Biblia Todo Logo
La Biblia Online
- Anuncios -




ሐዋርያት ሥራ 17:15 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

15 ጳው​ሎ​ስን የሸ​ኙት ሰዎ​ችም እስከ አቴና ከተማ ድረስ አብ​ረ​ውት መጥ​ተው ነበ​ርና ፈጥ​ነው ይከ​ተ​ሉት ዘንድ ወደ ሲላ​ስና ወደ ጢሞ​ቴ​ዎስ ላካ​ቸው፤ ተመ​ል​ሰ​ውም ሄዱ።

Ver Capítulo Copiar

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

15 ጳውሎስን የሸኙት ሰዎችም አቴና አደረሱት፤ ከዚያም ሲላስና ጢሞቴዎስ ወደ እርሱ በፍጥነት እንዲመጡ የሚል ትእዛዝ ተቀብለው ተመለሱ።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

15 ጳውሎስን የሸኙት ግን እስከ አቴና አደረሱት፤ እንደሚቻላቸውም በፍጥነት ወደ እርሱ ይመጡ ዘንድ ወደ ሲላስና ወደ ጢሞቴዎስ ትእዛዝ ተቀብለው ሄዱ።

Ver Capítulo Copiar

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

15 ጳውሎስን የሸኙት ሰዎች እስከ አቴና አደረሱት “ሲላስና ጢሞቴዎስ ሳይዘገዩ በቶሎ ወደ እኔ ይምጡልኝ” የሚለውንም የጳውሎስን ትእዛዝ ይዘው ወደ ቤርያ ተመለሱ።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

15 ጳውሎስን የሸኙት ግን እስከ አቴና አደረሱት፥ እንደሚቻላቸውም በፍጥነት ወደ እርሱ ይመጡ ዘንድ ወደ ሲላስና ወደ ጢሞቴዎስ ትእዛዝ ተቀብለው ሄዱ።

Ver Capítulo Copiar




ሐዋርያት ሥራ 17:15
11 Referencias Cruzadas  

ከቤተ ክር​ስ​ቲ​ያ​ንም በተ​ላኩ ጊዜ ወደ ሰማ​ር​ያና ወደ ፊንቄ ደር​ሰው አሕ​ዛብ ወደ ሃይ​ማ​ኖት እንደ ተመ​ለሱ ነገ​ሩ​ቸ​አ​ቸው፤ ወን​ድ​ሞ​ች​ንም ሁሉ እጅግ ደስ አሰ​ኙ​አ​ቸው።


ያን​ጊ​ዜም ወን​ድ​ሞች ጳው​ሎ​ስን ሸኝ​ተው ወደ ባሕር አደ​ረ​ሱት፤ ሲላ​ስና ጢሞ​ቴ​ዎስ ግን በዚ​ያው ቀሩ።


ጳው​ሎ​ስም በአ​ቴና ሆኖ ሲጠ​ብ​ቃ​ቸው ከተ​ማው ሁሉ ጣዖት ሲያ​መ​ልኩ ባየ ጊዜ ልቡ​ናው ተበ​ሳጨ።


የአ​ቴና ሰዎ​ችና በዚ​ያም የነ​በሩ እን​ግ​ዶች ሁሉ አዲስ ነገ​ርን ከመ​ና​ገ​ርና ከመ​ስ​ማት በቀር ሌላ ዐሳብ አል​ነ​በ​ራ​ቸ​ውም።


ጳው​ሎ​ስም በአ​ር​ዮ​ስ​ፋ​ጎስ ውስጥ ቆሞ እን​ዲህ አላ​ቸው፥ “እና​ንተ የአ​ቴና ሰዎች! በሥ​ራ​ችሁ ሁሉ አማ​ል​ክ​ትን ማም​ለክ እን​ደ​ም​ታ​በዙ አያ​ች​ኋ​ለሁ።


ከዚህ በኋላ ጳው​ሎስ ከአ​ቴና ወጥቶ ወደ ቆሮ​ን​ቶስ ሄደ።


ሲላ​ስና ጢሞ​ቴ​ዎ​ስም ከመ​ቄ​ዶ​ንያ በወ​ረዱ ጊዜ ጳው​ሎስ፥ ኢየ​ሱስ እርሱ ክር​ስ​ቶስ እንደ ሆነ ለአ​ይ​ሁድ እየ​መ​ሰ​ከረ ቃሉን በማ​ስ​ተ​ማር ይተጋ ነበር።


ስለዚህ ወደ ፊት እንታገሥ ዘንድ ባልተቻለን ጊዜ፥ በአቴና ብቻችንን ልንቀር በጎ ፈቃዳችን ሆነ።


አርጢሞንን ወይም ቲኪቆስን ወደ አንተ ስልክ፥ ወደ ኒቆጵልዮን ወደ እኔ እንድትመጣ ትጋ፤ በዚያ ልከርም ቈርጫለሁና።


Síguenos en:

Anuncios


Anuncios


¡Síguenos en WhatsApp! Síguenos