ሎጥም ወጣ፤ ልጆቹን ለሚያገቡት ለአማቾቹም አላቸው፥ “ተነሡ፤ ከዚች ስፍራ ውጡ፤ እግዚአብሔር ይህችን ከተማ ያጠፋታልና።” ለአማቾቹ ግን የሚያፌዝባቸው መሰላቸው።
ሐዋርያት ሥራ 17:32 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) የሙታንንም ትንሣኤ በሰሙ ጊዜ እኩሌቶቹ አፌዙበት፤ ሌሎችም፥ “ስለዚህ ነገር በሌላ ቀን እናዳምጥሃለን” አሉት። አዲሱ መደበኛ ትርጒም እነርሱም ስለ ሙታን ትንሣኤ በሰሙ ጊዜ፣ አንዳንዶቹ አፌዙ፤ ሌሎች ግን፣ “ስለዚህ ጕዳይ ከአንተ ዳግመኛ ለመስማት እንፈልጋለን” አሉት። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) የሙታንንም ትንሣኤ በሰሙ ጊዜ እኩሌቶቹ አፌዙበት፤ እኩሌቶቹ ግን “ስለዚህ ነገር ሁለተኛ እንሰማሃለን፤” አሉት። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም “ከሞት መነሣት” የሚለውን ቃል በሰሙ ጊዜ አንዳንዶች አፌዙበት፤ ሌሎች ግን “ስለዚህ ጉዳይ ስትናገር ሌላ ጊዜ እንሰማለን” አሉት። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) የሙታንንም ትንሣኤ በሰሙ ጊዜ እኵሌቶቹ አፌዙበት፥ እኵሌቶቹ ግን፦ ስለዚህ ነገር ሁለተኛ እንሰማሃለን አሉት። |
ሎጥም ወጣ፤ ልጆቹን ለሚያገቡት ለአማቾቹም አላቸው፥ “ተነሡ፤ ከዚች ስፍራ ውጡ፤ እግዚአብሔር ይህችን ከተማ ያጠፋታልና።” ለአማቾቹ ግን የሚያፌዝባቸው መሰላቸው።
እነርሱ ግን የእግዚአብሔር ቍጣ በሕዝቡ ላይ እስኪወጣ ድረስ፥ ፈውስም እስከማይገኝላቸው ድረስ፥ በእግዚአብሔር መልእክተኞች ይሳለቁ፥ ቃሉንም ያቃልሉ፥ በነቢያቱም ላይ ያፌዙ ነበር።
ሁሉም በአንድ ቃል ተባብረው እንቢ አሉ፤ የመጀመሪያው፦ እርሻ ገዝችአለሁ፤ ሄጄም ላያት እሻለሁ፤ እንቢ እንደ አላልሁ ቍጠርልኝ በለው አለው።
‘እነሆ፥ እናንተ የምታቃልሉ፥ እዩ፤ ተደነቁም፤ ያለዚያ ግን ትጠፋላችሁ፤ ማንም ቢነግራችሁ የማታምኑትን ሥራ እኔ በዘመናችሁ እሠራለሁና።’ ”
የኤፌቆሮስን ትምህርት ከተማሩ ፈላስፋዎች መካከልና ረዋቅያውያን ከሚባሉት ወገን የሆኑ ሌሎች ፈላስፎችም የተከራከሩት ነበሩ፤ እኩሌቶችም፥ “ይህ ለፍላፊ ምን ሊናገር ይፈልጋል?” ይሉ ነበር፤ ሌሎችም፥ “ስለ ኢየሱስ ከሙታን ስለ መነሣቱም ሰብኮላቸዋልና የአዲስ አምላክ ትምህርትን ያስተምራል” አሉ።
በመረጠው ሰው እጅ በዓለም በእውነት የሚፈርድባትን ቀን ወስኖአልና፤ እርሱን ከሙታን ለይቶ በማስነሣቱም ብዙዎችን ወደ ሃይማኖት መልሶአልና።”
እርሱም ስለ ጽድቅና ስለ ንጽሕና፥ ስለሚመጣውም ኵነኔ በነገራቸው ጊዜ በዚህ የተነሣ ፊልክስ ፈራና ጳውሎስን፥ “አሁንስ ሂድ፤ በተመቸኝም ጊዜ ልኬ አስጠራሃለሁ” አለው።
ስለ ሃይማኖታቸው ከሆነው ክርክርና ስለ ሞተው፥ ጳውሎስ ግን ሕያው ነው ስለሚለው ሰው ስለ ኢየሱስ ከሆነው ክርክር በቀር፤
ክርስቶስ ከሙታን ተለይቶ ተነሥቶአል ብለን ለሌላው የምናስተምር ከሆነ፥ እንግዲህ ከመካከላችሁ ሙታን አይነሡም የሚሉ እንዴት ይኖራሉ?
እኛስ ስለ ክርስቶስ ብለን አላዋቂዎች ነን፤ እናንተ ግን በክርስቶስ ጠቢባን ናችሁ፤ እኛ ደካሞች ነን፤ እናንተ ግን ብርቱዎች ናችሁ፤ እናንተ ክቡራን ናችሁ፤ እኛ ግን የተዋረድን ነን።