Biblia Todo Logo
La Biblia Online

- Anuncios -




ሐዋርያት ሥራ 17:1 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

1 አን​ፊ​ጶ​ልና አጶ​ሎ​ንያ ወደ​ሚ​ባሉ ሀገ​ሮ​ችም ሄዱ፤ የአ​ይ​ሁድ ምኵ​ራብ ወደ አለ​በት ወደ ተሰ​ሎ​ን​ቄም ደረሱ።

Ver Capítulo Copiar

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

1 ጳውሎስና ሲላስም በአንፊጶልና በአጶሎንያ ዐልፈው ወደ ተሰሎንቄ ሄዱ፤ በዚያም የአይሁድ ምኵራብ ነበር።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

1 በአንፊጶሊስና በአጶሎንያም ካለፉ በኋላ ወደ ተሰሎንቄ መጡ፤ በዚያም የአይሁድ ምኵራብ ነበረ።

Ver Capítulo Copiar

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

1 ጳውሎስና ሲላስ በአንፊጶሊስና በአጶሎንያ አልፈው ወደ ተሰሎንቄ ሄዱ፤ እዚያም የአይሁድ ምኲራብ ነበረ።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

1 በአንፊጶልና በአጶሎንያም ካለፉ በኋላ ወደ ተሰሎንቄ መጡ፥ በዚያም የአይሁድ ምኵራብ ነበረ።

Ver Capítulo Copiar




ሐዋርያት ሥራ 17:1
13 Referencias Cruzadas  

በተ​ሰ​ሎ​ን​ቄም ሳለሁ ደግሞ፥ አንድ ጊዜና ሁለት ጊዜ ለች​ግሬ ላካ​ች​ሁ​ልኝ።


ጳውሎስና ስልዋኖስ ጢሞቴዎስም፥ በእግዚአብሔር አብ በጌታ በኢየሱስ ክርስቶስም ወደምትሆን ወደ ተሰሎንቄ ሰዎች ቤተ ክርስቲያን፤ ከእግዚአብሔር ከአባታችን ከጌታ ከኢየሱስ ክርስቶስም ጸጋ ሰላምም ለእናንተ ይሁን።


ጳውሎስና ስልዋኖስ ጢሞቴዎስም፥ በእግዚአብሔር በአባታችን በጌታ በኢየሱስ ክርስቶስም ወደምትሆን ወደ ተሰሎንቄ ሰዎች ቤተ ክርስቲያን፤


ከእ​ር​ሱም ጋር የቤ​ርያ ሀገር ሰው የሚ​ሆን ሱሲ​ጳ​ጥ​ሮስ፥ የተ​ሰ​ሎ​ን​ቄም ሰዎች አር​ስ​ጥ​ሮ​ኮ​ስና ሲኮ​ን​ዱስ፥ የደ​ር​ቤኑ ሰው ጋይ​ዮ​ስና ጢሞ​ቴ​ዎ​ስም፥ የእ​ስያ ሰዎች የሚ​ሆኑ ቲኪ​ቆ​ስና ጥሮ​ፊ​ሞ​ስም አብ​ረ​ውት ሄዱ።


ዴማስ የአሁኑን ዓለም ወዶ ትቶኛልና፤ ወደ ተሰሎንቄም ሄዶአል፤ ቄርቂስም ወደ ገላትያ ቲቶም ወደ ድልማጥያ ሄደዋል።


በተ​ነ​ሣ​ንም ጊዜ ወደ እስያ በም​ት​ሄድ በአ​ድ​ራ​ማ​ጢስ መር​ከብ ተሳ​ፈ​ርን፤ የተ​ሰ​ሎ​ንቄ ሀገር ሰው የሚ​ሆን መቄ​ዶ​ን​ያ​ዊው አር​ስ​ጥ​ሮ​ኮ​ስም አብ​ሮን ሄደ።


በተ​ሰ​ሎ​ንቄ የነ​በሩ አይ​ሁድ ግን ጳው​ሎስ በቤ​ርያ የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ቃል እንደ አስ​ተ​ማረ ባወቁ ጊዜ፥ ወደ​ዚያ መጥ​ተው ሕዝ​ቡን አወ​ኩ​አ​ቸው።


በተ​ሰ​ሎ​ንቄ ካሉ​ትም እነ​ርሱ ይሻ​ላሉ፤ በፍ​ጹም ደስታ ቃላ​ቸ​ውን ተቀ​ብ​ለ​ዋ​ልና፤ ነገ​ሩም እንደ አስ​ተ​ማ​ሩ​አ​ቸው እንደ ሆነ ለመ​ረ​ዳት ዘወ​ትር መጻ​ሕ​ፍ​ትን ይመ​ረ​ምሩ ነበር።


በሰ​ን​በት ቀንም ከከ​ተ​ማዉ በር ወደ ባሕሩ ዳር ወጣን፤ በዚያ የጸ​ሎት ቤት ያለ መስ​ሎን ነበ​ርና፤ በዚ​ያም ተቀ​ም​ጠን፥ በዚያ ለተ​ሰ​በ​ሰቡ ሴቶች እና​ስ​ተ​ምር ጀመ​ርን።


ሙሴም ከጥ​ንት ጀምሮ በየ​ከ​ተ​ማዉ የሚ​ሰ​ብ​ክ​ላ​ቸው ትም​ህ​ርት ነበር፤ በየ​ም​ኵ​ራ​ቡም በየ​ሰ​ን​በቱ ያነ​ብ​ቡት ነበር።”


ኢቆ​ን​ዮን በም​ት​ባል ከተ​ማም እንደ ሁል​ጊ​ዜው ወደ አይ​ሁድ ምኵ​ራብ ገቡ፤ ከአ​ይ​ሁ​ድና ከአ​ረ​ማ​ው​ያ​ንም ብዙ ሰዎች እስ​ኪ​ያ​ምኑ ድረስ አስ​ተ​ማሩ።


ወን​ድ​ሞች ግን ጳው​ሎ​ስ​ንና ሲላ​ስን በሌ​ሊት ወደ ቤርያ ሸኙ​አ​ቸው፤ ወደ​ዚ​ያም በደ​ረሱ ጊዜ ወደ አይ​ሁድ ምኵ​ራብ ገቡ።


ነገር ግን እንደምታውቁት በፊልጵስዩስ አስቀድመን መከራ ተቀብለን ተንገላትተንም፥ በብዙ ገድል የእግዚአብሔርን ወንጌል ለእናንተ እንናገር ዘንድ በአምላካችን ደፈርን።


Síguenos en:

Anuncios


Anuncios