Biblia Todo Logo
La Biblia Online

- Anuncios -




1 ነገሥት 21:27 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

27 የእ​ስ​ራ​ኤ​ልም ልጆች ተቈ​ጠሩ፤ ሊገ​ጥ​ሙ​አ​ቸ​ውም ወጡ፤ የእ​ስ​ራ​ኤ​ልም ልጆች እንደ ሁለት ትና​ንሽ የፍ​የል መን​ጋ​ዎች ሆነው በፊ​ታ​ቸው ሰፈሩ፤ ሶር​ያ​ው​ያን ግን ምድ​ርን ሞል​ተ​ዋት ነበር።

Ver Capítulo Copiar

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

27 አክዓብም ይህን ቃል ሲሰማ ልብሱን ቀደደ፤ ማቅ ለብሶ፤ ጾመ፤ በማቅ ላይ ተኛ በሐዘን ኵርምት ብሎም ይሄድ ነበር።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

27 የእስራኤልም ልጆች ተሰለፉ፥ ሊገጥሙአቸውም ወጡ፥ የእስራኤልም ልጆች እንደ ሁለት ትናንሾች የፍየል መንጋዎች ሆነው በፊታቸው ሰፈሩ፥ ሶርያውያን ግን ምድሩን ሞልተው ነበር።

Ver Capítulo Copiar

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

27 ኤልያስ ንግግሩን ከፈጸመ በኋላ አክዓብ ልብሱን በመቅደድና አውልቆ በመጣል ማቅ ለበሰ፤ እህል መቅመስንም እምቢ አለ፤ ማቁንም እንደ ለበሰ ይተኛ ነበር፤ ሲሄድም ከጭንቀቱ ብዛት የተነሣ ፊቱ ጠቊሮ ይታይ ነበር።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

27 የእስራኤልም ልጆች ተሰለፉ፥ ሊገጥሙአቸውም ወጡ፤ የእስራኤልም ልጆች እንደ ሁለት ትናንሾች የፍየል መንጋዎች ሆነው በፊታቸው ሰፈሩ፤ ሶርያውያን ግን ምድሩን ሞልተው ነበር።

Ver Capítulo Copiar




1 ነገሥት 21:27
18 Referencias Cruzadas  

የእ​ስ​ራ​ኤ​ልም ንጉሥ የሴ​ቲ​ቱን ቃል ሰምቶ ልብ​ሱን ቀደደ፤ በቅ​ጥ​ርም ይመ​ላ​ለስ ነበር፤ ሕዝ​ቡም በስ​ተ​ው​ስጥ በሥ​ጋው ላይ ለብ​ሶት የነ​በ​ረ​ውን ማቅ አዩ።


ያዕ​ቆ​ብም ልብ​ሱን ቀደደ፤ በወ​ገ​ቡም ማቅ ታጥቆ ለልጁ ብዙ ቀን አለ​ቀሰ።


ዳዊ​ትም ኢዮ​አ​ብ​ንና ከእ​ርሱ ጋር የነ​በ​ሩ​ትን ሕዝብ ሁሉ፥ “ልብ​ሳ​ች​ሁን ቅደዱ፤ ማቅም ልበሱ፤ በአ​በ​ኔ​ርም ፊት አል​ቅሱ” አላ​ቸው። ንጉ​ሡም ዳዊት ከቃ​ሬ​ዛው በኋላ ሄደ።


መሥ​ዋ​ዕ​ቱና የመ​ጠጡ ቍር​ባን ከአ​ም​ላ​ካ​ችሁ ቤት ቀር​ቶ​አ​ልና እና​ንተ ካህ​ናት! ማቅ ታጥ​ቃ​ችሁ አል​ቅሱ፤ እና​ን​ተም የመ​ሠ​ውያ አገ​ል​ጋ​ዮች! ዋይ በሉ፤ እና​ን​ተም የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር አገ​ል​ጋ​ዮች ኑና በማቅ ላይ ተኙ።


ዐይ​ኖች ደከሙ፤ ወደ ሰማ​ይም ወደ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ማየት አል​ቻ​ል​ሁም። ጌታ ሆይ፦ ይቅር በለኝ፤ የሰ​ው​ነ​ቴ​ንም መከራ አር​ቅ​ልኝ።


በዚ​ያም ቀን የሠ​ራ​ዊት ጌታ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ልቅ​ሶ​ንና ዋይ​ታን፥ ራስን መን​ጨ​ት​ንና ማቅን መል​በ​ስን ጠራ።


በው​ድ​ቀት ላይ ውድ​ቀ​ትን አደ​ረ​ሱ​ብኝ፤ ኀያ​ላኑ እየ​ሠ​ገጉ ሮጡ​ብኝ።


የቤቱ አዛዥ የኬ​ል​ቅዩ ልጅ ኤል​ያ​ቄም፥ ጸሓ​ፊው ሳም​ናስ፥ ታሪክ ጸሓ​ፊ​ውም የአ​ሳፍ ልጅ ዮአስ ልብ​ሳ​ቸ​ውን ቀድ​ደው ወደ ሕዝ​ቅ​ያስ ገቡ፥ የራ​ፋ​ስ​ቂ​ስ​ንም ቃል ነገ​ሩት።


ወሬ​ውም ወደ ነነዌ ንጉሥ ደረሰ፤ እር​ሱም ከዙ​ፋኑ ተነ​ሥቶ መጐ​ና​ጸ​ፊ​ያ​ውን አወ​ለቀ፤ ማቅም ለበሰ፤ በአ​መ​ድም ላይ ተቀ​መጠ።


ለሁለቱም ምስክሮቼ ማቅ ለብሰው ሺህ ከሁለት መቶ ስድሳ ቀን ትንቢት ሊናገሩ እሰጣለሁ።”


የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ሰው መጥቶ የእ​ስ​ራ​ኤ​ልን ንጉሥ፥ “እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እን​ዲህ ይላል፦ ሶር​ያ​ው​ያን፦ የእ​ስ​ራ​ኤል አም​ላክ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር የተ​ራ​ሮች አም​ላክ ነው እንጂ የሸ​ለቆ አም​ላክ አይ​ደ​ለም ብለ​ዋ​ልና ይህን ታላቅ ሠራ​ዊት ሁሉ በእ​ጅህ አሳ​ልፌ እሰ​ጠ​ዋ​ለሁ፤ እኔም እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እንደ ሆንሁ ታው​ቃ​ለህ” አለው።


ንጉ​ሡም ሕዝ​ቅ​ያስ ይህን በሰማ ጊዜ ልብ​ሱን ቀደደ፥ ማቅም ለበሰ፥ ወደ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ቤት ገባ።


ዳዊ​ትም ዐይ​ኖ​ቹን አነሣ፤ የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም መል​አክ በም​ድ​ርና በሰ​ማይ መካ​ከል ቆሞ፥ የተ​መ​ዘ​ዘም ሰይፍ በእጁ ሆኖ ወደ ኢየ​ሩ​ሳ​ሌም ተዘ​ር​ግቶ አየ። ዳዊ​ትና ሽማ​ግ​ሌ​ዎ​ቹም ማቅ ለብ​ሰው በግ​ን​ባ​ራ​ቸው ተደፉ።


ንጉ​ሡም፥ ይህ​ንም ቃል ሁሉ የሰሙ አገ​ል​ጋ​ዮቹ ሁሉ አል​ደ​ነ​ገ​ጡም፤ ልብ​ሳ​ቸ​ው​ንም አል​ቀ​ደ​ዱም።


እግዚአብሔርም ከክፉ መንገዳቸው እንደተመለሱ ሥራቸውን አየ፤ እግዚአብሔርም ያደርግባቸው ዘንድ ከተናገረው ክፉ ነገር ተመለሰ፤ አላደረገውምም።


ሕዝ​ቡም ይህን ክፉ ወሬ ሰም​ተው ታላቅ ኀዘን አዘኑ፤


Síguenos en:

Anuncios


Anuncios