ነገር ግን ይህ ወንድምህ ሞቶ ነበረ፤ ሕያው ሆኖአልና፥ ጠፍቶም ተገኝቶአልና፥ ደስ ሊለን፥ ሐሤትም ልናደርግ ይገባል።”
ሐዋርያት ሥራ 15:3 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ከቤተ ክርስቲያንም በተላኩ ጊዜ ወደ ሰማርያና ወደ ፊንቄ ደርሰው አሕዛብ ወደ ሃይማኖት እንደ ተመለሱ ነገሩቸአቸው፤ ወንድሞችንም ሁሉ እጅግ ደስ አሰኙአቸው። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ቤተ ክርስቲያኒቱም እግረ መንገዳቸውን በፊንቄና በሰማርያ በኩል እንዲያልፉ ላከቻቸው፤ እነርሱም በእነዚህ ቦታዎች ለነበሩት የአሕዛብን መመለስና ማመን ነገሯቸው፤ ወንድሞችም ሁሉ በዚህ እጅግ ደስ አላቸው። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ቤተ ክርስቲያኑም በመንገድ እየረዳቸው እነርሱ የአሕዛብን መመለስ እየተረኩ በፊንቄና በሰማርያ አለፉ፤ ወንድሞችንም ሁሉ እጅግ ደስ አሰኙአቸው። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ስለዚህ እነርሱ በቤተ ክርስቲያን ተልከው ሄዱ፤ በፊንቄና በሰማርያ ሲያልፉም የአሕዛብን ወደ እግዚአብሔር መመለስ ተናገሩ፤ ይህም ዜና ክርስቲያኖችን ሁሉ አስደሰተ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ቤተ ክርስቲያኑም በመንገድ እየረዳቸው እነርሱ የአሕዛብን መመለስ እየተረኩ በፊንቄና በሰማርያ አለፉ፥ ወንድሞችንም ሁሉ እጅግ ደስ አሰኙአቸው። |
ነገር ግን ይህ ወንድምህ ሞቶ ነበረ፤ ሕያው ሆኖአልና፥ ጠፍቶም ተገኝቶአልና፥ ደስ ሊለን፥ ሐሤትም ልናደርግ ይገባል።”
አሕዛብም ይህን ሰምተው ደስ አላቸው፤ የእግዚአብሔርንም ቃል አከበሩ፤ ለዘለዓለም ሕይወትም የተዘጋጁ ሁሉ አመኑ።
አንጾኪያም በደረሱ ጊዜ ምእመናኑን ሁሉ ሰብስበው እግዚአብሔር ያደረገላቸውን ሁሉ፥ ለአሕዛብም የሃይማኖትን በር እንደ ከፈተላቸው ነገሩአቸው።
ከይሁዳ ሀገርም የወረዱ ሰዎች፥ “እንደ ሙሴ ሕግ ካልተገዘራችሁ ልትድኑ አትችሉም” እያሉ ወንድሞችን ያስተምሩ ነበር።
ያንጊዜም ሕዝቡ ሁሉ ጸጥ ብለው እግዚአብሔር በአሕዛብ ዘንድ ያደረገላቸውን ተአምራትና ድንቅ ሥራ ሁሉ ሲናገሩ ጳውሎስንና በርናባስን አዳመጡአቸው።
ከዚህም በኋላ ሐዋርያትና ቀሳውስት ሕዝቡም ሁሉ ከጳውሎስና ከበርናባስ ጋር ወደ አንጾኪያ የሚልኳቸውን ሰዎች ይመርጡ ዘንድ ተስማሙ፤ ከባልንጀሮቻቸው መካከልም የተማሩትን ሰዎች በርናባስ የተባለ ይሁዳንና ሲላስን መረጡ።
ወደ ኢየሩሳሌም በደረሱ ጊዜም ምእመናንና ሐዋርያት፥ ቀሳውስትም ተቀበሉአቸው፤ እግዚአብሔርም በአሕዛብ መካከል ያደረገላቸውን ነገሩአቸው።
ጳውሎስን የሸኙት ሰዎችም እስከ አቴና ከተማ ድረስ አብረውት መጥተው ነበርና ፈጥነው ይከተሉት ዘንድ ወደ ሲላስና ወደ ጢሞቴዎስ ላካቸው፤ ተመልሰውም ሄዱ።
ከዚህም በኋላ ለመሄድ ወጣን፤ ሁሉም ከሚስቶቻቸውና ከልጆቻቸው ጋር እስከ ከተማው ውጭ ሸኙን፤ በባሕሩም ዳር ተንበርክከን ጸለይን።
በዚያም ያሉት ወንድሞች ስለ እኛ በሰሙ ጊዜ፤ አፍዩስ ፋሩስ እስከሚባለው ገበያና እስከ ሦስተኛው ማረፊያ ድረስ ወጥተው ተቀበሉን፤ ጳውሎስም ባያቸው ጊዜ እግዚአብሔርን አመሰገነ፤ ልቡም ተጽናና።
በኢየሩሳሌም የነበሩ ሐዋርያትም የሰማርያ ሰዎች የእግዚአብሔርን ቃል እንደ ተቀበሉ በሰሙ ጊዜ ጴጥሮስንና ዮሐንስን ወደ እነርሱ ላኩላቸው።
ወደ አስባንያ ስሄድ እግረ መንገዴን ላያችሁ ተስፋ አደርጋለሁ፤ ቀደም ብዬ ከእናንተ ጋር ደስ ካለኝ በኋላም ከእናንተ ወደዚያ እሄዳለሁ።
እናንተም ወደምሄድበት ትሸኙኝ ዘንድ ምንአልባት የሆነውን ቀን ያህል በእናንተ ዘንድ እቈይ፥ ወይም እከርም ይሆናል።
በእናንተም በኩል ወደ መቄዶንያ እንዳልፍ፥ ዳግመኛም ከመቄዶንያ እንድመለስና እናንተም ደግሞ ወደ ይሁዳ ሀገር ትሸኙኝ ዘንድ መከርሁ።