“ትወርሱአት ዘንድ እኔ ወደምሰጣችሁ ርስት ወደ ከነዓን ምድር በገባችሁ ጊዜ፥ እኔም የለምጽ ደዌ ምልክት በርስታችሁ ምድር ቤቶች ባደረግሁ ጊዜ፥
ዘዳግም 17:14 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) “አምላክህ እግዚአብሔር ርስት አድርጎ ወደሚሰጥህ ምድር በገባህ፥ በወረስሃትም ጊዜ፥ በተቀመጥህባትም ጊዜ፦ በዙሪያዬ እንዳሉት አሕዛብ ሁሉ በላዬ አለቃ እሾማለሁ ብትል፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም አምላክህ እግዚአብሔር ወደሚሰጥህ ምድር ስትገባ፣ በምትወርሳትና በምትቀመጥባት ምድር፣ “በዙሪያዬ እንዳሉት አሕዛብ ሁሉ፣ እኔም በላዬ ንጉሥ ላንግሥ” ብትል፣ መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) “አምላክህ ጌታ ወደሚሰጥህ ምድር ስትገባ፥ በምትወርሳትና በምትቀመጥባት ምድር፥ ‘በዙሪያዬ እንዳሉት አሕዛብ ሁሉ፥ እኔም በላዬ ንጉሥ ላንግሥ’ ብትል፥ አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም “እግዚአብሔር አምላክህ ወደሚሰጥህ ምድር በመግባት ምድሩን ወርሰህ ከተደላደልክ በኋላ በዙሪያዬ እንዳሉት ሕዝቦች ንጉሥ ላንግሥ ብትል፥ መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) አምላክህ እግዚአብሔር ወደሚሰጥህ ምድር በገባህ፥ በወረስሃትም ጊዜ፥ በተቀመጥህባትም ጊዜ፦ በዙሪያዬ እንዳሉት አሕዛብ ሁሉ በላዬ ንጉሥ አነግሣለሁ ስትል፥ |
“ትወርሱአት ዘንድ እኔ ወደምሰጣችሁ ርስት ወደ ከነዓን ምድር በገባችሁ ጊዜ፥ እኔም የለምጽ ደዌ ምልክት በርስታችሁ ምድር ቤቶች ባደረግሁ ጊዜ፥
አምላካችሁ እግዚአብሔር በዕጣችሁ ለሁልጊዜ የሚሰጣችሁን ምድር ትገቡና ትወርሱ ዘንድ ዮርዳኖስን ትሻገራላችሁ፤ ትወርሱአታላችሁም፤ ትቀመጡባታላችሁም።
“አምላክህ እግዚአብሔር ወደሚሰጥህ ምድር በገባህ ጊዜ እነዚያ አሕዛብ የሚያደርጉትን ርኵሰት ታደርግ ዘንድ አትማር።
“አምላክህ እግዚአብሔር ልትወርሳት ወደምትገባባት ምድር ባመጣህ ጊዜ፥ ከፊትህም ብዙና ታላላቅ አሕዛብን፥ ከአንተ የበለጡትን፥ የበረቱትንም ሰባቱን አሕዛብ፥ ኬጤዎናዊውን፥ ጌርጌሴዎናዊውንም፥ አሞሬዎናዊውንም፥ ከነዓናዊውንም፥ ፌርዜዎናዊውንም፥ ኤዌዎናዊውንም፥ ኢያቡሴዎናዊውንም ባወጣ ጊዜ፥
“የእግዚአብሔር አገልጋይ ሙሴ እንዲህ ብሎ ያዘዛችሁን ቃል አስቡ፦ አምላካችሁ እግዚአብሔር ያሳርፋችኋል፤ ይህችንም ምድር ይሰጣችኋል።
እግዚአብሔርም ይሰጣቸው ዘንድ ለአባቶቻቸው የማለላቸውን ምድር ሁሉ ለእስራኤል ሰጠ፤ ወረሱአትም፥ ተቀመጡባትም።
ዛሬ ግን ከመከራችሁና ከጭንቃችሁ ሁሉ ያዳናችሁን እግዚአብሔርን ንቃችሁ፦ ‘እንዲህ አይሁን፤ ነገር ግን ንጉሥ አንግሥልን’ አላችሁት። አሁንም በየነገዳችሁና በየወገናችሁ በእግዚአብሔር ፊት ቁሙ” አላቸው።
ሳሙኤልም የንጉሡን ሥርዐት ነገራቸው፤ በመጽሐፍም ጻፈው፤ በእግዚአብሔርም ፊት አኖረው። ሳሙኤልም ሕዝቡን ሁሉ ወደ እየቤታቸው አሰናበታቸው። ሕዝቡም ሁሉ ወደ እየቤታቸው ሄዱ።
ሕዝቡም ሁሉ ሳሙኤልን፥ “ንጉሥ በመለመናችን በኀጢአታችን ሁሉ ላይ ይህን ክፋት ጨምረናልና እንዳንሞት ስለ ባሪያዎችህ ወደ አምላክህ ወደ እግዚአብሔር ጸልይልን” አሉት።
እንዲህም አለ፥ “በእናንተ ላይ የሚነግሠው የንጉሡ ሥርዐት ይህ ነው፤ ወንዶች ልጆቻችሁን ወስዶ ሰረገላ ነጂዎችና ፈረሰኞች ያደርጋቸዋል፤ በሰረገሎችም ፊት ይሮጣሉ፤