ሙሴም ሕዝቡን አለ፥ “ከባርነት ቤት ከግብፅ የወጣችሁባትን ይህችን ቀን ዐስቡ፤ እግዚአብሔር ከዚህ ቦታ በበረታች እጅ አውጥቶአችኋልና። ስለዚህ የቦካ እንጀራ አትብሉ።
ዘዳግም 13:11 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) እስራኤል ሁሉ ሰምተው ይፍሩ፤ እንዲህ ያለ ክፉ ሥራም እንደገና በእናንተ መካከል አይደገም። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ከዚያም እስራኤል ሁሉ ሰምተው ይፈራሉ፤ ከመካከልህም ማንም እንደዚህ ያለውን ክፉ ነገር ዳግም አያደርግም። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ከዚያም እስራኤል ሁሉ ሰምተው ይፈራሉ፤ ከመካከልህም በማንም እንደዚህ ያለውን ክፉ ነገር ዳግም አይደረግም።” አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ከዚህም በኋላ የእስራኤል ሕዝብ ሁሉ የሆነውን ነገር ሰምተው ይፈራሉ፤ ስለዚህም ያንን ዐይነት ክፉ ነገር እንደገና የሚያደርግ አይኖርም። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) እስራኤልም ሁሉ ሰምተው ይፈራሉ፥ እንዲህም ያለ ክፉ ሥራ እንደ ገና በአንተ መካከል አያደርጉም። |
ሙሴም ሕዝቡን አለ፥ “ከባርነት ቤት ከግብፅ የወጣችሁባትን ይህችን ቀን ዐስቡ፤ እግዚአብሔር ከዚህ ቦታ በበረታች እጅ አውጥቶአችኋልና። ስለዚህ የቦካ እንጀራ አትብሉ።
“ደግሞ የእስራኤልን ልጆች እንዲህ በላቸው፦ ከእስራኤል ልጆች ወይም በእስራኤል ዘንድ ከሚቀመጡ እንግዶች ማናቸውም ሰው ዘሩን ለሞሎክ አገልግሎት ቢሰጥ ፈጽሞ ይገደል፤ የሀገሩ ሕዝብ በድንጋይ ይውገሩት።
እግዚአብሔርም ሙሴን አለው፥ “የእግዚአብሔርን ትእዛዝ ስላፈረሱ የሕዝቡን አለቆች ሁሉ ወስደህ በፀሐይ ፊት ቅጣቸው። የእግዚአብሔርም ቍጣ ከእስራኤል ይርቃል።”
የከተማዉም ሰዎች ሁሉ በድንጋይ ደብድበው ይግደሉት፤ እንዲህም ክፉውን ነገር ከመካከልህ ታርቃለህ፤ እስራኤልም ሁሉ ሰምተው ይፈራሉ።
ኢያሱም፥ “ለምን አጠፋኸን? ዛሬ እንዳጠፋኸን እግዚአብሔር ዛሬ ያጥፋህ” አለው፤ እስራኤልም ሁሉ በድንጋይ ወገሩት፤ በእሳትም አቃጠሉት፤ በድንጋይም ወገሩአቸው።