አሞጽ 1:2 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) እንዲህም አለ፥ “እግዚአብሔር ከጽዮን ሆኖ ድምፁን ከፍ አድርጎ ይናገራል፤ ከኢየሩሳሌምም ሆኖ ቃሉን ይሰጣል፤ የእረኞችም ማሰማሪያዎች ያለቅሳሉ፤ የቀርሜሎስም ራስ ይደርቃል።” አዲሱ መደበኛ ትርጒም እርሱም እንዲህ አለ፤ “እግዚአብሔር ከጽዮን ድምፁን ከፍ አድርጎ ያሰማል፤ ከኢየሩሳሌምም ያንጐደጕዳል፤ የእረኞች ማሰማሪያዎች ደርቀዋል፤ የቀርሜሎስም ዐናት ጠውልጓል።” መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) እንዲህም አለ፦ “ጌታ በጽዮን ሆኖ ድምፁን ከፍ አድርጎ ይጮኻል፥ በኢየሩሳሌምም ሆኖ ድምፁን ያስተጋባል፤ የእረኞችም ማሰማርያዎች ይጠወልጋሉ፥ የቀርሜሎስም ራስ ይደርቃል።” አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም አሞጽ እንዲህ አለ፦ “እግዚአብሔር በጽዮን ተራራ ሆኖ እንደሚያገሣ አንበሳ የሚያስፈራ ድምፁን ያሰማል፤ ቃሉም ከኢየሩሳሌም ያስተጋባል፤ እረኞች መንጋ የሚያሰማሩበት መስክ ይጠወልጋል፤ በቀርሜሎስ ተራራ የሚገኘውም ልምላሜ ይደርቃል።” መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) እንዲህም አለ፦ እግዚአብሔር በጽዮን ሆኖ ድምፁን ከፍ አድርጎ ይጮኻል፥ በኢየሩሳሌምም ሆኖ ቃሉን ይሰጣል፥ የእረኞችም ማሰማርያዎች ያለቅሳሉ፥ የቀርሜሎስም ራስ ይደርቃል። |
የዮርዳኖስም ምድረ በዳ ያብባል፤ ሐሤትንም ያደርጋል፤ የሊባኖስ ክብርና የቀርሜሎስ ክብር ይሰጠዋል፤ ሕዝቤም የጌታን ክብር፥ የአምላክንም ግርማ ያያሉ።
የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔር ይወጣል፤ ኀይለኛውንም ያጠፋል፤ ቅንአትንም ያስነሣል፤ በጠላቶቹም ላይ በኀይል ይጮኻል።
በሚኖሩባት ሰዎች ክፋት ምድሪቱ የምታለቅሰውና የዱሩ ሣርስ ሁሉ የሚደርቀው እስከ መቼ ነው? እግዚአብሔር ፍጻሜያችንን አያይም ብለዋልና እንስሶችና ወፎችም ጠፍተዋል።
“ስለዚህም ይህን ቃል ሁሉ ትንቢት ትናገርባቸዋለህ፤ እንዲህም ትላቸዋለህ፦ እግዚአብሔር በላይ ሆኖ እንደ አንበሳ ያገሣል፤ በቅዱስ ማደሪያውም ሆኖ ድምፁን ያሰማል፤ በበረቱ ላይ እጅግ ያገሣል፤ ወይንም እንደሚጠምቁ በምድር በሚኖሩ ሁሉ ላይ ይጮኻል።
ከጥንት ከእኔና ከአንተ በፊት የነበሩ ነቢያት በብዙ ሀገርና በታላላቅ መንግሥታት ላይ ስለ ሰልፍና ስለ ክፉ ነገር ስለ ቸነፈርም ትንቢት ተናገሩ።
እስራኤልንም ወደ ማሰማርያው እመልሳለሁ፥ በቀርሜሎስና በባሳን፥ በኤፍሬም ተራራና በገለዓድም ይሰማራል፤ ነፍሱም ትጠግባለች።
ጌታ እግዚአብሔርን እከተለው ዘንድ እሄዳለሁ፤ እርሱ ያድነናልና፤ እርሱም እንደ አንበሳ ያገሣል፤ የውኃ ልጆችም ይደነግጣሉ።
በአሦራውያንም መንገድ አጠገብ እንደ ተራበ ድብ እገጥማቸዋለሁ፤ የልባቸውንም ሥር እቈርጣለሁ፤ በዚያም የዱር አንበሶች ይበሏቸዋል፤ የምድረ በዳም አራዊት ይነጣጠቋቸዋል።
አቤቱ! እሳት የምድረ በዳውን ውበት አጥፍቶአልና፥ ነበልባሉም የዱሩን ዛፍ ሁሉ አቃጥሎአልና ወደ አንተ እጮኻለሁ።
እግዚአብሔርም በሠራዊቱ ፊት ድምፁን ይሰጣል፤ ሰፈሩ እጅግ ብዙ ነውና፥ የቃሉም ሥራ ጽኑዕ ነውና፤ የእግዚአብሔርም ቀን ታላቅና እጅግ የምታስፈራ ናትና፥ ፈጽማ ትገለጣለች፥ መጠኗ ምንድን ነው? ማንስ ይችላታል?
እግዚአብሔርም በጽዮን ሆኖ ድምፁን ከፍ አድርጎ ይጮኻል፤ በኢየሩሳሌምም ሆኖ ቃሉን ይሰጣል፤ ሰማይና ምድርም ይናወጣሉ፤ እግዚአብሔር ግን ለሕዝቡ ይራራል፤ የእስራኤልንም ልጆች ያጸናል።
በቀርሜሎስ ራስ ውስጥ ቢሸሸጉ ፈልጌ ከዚያ አወጣቸዋለሁ፤ በባሕሩም ጥልቅ ውስጥ ከዐይኔ ቢደበቁ በዚያ እባቡን አዝዛለሁ፤ እርሱም ይነድፋቸዋል፤
በማዖንም የተቀመጠ አንድ ሰው ነበረ፤ ከብቱም በቀርሜሎስ ነበረ፤ እጅግም ታላቅ ሰው ነበረ፤ ለእርሱም ሦስት ሺህ በጎችና አንድ ሺህ ፍየሎች ነበሩት፤ በቀርሜሎስም በጎቹን ሊሸልት ሄደ።