ደቀ መዛሙርቱም ከበቡት፤ ነገር ግን ተነሥቶ አብሮአቸው ወደ ከተማ ገባ፤ በማግሥቱም ከበርናባስ ጋር ወደ ደርቤን ሄደ።
ሐዋርያት ሥራ 20:4 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ከእርሱም ጋር የቤርያ ሀገር ሰው የሚሆን ሱሲጳጥሮስ፥ የተሰሎንቄም ሰዎች አርስጥሮኮስና ሲኮንዱስ፥ የደርቤኑ ሰው ጋይዮስና ጢሞቴዎስም፥ የእስያ ሰዎች የሚሆኑ ቲኪቆስና ጥሮፊሞስም አብረውት ሄዱ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም የጳይሮስ ልጅ የቤርያው ሱሲጴጥሮስ፣ የተሰሎንቄዎቹ አርስጥሮኮስና ሲኮንዱስ፣ የደርቤኑ ጋይዮስ፣ ከእስያ አውራጃ የመጡት ቲኪቆስና ጥሮፊሞስ እንዲሁም ጢሞቴዎስ ዐብረውት ሄዱ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) የሸኙትም የቤርያው ሶጳጥሮስ ከተሰሎንቄ ሰዎችም አርስጥሮኮስና ሲኮንዱስ የደርቤኑም ጋይዮስና ጢሞቴዎስ የእስያ ሰዎችም ቲኪቆስ ጥሮፊሞስም ነበሩ፤ አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም የጲርሁስ ልጅ ሶጳጥሮስ ከቤርያ፥ አርስጥሮኮስና ሲኮንዱስ ከተሰሎንቄ፥ ጋይዮስ ከደርቤ፥ ጢሞቴዎስ፥ ቲኪቆስና ጥሮፊሞስ ከእስያ አብረውት ሄዱ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) የሸኙትም የቤርያው ሱሲጳጥሮስ ከተሰሎንቄ ሰዎችም አርስጥሮኮስና ሲኮንዱስ የደርቤኑም ጋይዮስና ጢሞቴዎስ የእስያ ሰዎችም ቲኪቆስ ጥሮፊሞስም ነበሩ፤ |
ደቀ መዛሙርቱም ከበቡት፤ ነገር ግን ተነሥቶ አብሮአቸው ወደ ከተማ ገባ፤ በማግሥቱም ከበርናባስ ጋር ወደ ደርቤን ሄደ።
ወደ ደርቤንና ወደ ልስጥራን ከተማም ደረሰ፤ እነሆም፥ በዚያ የአንዲት ያመነች አይሁዳዊት ልጅ ጢሞቴዎስ የሚባል አንድ ደቀ መዝሙር ነበር፤ አባቱ ግን አረማዊ ነበረ።
ነገር ግን የእግዚአብሔርን ቃል በእስያ እንዳይናገሩ መንፈስ ቅዱስ ስለከለከላቸው ወደ ፍርግያና ወደ ገላትያ አውራጃ ሄዱ፤
በተሰሎንቄ የነበሩ አይሁድ ግን ጳውሎስ በቤርያ የእግዚአብሔርን ቃል እንደ አስተማረ ባወቁ ጊዜ፥ ወደዚያ መጥተው ሕዝቡን አወኩአቸው።
ከተማውም ሁሉ ታወከ፤ የመቄዶንያን ሰዎች የጳውሎስን ወዳጆች ጋይዮስንና አርስጥሮኮስንም ከእነርሱ ጋር እየጐተቱበአንድነት ወደ ጨዋታው ቦታ ሮጡ።
እኛ በተወለድንበት በጳርቴ፥ በሜድ፥ በኢላሜጤ፥ በሁለቱ ወንዞች መካከል፥ በይሁዳ፥ በቀጰዶቅያ፥ በጳንጦስና በእስያ፥
ጳውሎስም በእስያ እንዳይዘገይ በኤፌሶን በኩል ሊሄድ ቈርጦ ነበር፤ የሚቻለውም ቢሆን ለበዓለ ኀምሳ ኢየሩሳሌም ለመድረስ ቸኵሎ ነበርና።
ወደ እርሱም በመጡ ጊዜ እንዲህ አላቸው፥ “ወደ እስያ ከገባሁበት ከመጀመሪያው ቀን ጀምሮ በዘመኑ ሁሉ ከእናንተ ዘንድ እንደ ተቀመጥሁ እናንተ ታውቃላችሁ።
የኤፌሶን ሀገር ሰው የሆነ ጥሮፊሞስን ከጳውሎስ ጋር በከተማ አይተውት ነበርና፤ ጳውሎስም ወደ ቤተ መቅደስ ያስገባው መስሎአቸው ነበርና።
በተነሣንም ጊዜ ወደ እስያ በምትሄድ በአድራማጢስ መርከብ ተሳፈርን፤ የተሰሎንቄ ሀገር ሰው የሚሆን መቄዶንያዊው አርስጥሮኮስም አብሮን ሄደ።
ከእኔ ጋር በሥራ የሚተባበረው ጢሞቴዎስም፥ ከዘመዶች ወገን የሚሆኑ ሉቅዮስም፥ ኢያሶንም፥ ሱሲ ጴጥሮስም ሰላም ይሉአችኋል።
እኔንና አብያተ ክርስቲያናትን ሁሉ በእንግድነት የተቀበለ ጋይዮስም ሰላም ብሎአችኋል፤ የከተማው መጋቢ አርስጦስና ወንድማችን ቁአስጥሮስም ሰላም ብለዋችኋል።
በእግዚአብሔር ፈቃድ የኢየሱስ ክርስቶስ ሐዋርያ ከሆነ ጳውሎስና ከወንድማችን ጢሞቴዎስ በቆሮንቶስ ሀገር ላለችው የእግዚአሔር ቤተ ክርስቲያንና በአካይያ ሀገር ላሉ ቅዱሳን ሁሉ፥
እኛ ማለት እኔ ጳውሎስ፥ ስልዋኖስና ጢሞቴዎስ የሰበክንላችሁ የእግዚአብሔር ልጅ ኢየሱስ ክርስቶስ እውነትና ሐሰት አይደለም፤ ነገር ግን ስለ እርሱ ያስተማርነው እውነት ነው።
እናንተም ዜናዬን እንድታውቁ የምንወደው ወንድማችን የታመነ የእግዚአብሔር አገልጋይ ቲኪቆስ የምሠራውን ሁሉ ያስረዳችኋል።
ጢሞቴዎስን እንድልክላችሁ፥ እኔም ዜናችሁን ሰምቼ ደስ እንዲለኝ በጌታችን በኢየሱስ ክርስቶስ ተስፋ አደርጋለሁ።
ከእኔ ጋር የተማረከው አርስጥሮኮስ፥ ወደ እናንተ በሚመጣ ጊዜ ትቀበሉት ዘንድ ስለ እርሱ ያዘዝኋችሁ የበርናባስ የአባቱ ወንድም ልጅ ማርቆስም፥