ከፊቱ አውጥቶ እስኪጥላቸው ድረስ ይህ ነገር በእግዚአብሔር ቍጣ በኢየሩሳሌምና በይሁዳ ላይ ሆኖአልና፤ ሴዴቅያስም በባቢሎን ንጉሥ ላይ ዐመፀ።
ዘዳግም 4:24 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) አምላክህ እግዚአብሔር የሚበላ እሳት፥ ቀናተኛም አምላክ ነውና። አዲሱ መደበኛ ትርጒም አምላካችሁ እግዚአብሔር የሚባላ እሳት፣ ቀናተኛም አምላክ ነውና። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ጌታ እግዚአብሔር የሚበላ እሳት፥ ቀናተኛ አምላክ ነውና። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም አምላካችሁ እግዚአብሔር የሚባላ እሳት ነው፤ ቀናተኛ አምላክ ነው። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) አምላክህ እግዚአብሔር የሚበላ እሳት ቀናተኛም አምላክ ነውና። |
ከፊቱ አውጥቶ እስኪጥላቸው ድረስ ይህ ነገር በእግዚአብሔር ቍጣ በኢየሩሳሌምና በይሁዳ ላይ ሆኖአልና፤ ሴዴቅያስም በባቢሎን ንጉሥ ላይ ዐመፀ።
አትስገድላቸው፤ አታምልካቸውም፤ እኔ እግዚአብሔር አምላክህ ቀናተኛ አምላክ ነኝና። በሚጠሉኝ እስከ ሦስተኛና አራተኛ ትውልድ ድረስ የአባቶችን ኀጢአት በልጆች ላይ የማመጣ፤
ወተትና ማርም ወደምታፈስሰው ምድር አስገባሃለሁ፤ አንገተ ደንዳና ስለሆኑ ሕዝብህ በመንገድ ላይ እንዳላጠፋህ እኔ ከአንተ ጋር አልወጣም።”
እነሆ፥ የእግዚአብሔር ስም ከብዙ ጊዜ በኋላ ይመጣል፤ ቍጣውም ከከንፈሮቹ ቃል ክብር ጋር ይነድዳል፤ ቃሉም ቍጣን የተመላ ነው፤ የቍጣውም መቅሠፍት እንደምትበላ እሳት ናት፤
ከቀድሞም ጀምሮ የማቃጠያ ስፍራ ተዘጋጅታለች፤ ለንጉሥም ተበጅታለች፤ ጥልቅና ሰፊም አድርጎአታል፤ እሳትና ብዙ ማገዶ ተከምሮአል፤ የእግዚአብሔርም ቍጣ እንደ ዲን ፈሳሽ ያቃጥለዋል።
በጽዮን ያሉ ኀጢአተኞች ፈሩ፤ መንቀጥቀጥ ዝንጉዎችን ያዘ፤ እሳት እንደሚነድድ የሚነግራችሁ ማን ነው? የዘለዓለም ሀገርንስ የሚነግራችሁ ማን ነው?
በዮሴፍ ቤት እሳት እንዳትቃጠል፥ እንዳትበላቸውም የእስራኤልንም ቤት እሳት የሚያጠፋላቸው እንዳያጡ እግዚአብሔርን ፈልጉ፤ በሕይወትም ትኖራላችሁ።
እግዚአብሔር ቀናተኛና ተበቃይ አምላክ ነው፣ እግዚአብሔር ተበቃይና መዓትን የተሞላ ነው፣ እግዚአብሔር ተቃዋሚዎቹን ይበቀላል፥ ለጠላቶቹም ቍጣውን ይጠብቃል።
በእግዚአብሔርም ቍጣ ቀን ብራቸውና ወርቃቸው ሊያድናቸው አይችልም፣ እርሱም በምድር የሚኖሩትን ሁሉ ፈጥኖ ይጨርሳቸዋልና ምድር ሁሉ በቅንዓቱ እሳት ትበላለች።
መዓቴንና የቍጣዬን ትኵሳት ሁሉ አፈስስባቸው ዘንድ ፍርዴ አሕዛብን ለመሰብሰብ፥ መንግሥታትንም ለማከማቸት ነውና፥ ምድርም ሁሉ በቅንዓቴ እሳት ትበላለችና ስለዚህ ለመበዝበዝ እስከምነሣበት ቀን ድረስ ጠብቁኝ፥ ይላል እግዚአብሔር።
“የካህኑ የአሮን ልጅ የአልዓዛር ልጅ ፊንሐስ በቅንዓቴ በመካከላቸው ቀንቶአልና ቍጣዬን ከእስራኤል ልጆች መለሰ፤ እኔም የእስራኤልን ልጆች በቅንዓቴ አላጠፋሁም።
የእግዚአብሔር ቍጣ፥ ቅንአቱም በዚያ ሰው ላይ ይነድዳል እንጂ እግዚአብሔር ይቅርታ አያደርግለትም፤ በዚህም መጽሐፍ የተጻፈው ርግማን ሁሉ በላዩ ይኖራል፤ እግዚአብሔርም ስሙን ከሰማይ በታች ይደመስሰዋል።
አትስገድላቸው፤ አታምልካቸውም፤ እኔ እግዚአብሔር አምላክህ ቀናተኛ አምላክ ነኝና፤ በሚጠሉኝ እስከ ሦስተኛና እስከ አራተኛ ትውልድ ድረስ የአባቶችን ኀጢአት በልጆች ላይ የማመጣ፤
በመካከልህ ያለው አምላክህ እግዚአብሔር ቀናተኛ አምላክ ነውና የአምላክህ የእግዚአብሔር ቁጣ እንዳይነድድብህ፥ ከምድርም ፊት እንዳያጠፋህ ተጠንቀቅ።
አምላክህም እግዚአብሔር በፊትህ እንዲያልፍ ዛሬ ዕወቅ፤ እርሱ የሚበላ እሳት ነው፤ እርሱ ያጠፋቸዋል፤ በፊትህም ያዋርዳቸዋል፤ እግዚአብሔርም እንደ ነገረህ ከፊትህ ያርቃቸዋል፥ ፈጥኖም ያጠፋቸዋል።