ዮሴፍም ወንድሞቹን፥ “ወደ እኔ ቅረቡ” አላቸው። ወደ እርሱም ቀረቡ። እንዲህም አላቸው፥ “ወደ ግብፅ የሸጣችሁኝ እኔ ወንድማችሁ ዮሴፍ ነኝ።
ሐዋርያት ሥራ 9:17 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ያንጊዜም ሐናንያ ሄደ፤ ወደ ቤትም ገባ፤ እጁንም ጫነበትና፥ “ወንድሜ ሳውል፥ በመንገድ ስትመጣ የታየህ ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ታይና መንፈስ ቅዱስ ይመላብህ ዘንድ ወደ አንተ ልኮኛል” አለው። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ሐናንያ ሄዶ፣ ወደተባለውም ቤት ገባ፤ በሳውልም ላይ እጁን ጭኖ፣ “ወንድሜ ሳውል ሆይ፤ ወደዚህ ስትመጣ በመንገድ ላይ የተገለጠልህ ጌታ ኢየሱስ፣ ዐይንህ እንዲበራና በመንፈስ ቅዱስም እንድትሞላ እኔን ልኮኛል” አለው። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ሐናንያም ሄዶ ወደ ቤቱ ገባ፤ እጁንም ጭኖበት “ወንድሜ ሳውል ሆይ! ጌታ፥ እርሱም በመጣህበት መንገድ የታየህ ኢየሱስ ነው፤ ደግሞ ታይ ዘንድና መንፈስ ቅዱስ ይሞላብህ ዘንድ ላከኝ፤” አለ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ስለዚህ ሐናንያ ወደዚያ ሄዶ እርሱ ወደ ነበረበትም ቤት ገባ፤ እጁንም በሳውል ላይ ጭኖ፥ “ወንድሜ ሳውል ሆይ! ወደዚህ ስትመጣ ሳለ በመንገድ የተገለጠልህ ጌታ ኢየሱስ እንደገና ማየት እንድትችልና መንፈስ ቅዱስም እንዲሞላብህ ወደ አንተ ልኮኛል” አለው። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ሐናንያም ሄዶ ወደ ቤቱ ገባ፥ እጁንም ጭኖበት፦ “ወንድሜ ሳውል ሆይ፥ ጌታ፥ እርሱም በመጣህበት መንገድ የታየህ ኢየሱስ ነው፥ ደግሞ ታይ ዘንድና መንፈስ ቅዱስ ይሞላብህ ዘንድ ላከኝ” አለ። |
ዮሴፍም ወንድሞቹን፥ “ወደ እኔ ቅረቡ” አላቸው። ወደ እርሱም ቀረቡ። እንዲህም አላቸው፥ “ወደ ግብፅ የሸጣችሁኝ እኔ ወንድማችሁ ዮሴፍ ነኝ።
ነገር ግን ይህ ወንድምህ ሞቶ ነበረ፤ ሕያው ሆኖአልና፥ ጠፍቶም ተገኝቶአልና፥ ደስ ሊለን፥ ሐሤትም ልናደርግ ይገባል።”
ጳውሎስም እጁን በጫነባቸው ጊዜ መንፈስ ቅዱስ በእነርሱ ላይ ወረደ፤ ያንጊዜም በሀገሩ ሁሉ ቋንቋ ተናገሩ፤ ትንቢትም ተናገሩ።
ሁሉም መንፈስ ቅዱስን ተሞሉ፤ ይናገሩ ዘንድ መንፈስ ቅዱስ እንደ አደላቸው መጠንም እየራሳቸው በሀገሩ ሁሉ ቋንቋ ይናገሩ ጀመሩ።
እነርሱም ሰምተው እግዚአብሔርን አመሰገኑ፤ እንዲህም አሉ፥ “ወንድማችን ሆይ፥ ከአይሁድ መካከል ያመኑት ስንት አእላፋት እንደ ሆኑ ታያለህን? ሁሉም ለኦሪት የሚቀኑ ናቸው።
ሲጸልዩም በአንድነት ተሰብስበው የነበሩበት ቦታ ተናወጠ፤ በሁሉም ላይ መንፈስ ቅዱስ መላባቸውና የእግዚአብሔርን ቃል በግልጥ አስተማሩ።
ያንጊዜም ፈጥኖ እንደ ቅርፊት ያለ ነገር ከዐይኖቹ ላይ ተገፎ ወደቀ፤ ዐይኖቹም ተገለጡ፤ ወዲያውም አየ፤ ተነሥቶም ተጠመቀ።
እኔ ነጻ አይደለሁምን? ሐዋርያስ አይደለሁምን? ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስን ያየሁ አይደለሁምን? እናንተስ በጌታችን ሥራዬ አይደላችሁምን?
ከእንግዲህ ወዲህ እንደ ባሪያ አይሆንም፤ ነገር ግን ለእኔ በተለየ የተወደደ ወንድም ከሆነ፥ ለአንተማ ይልቅ በሥጋውም በጌታም ዘንድ ከባሪያ የሚሻል የተወደደ ወንድም እንዴት አይሆንም?