የስደተኞቹም ልጆች እንዲህ አደረጉ፤ ካህኑ ዕዝራ፥ የአባቶችም ቤቶች አለቆች በየአባቶቻቸው ቤቶች ሁሉም በየስማቸው ተለዩ፤ በዐሥረኛውም ወር በመጀመሪያው ቀን ነገሩን ይመረምሩ ዘንድ ተቀመጡ።
ዘዳግም 13:15 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) የዚያችን ሀገር ሰዎች በሰይፍ ስለት ፈጽሞ ትመታቸዋለህ፤ ሀገሪቱን፥ በውስጥዋም ያለውን ሁሉ ትረግማለህ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም በዚያች ከተማ የሚኖሩትን ሁሉ በሰይፍ ግደላቸው፤ ከተማዪቱን ከነሕዝቧና ከነቀንድ ከብቷ ፈጽሞ ደምስሳት። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) በዚያች ከተማ የሚኖሩትን ሁሉ በሰይፍ ግደላቸው፤ ከተማይቱን ከነ ሕዝቧና ከነ ቀንድ ከብቷ ፈጽሞ ደምስስ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም በዚያች ከተማ የሚኖሩትን ሰዎች ከከብቶቻቸው ሁሉ ጋር በሙሉ ግደል፤ ያቺንም ከተማ በፍጹም ደምስስ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) የዚያችን ከተማ ሰዎች በሰይፍ ስለት ፈጽሞ ትመታቸዋለህ፤ ከተማይቱን፥ በእርስዋም ያለውን ሁሉ፥ እንስሳውንም በሰይፍ ስለት ታጠፋቸዋለህ። |
የስደተኞቹም ልጆች እንዲህ አደረጉ፤ ካህኑ ዕዝራ፥ የአባቶችም ቤቶች አለቆች በየአባቶቻቸው ቤቶች ሁሉም በየስማቸው ተለዩ፤ በዐሥረኛውም ወር በመጀመሪያው ቀን ነገሩን ይመረምሩ ዘንድ ተቀመጡ።
ለአማልክቶቻቸው አትስገድ፤ አታምልካቸውም፤ እንደ ሥራቸውም አትሥራ፤ ነገር ግን ፈጽመህ አፍርሳቸው፤ ምስሎቻቸውንም ሰባብራቸው።
“ለእግዚአብሔርም የተለየ እርም የሆነ ነገር ሁሉ፥ ሰው ቢሆን ወይም እንስሳ ወይም የርስቱ እርሻ ቢሆን፥ አይሸጥም፤ አይቤዥም፤ እርም የሆነ ነገር ሁሉ ለእግዚአብሔር ቅዱሰ ቅዱሳን ነው።
ትፈልጋለህ ትመረምራለህም፤ ትጠይቃለህም፤ እነሆም፥ እውነት ቢሆን፥ ይህም ክፉ ነገር በመካከልህ እንደ ተደረገ ርግጥ ሆኖ ቢገኝ፥
ከግብፅ ምድር ካወጣችሁ፥ ከባርነትም ቤት ካዳናችሁ ከአምላካችሁ ከእግዚአብሔር ሊያስታችሁ፥ አምላክህ እግዚአብሔርም ትሄድባት ዘንድ ካዘዘህ መንገድ ሊያወጣህ ተናግሮአልና ያ ነቢይ ወይም ሕልም አላሚ ይገደል፤ እንዲሁም ክፉውን ነገር ከአንተ አርቅ።
ቢያወሩልህም ብትሰማም፥ ያን ፈጽመህ መርምር፤ እነሆም፥ እውነት ቢሆን፥ በእስራኤልም መካከል እንዲህ ያለ ርኵሰት እንደ ተሠራ ርግጥ ሆኖ ቢገኝ፥
በዚያን ጊዜም ከተሞቹን ሁሉ ወሰድን፤ ከተማውንም ሁሉ፥ ሴቶችንም፥ ሕፃኖችንም አጠፋን፤ አንዳችም የሸሸ በሕይወት አላስቀረንም፥
አምላክህም እግዚአብሔር የሚሰጥህን የአሕዛብ ምርኮ ትበላለህ፤ ዐይንህም አታዝንላቸውም፤ ያም ለአንተ ክፉ ይሆንብሃልና አማልክቶቻቸውን አታምልካቸው።
አምላክህ እግዚአብሔርም በእጅህ አሳልፎ በሰጣቸውና በመታሃቸው ጊዜ፥ ፈጽመህ አጥፋቸው፤ ከእነርሱም ጋር ቃል ኪዳን አታድርግ፤ አትማራቸውም፤
ከተማዪቱንም፥ በእርስዋም የነበረውን ሁሉ በእሳት አቃጠሉ፤ ነገር ግን ብሩንና ወርቁን፥ የናሱንና የብረቱንም ዕቃ በእግዚአብሔር ግምጃ ቤት ውስጥ አገቡ።
የብንያምም ልጆች የእስራኤል ልጆች ወደ መሴፋ እንደ ወጡ ሰሙ። የእስራኤልም ልጆች፥ “ይህ ክፉ ነገር እንደምን እንደ ተደረገ ንገሩን” አሉ።
የእስራኤልም ሰዎች በብንያም ልጆች ላይ ዳግመኛ ተመለሱ፤ ሞላውን ከተማ፥ ከብቱንም፥ ያገኙትንም ሁሉ በሰይፍ ስለት አጠፉ፤ ያገኙትንም ከተማ ሁሉ በእሳት አቃጠሉ።