እግዚአብሔርም ለአብራም ተገለጠለትና፥ “ይህችን ምድር ለዘርህ እሰጣለሁ” አለው። አብራምም ለእርሱ ለተገለጠለት ለእግዚአብሔር በዚያ መሠውያን ሠራ።
ሐዋርያት ሥራ 7:5 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) በውስጥዋም አንድ ጫማ ታህል ስንኳን ርስት አልሰጠውም፤ ነገር ግን እርሱ ከእርሱም በኋላ ዘሩ ሊገዛት ልጅ ሳይኖረው ያንጊዜ እርስዋን ያወርሰው ዘንድ ተስፋ ሰጠው። አዲሱ መደበኛ ትርጒም በዚህም ስፍራ አንዲት ጫማ ታኽል እንኳ ርስት አልሰጠውም፤ ነገር ግን በዚያ ጊዜ ምንም ልጅ ሳይኖረው፣ እርሱና ከርሱም በኋላ ዘሩ ምድሪቱን እንደሚወርሱ እግዚአብሔር ቃል ገባለት። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) በዚችም የእግር ጫማ ስንኳ የሚያህል ርስት አልሰጠውም፤ ነገር ግን ልጅ ሳይኖረው ለእርሱ ከእርሱም በኋላ ለዘሩ ርስት አድርጎ ይሰጠው ዘንድ ተስፋ ሰጠው። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ይሁን እንጂ የእግር ማሳረፊያ እንኳ የሚያኽል ርስት አልሰጠውም፤ ነገር ግን ይህችን አገር ለእርሱና ከእርሱም በኋላ ለዘሩ ርስት አድርጎ እንደሚሰጠው ቃል ገብቶለት ነበር፤ ይህን ቃል የገባለትም አብርሃም ገና ልጅ ሳይኖረው ነበር። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) በዚችም የእግር ጫማ ስንኳ የሚያህል ርስት አልሰጠውም፤ ነገር ግን ልጅ ሳይኖረው ለእርሱ ከእርሱም በኋላ ለዘሩ ርስት አድርጎ ይሰጠው ዘንድ ተስፋ ሰጠው። |
እግዚአብሔርም ለአብራም ተገለጠለትና፥ “ይህችን ምድር ለዘርህ እሰጣለሁ” አለው። አብራምም ለእርሱ ለተገለጠለት ለእግዚአብሔር በዚያ መሠውያን ሠራ።
በዚያችም ቀን እግዚአብሔር ለአብራም ተስፋ ያደረገለትን ቃል ኪዳን አጸና፤ እንዲህም አለው፥ “ከግብፅ ወንዝ ጀምሮ እስከ ትልቁ ወንዝ እስከ ኤፍራጥስ ወንዝ ድረስ ይህችን ምድር ለዘርህ እሰጣታለሁ፤
ሦራም አብራምን፥ “እነሆ፥ እንዳልወልድ እግዚአብሔር ዘጋኝ፤ ከእርስዋ ትወልድ ዘንድ ወደ አገልጋዬ ሂድ” አለችው። አብራምም የሚስቱን የሦራን ቃል ሰማ።
በውስጥዋ የምትኖርባትን ይህችን ምድር፥ የከነዓንን ምድር ሁሉ፥ ለዘለዓለም ይገዙአት ዘንድ ለዘርህ እሰጣለሁ፤ አምላክም እሆናቸዋለሁ።”
“እኔ በእናንተ ዘንድ ስደተኛና መጻተኛ ነኝ፤ በእናንተ ዘንድ እንድገዛ የመቃብር ርስት ስጡኝ፤ ሬሳዬንም እንደ እናንተ ልቅበር።”
በዚህች ምድር ተቀመጥ፤ ከአንተ ጋርም እሆናለሁ፤ እባርክሃለሁም፤ ይህችን ምድር ሁሉ ለአንተም፥ ለዘርህም እሰጣለሁና፥ ለአባትህም ለአብርሃም የማልሁለትን መሐላ ከአንተ ጋር አጸናለሁ።
ልቡም በፊትህ የታመነ ሆኖ አገኘኸው፤ የከነዓናዊውንና የኬጤዎናዊውን፥ የአሞሬዎናዊውንም፥ የፌርዜዎናዊውንም፥ የኢያቡሴዎናዊውንም፥ የጌርጌሴዎናዊውንም ምድር ለእርሱና ለዘሩ ትሰጥ ዘንድ ከእርሱ ጋር ቃል ኪዳን አደረግህ፤ አንተም ጻድቅ ነህና ቃልህን አጸናህ።
“የሰው ልጅ ሆይ! በእስራኤል ምድር በአሉ በባድማ ስፍራዎች የተቀመጡ፦ አብርሃም ብቻውን ሳለ ምድሪቱን ወረሰ፤ እኛም ብዙዎች ነን፤ ምድሪቱም ርስት ሆና ለእኛ ተሰጥታለች ይላሉ። ስለዚህ እንዲህ በላቸው፦
እግዚአብሔርም፦ ‘ተነሥተህ በሕዝቡ ፊት ተጓዝ፤ ለአባቶቻቸውም ልሰጣቸው ወደ ማልሁላቸው ምድር ይግቡ፤ ይውረሱአትም’ አለኝ።
እግዚአብሔር ለእነርሱና ከእነርሱም በኋላ ለዘራቸው ወተትና ማር የምታፈስሰውን ምድር ይሰጣቸው ዘንድ ለአባቶቻችሁ በማለላቸው ምድር ላይ ዕድሜያችሁ እንዲረዝም።
የሴይርን ተራራ ለዔሳው ልጆች ርስት አድርጌ ስለ ሰጠሁ እኔ ከምድራቸው የጫማ መርገጫ ታህል እንኳን አልሰጣችሁምና አትጣሉአቸው።
እግዚአብሔርም ሙሴን፥ “ለዘርህ እሰጣታለሁ ብዬ ለአብርሃምና ለይስሐቅ ለያዕቆብም የማልሁላቸው ምድር ይህች ናት፤ እነሆም፥ በዐይንህ እንድታያት አደረግሁህ፤ ነገር ግን ወደዚያች አትገባም” አለው።
ምድራቸውን ትወርሳት ዘንድ የምትገባው ስለ ጽድቅህና ስለ ልብህ ቅንነት አይደለም፤ ነገር ግን አምላክህ እግዚአብሔር ከፊትህ በሚያጠፋቸው በእነዚያ አሕዛብ ኀጢአት ምክንያትና ለአባቶችህ ለአብርሃምና ለይስሐቅ ለያዕቆብም የማለላቸውን ቃል ያጸና ዘንድ ነው።