መክብብ 3:7 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ለመቅደድ ጊዜ አለው፥ ለመስፋትም ጊዜ አለው፤ ዝም ለማለት ጊዜ አለው፥ ለመናገርም ጊዜ አለው፤ አዲሱ መደበኛ ትርጒም ለመቅደድ ጊዜ አለው፤ ለመስፋትም ጊዜ አለው፤ ለዝምታ ጊዜ አለው፤ ለመናገርም ጊዜ አለው፤ መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ለመቅደድ ጊዜ አለው፥ ለመስፋትም ጊዜ አለው፥ ዝም ለማለት ጊዜ አለው፥ ለመናገርም ጊዜ አለው፥ አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ለመቅደድ ጊዜ አለው፤ ለመስፋትም ጊዜ አለው፤ ለዝምታ ጊዜ አለው፤ ለንግግርም ጊዜ አለው። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ለመቅደድ ጊዜ አለው፥ ለመስፋትም ጊዜ አለው፥ ዝም ለማለት ጊዜ አለው፥ ለመናገርም ጊዜ አለው፥ |
ይሁዳም ወደ እርሱ ቀረበ፤ እንዲህም አለ፥ “ጌታዬ ሆይ፥ እኔ አገልጋይህ በፊትህ አንዲት ቃልን እንድናገር እለምናለሁ፤ እኔን አገልጋይህን አትቈጣኝ፤ አንተ ከፈርዖን ቀጥለህ ነህና።
አለዚያም ብላቴናው ከእኛ ጋር ከሌለ እኔ ወደ አባታችን እንዴት እሄዳለሁ? አባታችንን የሚያገኘውን መከራ እንዳላይ።”
ዳዊትም ኢዮአብንና ከእርሱ ጋር የነበሩትን ሕዝብ ሁሉ፥ “ልብሳችሁን ቅደዱ፤ ማቅም ልበሱ፤ በአበኔርም ፊት አልቅሱ” አላቸው። ንጉሡም ዳዊት ከቃሬዛው በኋላ ሄደ።
የእስራኤልም ልጆች ተቈጠሩ፤ ሊገጥሙአቸውም ወጡ፤ የእስራኤልም ልጆች እንደ ሁለት ትናንሽ የፍየል መንጋዎች ሆነው በፊታቸው ሰፈሩ፤ ሶርያውያን ግን ምድርን ሞልተዋት ነበር።
የእስራኤልም ንጉሥ ደብዳቤውን ባነበበ ጊዜ ልብሱን ቀድዶ፥ “ሰውን ከለምጹ እፈውስ ዘንድ ይህ ሰው ወደ እኔ መስደዱ እኔ በውኑ ለመግደልና ለማዳን የምችል አምላክ ነኝን? ተመልከቱ፥ የጠብ ምክንያት እንደሚፈልግብኝ ተመልከቱ” አለ።
የእስራኤልም ንጉሥ የሴቲቱን ቃል ሰምቶ ልብሱን ቀደደ፤ በቅጥርም ይመላለስ ነበር፤ ሕዝቡም በስተውስጥ በሥጋው ላይ ለብሶት የነበረውን ማቅ አዩ።
ሰባት ቀንና ሰባት ሌሊትም በአጠገቡ ተቀመጡ፤ ሕማሙ እጅግ አስፈሪና ታላቅ እንደ ነበረ አይተዋልና ከእነርሱ አንድ ቃል የሚናገረው አልነበረም።
“ዝም ብለን ለምን እንቀመጣለን? እግዚአብሔርን ስለ በደልን አምላካችን እግዚአብሔር አጥፍቶናልና፥ የሐሞትንም ውኃ አጠጥቶናልና ተሰብስባችሁ ወደ ተመሸጉ ከተሞች እንግባ በዚያም እንጥፋ።
ልባችሁን እንጂ ልብሳችሁን አትቅደዱ፤ አምላካችሁም እግዚአብሔር መሓሪና ይቅር ባይ፥ ቍጣው የዘገየ ምሕረቱም የበዛ፥ ለክፋትም የተጸጸተ ነውና ወደ እርሱ ተመለሱ።”
ያንጊዜም በመቅደሶቻቸው ዋይ ዋይ ይላሉ” ይላል ጌታ እግዚአብሔር፤ በየስፍራው የሚወድቀው ሬሳ ይበዛልና፤ እነርሱም ይጠፋሉና።
ጴጥሮስም ተነሥቶ አብሮአቸው ሄደ፤ በደረሰም ጊዜ ወደ ሰገነት አወጡት፤ ባልቴቶችም ሁሉ ወደ እርሱ መጥተው በፊቱ ቆሙ፤ ያለቅሱላትም ነበር፤ ዶርቃስም በሕይወት ሳለች የሠራችውን ቀሚሱንና መጐናጸፊያውን አሳዩት።