቱ ነው።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

23 ዘመኑ ሁሉ ስቃይ፥ ጥረትም ትካዜ ነው፥ ልቡም በሌሊት አያርፍም፥ ይህም ደግሞ ከንቱ ነው።

Ver Capítulo Copiar

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

23 በሕይወቱ ዘመን የሚሠራው ነገር ሁሉ ከሐዘንና ከትካዜ በቀር የሚያተርፍለት ምንም ዐይነት ጥቅም የለም፤ ሌሊት እንኳ አእምሮው ዕረፍት አያገኝም፤ ይህም ሁሉ ከንቱ ነው።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

23 ዘመኑ ሁሉ ኀዘን፥ ጥረትም ትካዜ ነው፥ ልቡም በሌሊት አይተኛም፥ ይህም ደግሞ ከንቱ ነው።

Ver Capítulo Copiar




መክብብ 2:23
20 Referencias Cruzadas  

“ከሴት የተ​ወ​ለደ ሟች ሰው የሕ​ይ​ወቱ ዘመን ጥቂት ነው፥ የቍጣ መከ​ራ​ንም የተ​ሞላ ነው።


የአ​ሞራ ግል​ገ​ሎች ግን ወደ ላይ እየ​በ​ረሩ ከፍ እን​ዲሉ፥ ሰው እን​ዲሁ ለድ​ካም ተወ​ል​ዶ​አል።


የድ​ካ​ም​ህን ፍሬ ትመ​ገ​ባ​ለህ፤ ብፁዕ ነህ፥ መል​ካ​ምም ይሆ​ን​ል​ሃል።


የደቀ መዛ​ሙ​ር​ት​ንም ልቡና አጽ​ናኑ፤ በሃ​ይ​ማ​ኖ​ትም እን​ዲ​ጸኑ፦“ በብዙ ድካ​ምና መከራ ወደ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር መን​ግ​ሥት እን​ገባ ዘንድ ይገ​ባ​ናል” እያሉ መከ​ሩ​አ​ቸው።


ብዙ ወይም ጥቂት ቢበላ የአ​ገ​ል​ጋይ እን​ቅ​ልፉ ጣፋጭ ነው፤ ብል​ጽ​ግ​ናን ያበዛ ሰውን ግን ይተኛ ዘንድ የሚ​ተ​ወው የለም።


በጥ​በብ መብ​ዛት ትካዜ ይበ​ዛ​ልና፤ ዕው​ቀ​ት​ንም የሚ​ያ​በዛ መከ​ራን ያበ​ዛ​ልና።


ይጠ​ራ​ኛል እመ​ል​ስ​ለ​ት​ማ​ለሁ፥ በመ​ከ​ራ​ውም ጊዜ ከእ​ርሱ ጋር እሆ​ና​ለሁ፤ አድ​ነ​ዋ​ለሁ አከ​ብ​ረ​ው​ማ​ለሁ።


የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ቃል እው​ነት ነውና ሥራ​ውም ሁሉ በእ​ም​ነት ነውና።


ያዕ​ቆ​ብም ለፈ​ር​ዖን አለው፥ “በእ​ን​ግ​ድ​ነት የኖ​ር​ሁት የሕ​ይ​ወቴ ዘመ​ንስ መቶ ሠላሳ ዓመት ነው፤ የሕ​ይ​ወ​ቴም ዘመ​ኖች ጥቂ​ትም ክፉም ሆኑ​ብኝ፤ አባ​ቶች በእ​ን​ግ​ድ​ነት የተ​ቀ​መ​ጡ​በ​ት​ንም ዘመን አያ​ህ​ሉም።”


እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም አዳ​ምን አለው፥ “የሚ​ስ​ት​ህን ቃል ሰም​ተ​ሃ​ልና፥ ከእ​ርሱ እን​ዳ​ት​በላ ከአ​ዘ​ዝ​ሁህ ከዚያ ዛፍም በል​ተ​ሃ​ልና ምድር በሥ​ራህ የተ​ረ​ገ​መች ትሁን፤ በሕ​ይ​ወት ዘመ​ን​ህም ሁሉ በድ​ካም ከእ​ር​ስዋ ትበ​ላ​ለህ፤


ከሰ​ማ​ይም በታች ስለ​ተ​ደ​ረ​ገው ሁሉ በጥ​በብ ለመ​መ​ር​መ​ርና ለመ​ፈ​ተን ልቤን አተ​ጋሁ፤ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ይደ​ክ​ሙ​በት ዘንድ ክፉ ድካ​ምን ለሰው ልጆች ሰጥ​ት​ዋ​ልና።


እጄ የሠ​ራ​ቻ​ትን ሥራ​ዬን ሁሉ፥ የደ​ከ​ም​ሁ​በ​ት​ንም ድካ​ሜን ሁሉ ተመ​ለ​ከ​ትሁ፤ እነሆ፥ ሁሉ ከንቱ፥ ነፋ​ስ​ንም እንደ መከ​ተል ነበረ፥ ከፀ​ሐይ በታ​ችም ትርፍ አል​ነ​በ​ረም።


ዘመኑ ሁሉ በጨ​ለማ በል​ቅ​ሶና በብዙ ብስ​ጭት በደ​ዌና በኀ​ዘን ነውና።


ጥበ​ብን አውቅ ዘንድ በም​ድር የሚ​ሆ​ነ​ው​ንም ድካም አይ ዘንድ ልቤን ሰጠሁ፥ በቀ​ንና በሌ​ሊት እን​ቅ​ል​ፍን በዐ​ይኑ የሚ​ያይ የለ​ምና።


Síguenos en:

Anuncios


Anuncios