የመንግሥታት ክብር፥ የከለዳውያንም የትዕቢታቸው ትምክሕት የሆነች ባቢሎንም እግዚአብሔር እንደ ገለበጣቸው እንደ ሰዶምና እንደ ገሞራ ትሆናለች።
አሞጽ 4:11 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ሰዶምንና ገሞራን አስቀድሜ እንደ ገለበጥኋቸው፥ እንዲሁ ገለበጥኋችሁ፤ እናንተም ከእሳት ውስጥ እንደ ተነጠቀ ትንታግ ሆናችሁ፤ በዚህም ወደ እኔ አልተመለሳችሁም” ይላል እግዚአብሔር። አዲሱ መደበኛ ትርጒም “ሰዶምንና ገሞራን እንደ ገለበጥኋቸው፣ አንዳንዶቻችሁን ገለበጥሁ፤ ከእሳት እንደ ተነጠቀ ትንታግ ሆናችሁ፤ እናንተ ግን ወደ እኔ አልተመለሳችሁም፤” ይላል እግዚአብሔር። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) “ሰዶምንና ገሞራን እግዚአብሔር እንደ ገለባበጣቸው፥ እንዲሁ ገለባበጥኋችሁ፥ እናንተም ከእሳት ውስጥ እንደ ተነጠቀ ትንታግ ሆናችሁ፤ ነገር ግን ወደ እኔ አልተመለሳችሁም፥” ይላል ጌታ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም “ሰዶምንና ገሞራን እንደ ደመሰስኩ ከእናንተም ብዙዎችን ደመሰስኩ፤ እናንተም የተረፋችሁት በእሳት ከተቀጣጠለ በኋላ ተነጥቆ እንደ ወጣ እንጨት ነው፤ ይህም ሁሉ ሆኖ ወደ እኔ አልተመለሳችሁም። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ሰዶምንና ገሞራን እግዚአብሔር እንደ ገለበጣቸው፥ እንዲሁ ገለበጥኋችሁ፥ እናንተም ከእሳት ውስጥ እንደ ተነጠቀ ትንታግ ሆናችሁ፥ ነገር ግን ወደ እኔ አልተመለሳችሁም፥ ይላል እግዚአብሔር። |
የመንግሥታት ክብር፥ የከለዳውያንም የትዕቢታቸው ትምክሕት የሆነች ባቢሎንም እግዚአብሔር እንደ ገለበጣቸው እንደ ሰዶምና እንደ ገሞራ ትሆናለች።
እንዲህም በለው፥ “ተጠበቅ፥ ዝምም በል፤ አትፍራ፤ ከእነዚህ ከሚጤሱ ሁለት የእንጨት ጠለሸቶች፥ የተነሣ ልብህ አይደንግጥ፤ ከተቈጣሁ በኋላ ይቅር እላለሁና።
ጠላቶቹን ሶርያውያንንም ከምሥራቅ፥ አረማውያንንም ከምዕራብ ያንቀሳቅስበታል፤ እስራኤልንም በተከፈተ አፍ ይበሉታል። በዚህም ሁሉ እንኳ ቍጣው አልተመለሰችም፤ ነገር ግን እጁ ገና ተዘርግታ ትኖራለች።
በኢየሩሳሌምም ነቢያት ላይ የሚያስደነግጥን ነገር አይቻለሁ፤ ያመነዝራሉ፤ በሐሰትም ይሄዳሉ፤ ማንም ከክፋቱ እንዳይመለስ የክፉ አድራጊዎችን እጅ ያበረታሉ፤ ሁሉም እንደ ሰዶም፥ የሚኖሩባትም እንደ ገሞራ ሆኑብኝ።
ሰዶምና ገሞራ፥ በእነርሱም አጠገብ የነበሩት ከተሞች እንደ ተገለበጡ፥ ይላል ሁሉን የሚገዛ እግዚአብሔር፤ እንዲሁ በዚያ ሰው አይቀመጥም፤ የሰው ልጅም አይኖርባትም።
አቤቱ! ዐይኖችህ ለሃይማኖት አይደሉምን? አንተ ቀሥፈሃቸዋል፤ ነገር ግን አላዘኑም፤ ቀጥቅጠሃቸውማል፤ ነገር ግን ተግሣጽን እንቢ አሉ፤ ፊታቸውን ከድንጋይ ይልቅ አጠንክረዋል፤ ይመለሱም ዘንድ እንቢ አሉ።
ሰዶምንና ገሞራን፥ በአጠገባቸውም የነበሩትን ከተሞች እግዚአብሔር እንደ ገለበጣቸው፥ ይላል እግዚአብሔር፤ እንዲሁ ሰው በዚያ አይቀመጥም፤ የሰውም ልጅ አይኖርባትም።
በርኵሰትሽ ሴሰኝነት አለ፤ አነጻሁሽ፤ አልነጻሽምና መዓቴን በላይሽ እስክጨርስ ድረስ እንግዲህ ከርኵሰትሽ አትነጺም።
እኔም “አምልኮቴን ትተሃል አልሁ፤ ኤፍሬም ሆይ! እንዴት አደርግሃለሁ? እስራኤል ሆይ! እንዴትስ እደግፍሃለሁ? እንዴትስ አደርግሃለሁ? እንደ አዳማ ነውን? ወይስ እንደ ሲባዮ? ልቤ በውስጤ ተናውጣለች፤ ምሕረቴም ተገልጣለች።
“በከተማችሁ ሁሉ ጥርስን ማጥረስን፥ በስፍራችሁም ሁሉ እንጀራን ማጣትን ሰጠኋችሁ፤ እናንተ ግን ወደ እኔ አልተመለሳችሁም ይላል እግዚአብሔር።
እግዚአብሔርም ሰይጣንን፦ ሰይጣን ሆይ፥ እግዚአብሔር ይገሥጽህ፣ ኢየሩሳሌምን የመረጠ እግዚአብሔር ይገሥጽህ፣ በውኑ ይህ ከእሳት የተነጠቀ ትንታግ አይደለምን? አለው።
ኢሳይያስም አስቀድሞ እንደ ተናገረ “እግዚአብሔር ጸባኦት ዘር ያስቀረልን ባይሆን ኖሮ እንደ ሰዶም በሆን፥ ገሞራንም በመሰልን ነበር።”
ምድርም በሁለንተናዋ ዲንና ጨው፥ መቃጠልም እንደ ሆነባት፥ እንዳይዘራባትም፥ እንዳታበቅልም፥ ማናቸውም ሣርና ልምላሜም እንዳይወጣባት፥ እግዚአብሔር በቍጣውና በመዓቱ እንደ ገለበጣቸው እንደ ሰዶምና ገሞራ፥ እንደ አዳማና እንደ ሲባዮ እንደ ሆነች ባዩ ጊዜ፥
እንዲሁም እንደ እነርሱ ዝሙትን ያደረጉና ሌላን ሥጋ የተከተሉ ሰዶምና ገሞራ በዙሪያቸውም የነበሩ ከተማዎች በዘላለም እሳት እየተቀጡ ምሳሌ ሆነዋል።
በእነዚህም መቅሠፍቶች ያልተገደሉት የቀሩቱ ሰዎች ለአጋንንትና ያዩ ወይም ይሰሙ ወይም ይሄዱ ዘንድ ለማይችሉ ከወርቅና ከብር ከናስም ከድንጋይም ከእንጨትም ለተሠሩ ለጣዖቶች እንዳይሰግዱ ስለ እጃቸው ሥራ ንስሓ አልገቡም፤