ዘዳግም 13:13 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ክፋተኞች ሰዎች ከእናንተ ዘንድ ወጥተው፦ ሄደን የማታውቋቸውን ሌሎች አማልክት እናምልክ ብለው የከተማቸውን ሰዎች አሳቱ ሲሉ ወሬ ብትሰማ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም ምናምንቴ ሰዎች ከመካከላችሁ ተነሥተው አንተ የማታውቃቸውን፣ “ሌሎች አማልክትን ሄደን እናምልክ” በማለት የከተማቸውን ሕዝብ እያሳቱ ቢሆን፣ መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ክፉ ሰዎች ከመካከላችሁ ተነሥተው አንተ የማታውቃቸውን፥ ‘ሌሎች አማልክትን ሄደን እናምልክ’ በማለት የከተማቸውን ሕዝብ እያሳቱ ቢሆን፥ |
በዚያም አንድ ብንያማዊ የቢኮሪ ልጅ ስሙ ሳቡሄ የሚባል የዐመፅ ልጅ የሆነ ሰው ነበረ፤ እርሱም፥ “ከዳዊት ዘንድ እድል ፋንታ የለንም፦ ከእሴይም ልጅ ዘንድ ርስት የለንም፤ እስራኤል ሆይ፥ እያንዳንድህ ወደ ድንኳንህ ተመለስ” ብሎ መለከት ነፋ።
ዳግመኛም ወልደ አዴር እንዲህ ብሎ ወደ እርሱ ላከ፥ “ሕዝቤና ሠራዊቴ ሁሉ ሀገርህን ሰማርያን ባያጠፉት፥ የቀበሮም ማደሪያ ባያደርጉት አማልክት እንዲህ ያድርጉብኝ፤ እንዲህም ይግደሉኝ።”
እነሆም፥ አንድ ነቢይ ወደ እስራኤል ንጉሥ ወደ አክዓብ መጥቶ፥ “እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ ይህን ብዙ ሕዝብ ሁሉ ታያለህን? እነሆ፥ ዛሬ በእጅህ አሳልፌ እሰጣቸዋለሁ፤ እንግዲህ እኔም እግዚአብሔር እንደ ሆንሁ ታውቃለህ” አለው።
እስራኤልም ከዳዊት ቤት ተለዩ፤ የናባጥንም ልጅ ኢዮርብዓምን አነገሡ፤ ኢዮርብዓምም እግዚአብሔርን ከመከተል እስራኤልን መለሰ፤ ታላቅም ኀጢአት አሠራቸው።
ክፉዎች ሰዎችና የሕግ ተላላፊዎች ልጆችም ወደ እርሱ ተሰበሰቡ፤ ሮብዓም ሕፃን በነበረና በልቡ ድፍረት ባልነበረው ጊዜ፥ ሊቋቋመውም ባልቻለበት ጊዜ፥ በሰሎሞን ልጅ በሮብዓም ላይ በረታበት።
እናንተስ ከአባታችሁ ከሰይጣን ናችሁ፤ የአባታችሁንም ፈቃድ ልታደርጉ ትወዳላችሁ፤ እርሱ ከጥንት ጀምሮ ነፍሰ ገዳይ ነው፤ በእውነትም አይቆምም፤ በእርሱ ዘንድ እውነት የለምና፤ ሐሰትንም በሚናገርበት ጊዜ ከራሱ አንቅቶ ይናገራል፤ ሐሰተኛ ነውና፤ የሐሰትም አባት ነውና።
ክርስቶስን ከቤልሆር ጋር አንድ የሚያደርገው ማን ነው? ወይስ ምእመናንን ከመናፍቃን ጋር አንድ ወገን የሚያደርጋቸው ማን ነው?
ትፈልጋለህ ትመረምራለህም፤ ትጠይቃለህም፤ እነሆም፥ እውነት ቢሆን፥ ይህም ክፉ ነገር በመካከልህ እንደ ተደረገ ርግጥ ሆኖ ቢገኝ፥
እርሱም፦ ሄደን የማታውቃቸውን ሌሎች አማልክት እንከተል እናምልካቸውም ብሎ የተናገረህ ምልክቱ ወይም ተአምራቱ ቢፈጸም፥
“የአባትህ ወይም የእናትህ ልጅ ወንድምህ ወይም ወንድ ልጅህ ወይም ሴት ልጅህ ወይም አብራህ የምትተኛ ሚስትህ ወይም እንደ ነፍስህ ያለ ወዳጅህ በስውር፦ ና፥ ሄደን አንተም አባቶችህም የማታውቋቸውን ሌሎች አማልክት እናምልክ ብሎ ቢያስትህ፥
ቢያወሩልህም ብትሰማም፥ ያን ፈጽመህ መርምር፤ እነሆም፥ እውነት ቢሆን፥ በእስራኤልም መካከል እንዲህ ያለ ርኵሰት እንደ ተሠራ ርግጥ ሆኖ ቢገኝ፥
ወደ ሰማይ አትመልከት፤ አምላክህ እግዚአብሔር ከሰማይ ሁሉ በታች ላሉት አሕዛብ ሁሉ የሰጣቸውን ፀሐይንና ጨረቃን፥ ከዋክብትንና የሰማይን ሠራዊት ሁሉ አይተህ፥ ሰግደህላቸው፥ አምልከሃቸውም እንዳትስት ተጠንቀቅ።
ከእኛ ዘንድ ወጡ፥ ዳሩ ግን ከእኛ ወገን አልነበሩም፤ ከእኛ ወገንስ ቢሆኑ ከእኛ ጋር ጸንተው በኖሩ ነበር፤ ነገር ግን ሁሉ ከእኛ ወገን እንዳልሆኑ ይገለጡ ዘንድ ወጡ።
ሰውነታቸውንም ደስ ባሰኙ ጊዜ የኃጥኣን ልጆች የሆኑ የከተማው ሰዎች ቤቱን ከበቡ፤ በሩንም ይደበድቡ ነበር፤ ባለቤቱንም ሽማግሌውን ሰው፥ “ወደ ቤትህ የገባውን ሰው እንድንደርስበት አውጣልን” አሉት።
“አሁንም በገባዖን ውስጥ የበደሉ የዐመፅ ሰዎችን እንድንገድላቸው አውጥታችሁ ስጡን፤ ከእስራኤልም ልጆች ክፋትን እናርቃለን።” የብንያም ልጆች ግን የወንድሞቻቸውን የእስራኤልን ልጆች ቃል ሊሰሙ አልወደዱም።
ስለዚህም በጌታችንና በቤቱ ሁላ ክፉ ነገር እንዲመጣ ተቈርጦአልና፥ እርሱ ክፉ ሰው ስለ ሆነ ማንም ሊናገረው አይችልምና የምታደርጊውን ተመልከቺና ዕወቂ።”
በዚህ ክፉ ሰው በናባል ላይ ጌታዬ ልቡን እንዳይጥል እለምናለሁ፤ እንደ ስሙ እንዲሁ እርሱ ነው፤ ስሙ ናባል ነው፤ ስንፍናም አድሮበታል፤ እኔ ባሪያህ ግን አንተ የላክሃቸውን ብላቴኖችህን አላየሁም።