Biblia Todo Logo
La Biblia Online
- Anuncios -




ሮሜ 15:24 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

24 ወደ አስ​ባ​ንያ ስሄድ እግረ መን​ገ​ዴን ላያ​ችሁ ተስፋ አደ​ር​ጋ​ለሁ፤ ቀደም ብዬ ከእ​ና​ንተ ጋር ደስ ካለኝ በኋ​ላም ከእ​ና​ንተ ወደ​ዚያ እሄ​ዳ​ለሁ።

Ver Capítulo Copiar

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

24 ይህን ዕቅድ ወደ እስጳንያ በምሄድበት ጊዜ ልፈጽመው ዐስባለሁ። በማልፍበትም ጊዜ ልጐበኛችሁና ከእናንተ ጋራ ለጥቂት ጊዜ ቈይቼ ናፍቆቴን ከተወጣሁ በኋላ በጕዞዬ እንደምትረዱኝ ተስፋ አደርጋለሁ።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

24 ወደ ስፔን በምሄድበት ጊዜ፥ ከእናንተ ጋር ተደስቼ ጥቂት ካሳላፍሁ በኋላ በጉዞዬ እንድትረዱኝ ሳልፍ ላያችሁ ተስፋ አደርጋለሁ።

Ver Capítulo Copiar

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

24 ወደ እስፔን በምሄድበት ጊዜ እግረ መንገዴን ልጐበኛችሁ ዐቅጃለሁ። ለጥቂት ጊዜ ከእናንተ ጋር ደስ ብሎኝ ከቈየሁ በኋላ ጒዞዬን ለመቀጠል የሚያስችለኝን ርዳታ እንደምታደርጉልኝ ተስፋ አደርጋለሁ።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

24 ወደ እስጳንያ በሄድሁ ጊዜ ሳልፍ እናንተን እንዳይ፥ አስቀድሜም ጥቂት ብጠግባችሁ ወደዚያ በጉዞዬ እንድትረዱኝ ተስፋ አደርጋለሁ።

Ver Capítulo Copiar




ሮሜ 15:24
9 Referencias Cruzadas  

ከቤተ ክር​ስ​ቲ​ያ​ንም በተ​ላኩ ጊዜ ወደ ሰማ​ር​ያና ወደ ፊንቄ ደር​ሰው አሕ​ዛብ ወደ ሃይ​ማ​ኖት እንደ ተመ​ለሱ ነገ​ሩ​ቸ​አ​ቸው፤ ወን​ድ​ሞ​ች​ንም ሁሉ እጅግ ደስ አሰ​ኙ​አ​ቸው።


ይህም ከተ​ፈ​ጸመ በኋላ ጳው​ሎስ በመ​ቄ​ዶ​ን​ያና በአ​ካ​ይያ በኩል አልፎ ወደ ኢየ​ሩ​ሳ​ሌም ሊሄድ በልቡ ዐሰበ፥ “እዚ​ያም ከደ​ረ​ስሁ በኋላ ሮሜን ላያት ይገ​ባ​ኛል” አለ።


ከዚ​ህም በኋላ ለመ​ሄድ ወጣን፤ ሁሉም ከሚ​ስ​ቶ​ቻ​ቸ​ውና ከል​ጆ​ቻ​ቸው ጋር እስከ ከተ​ማው ውጭ ሸኙን፤ በባ​ሕ​ሩም ዳር ተን​በ​ር​ክ​ከን ጸለ​ይን።


ይህ​ንም ማለቴ በመ​ካ​ከ​ላ​ችን ባለች በእ​ና​ን​ተና በእኔ እም​ነት አብ​ረን በእ​ና​ንተ እን​ድ​ን​ጽ​ናና ነው።


እን​ግ​ዲህ ይህን ፍሬ ጨር​ሼና አትሜ በእ​ና​ንተ በኩል ወደ አስ​ባ​ንያ እሄ​ዳ​ለሁ።


በእ​ና​ን​ተም በኩል ወደ መቄ​ዶ​ንያ እን​ዳ​ልፍ፥ ዳግ​መ​ኛም ከመ​ቄ​ዶ​ንያ እን​ድ​መ​ለ​ስና እና​ን​ተም ደግሞ ወደ ይሁዳ ሀገር ትሸ​ኙኝ ዘንድ መከ​ርሁ።


እነርሱም በማኅበር ፊት ስለ ፍቅርህ መስክረዋል፤ ለእግዚአብሔር እንደሚገባ አድርገህ በጉዞአቸው ብትረዳ መልካም ታደርጋለህ፤


Síguenos en:

Anuncios


Anuncios


¡Síguenos en WhatsApp! Síguenos