ስለዚህ፥ እነሆ፥ ነቢያትንና ጥበበኞችን ጻፎችንም ወደ እናንተ እልካለሁ፤ ከእነርሱም ትገድላላችሁ ትሰቅሉማላችሁ፥ ከእነርሱም በምኵራባችሁ ትገርፋላችሁ ከከተማም ወደ ከተማ ታሳድዳላችሁ፤
ሐዋርያት ሥራ 11:27 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ያንጊዜም ነቢያት ከኢየሩሳሌም ወደ አንጾኪያ ወረዱ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም በዚህ ጊዜ አንዳንድ ነቢያት ከኢየሩሳሌም ወደ አንጾኪያ ወረዱ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) በዚያም ወራት ነቢያት ከኢየሩሳሌም ወደ አንጾኪያ ወረዱ፤ አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም በዚያን ጊዜ አንዳንድ ነቢያት ተብለው የሚጠሩ መምህራን ከኢየሩሳሌም ወደ አንጾኪያ ሄዱ፤ መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) በዚያም ወራት ነቢያት ከኢየሩሳሌም ወደ አንጾኪያ ወረዱ፤ |
ስለዚህ፥ እነሆ፥ ነቢያትንና ጥበበኞችን ጻፎችንም ወደ እናንተ እልካለሁ፤ ከእነርሱም ትገድላላችሁ ትሰቅሉማላችሁ፥ ከእነርሱም በምኵራባችሁ ትገርፋላችሁ ከከተማም ወደ ከተማ ታሳድዳላችሁ፤
ስለዚህ የእግዚአብሔር ጥበቡ እንዲህ አለች፦ እነሆ፥ እኔ ነቢያትንና ሐዋርያትን ወደ እነርሱ እልካለሁ፤ ከእነርሱም ይገድላሉ፤ ያሳድዳሉም።
ከመካከላቸውም ወደ አንጾኪያ ሄደው ለአረማውያን የጌታችን የኢየሱስ ክርስቶስን ነገር ያስተማሩ የቆጵሮስና የቄሬና ሰዎች ነበሩ።
ስለ እነርሱ የተነገረውም ይህ ነገር በኢየሩሳሌም ባለችው ቤተ ክርስቲያን ዘንድ ተሰማ፤ በርናባስንም ወደ አንጾኪያ ላኩት።
በአንጾኪያ በነበረችው ቤተ ክርስቲያንም ነቢያትና መምህራን ነበሩ፤ እነርሱም በርናባስ፥ ኔጌር የተባለው ስምዖን፥ የቀሬናው ሉቅዮስ፥ ከአራተኛው ክፍል ገዢ ከሄሮድስ ጋር ያደገው ምናሔ፥ ሳውልም ነበሩ።
ከዚህም በኋላ ሐዋርያትና ቀሳውስት ሕዝቡም ሁሉ ከጳውሎስና ከበርናባስ ጋር ወደ አንጾኪያ የሚልኳቸውን ሰዎች ይመርጡ ዘንድ ተስማሙ፤ ከባልንጀሮቻቸው መካከልም የተማሩትን ሰዎች በርናባስ የተባለ ይሁዳንና ሲላስን መረጡ።
በኋለኛዪቱ ቀን እንዲህ ይሆናል ይላል እግዚአብሔር፦ ሥጋን በለበሰ ሁሉ ላይ ከመንፈሴ አፈስሳለሁ፤ ወንዶች ልጆቻችሁና ሴቶች ልጆቻችሁ ትንቢት ይናገራሉ፤ ጐልማሶቻችሁ ራእይን ያያሉ፤ ሽማግሌዎቻችሁም ሕልምን ያልማሉ።
በዚያም ደቀ መዛሙርትን አገኘንና በእነርሱ ዘንድ ሰባት ቀን ተቀመጥን፤ እነርሱም በመንፈስ ቅዱስ ተገልጾላቸው ጳውሎስን ወደ ኢየሩሳሌም እንዳይወጣ ነገሩት።
ይህም ነገር በእነርሱ ዘንድ የተወደደ ሆነ፤ ሃይማኖቱ የቀናና መንፈስ ቅዱስ ያደረበትን ሰው እስጢፋኖስን፥ ፊልጶስን፥ ጵሮኮሮስን፥ ኒቃሮናን፥ ጢሞናን፥ ጰርሜናን፥ ወደ ይሁዲነት የተመለሰውን የአንጾኪያውን ኒቆላዎስንም መረጡ።
ለአንዱም ተአምራትን ማድረግ፥ ለአንዱም ትንቢትን መናገር፥ ለአንዱም መናፍስትን መለየት፥ ለአንዱም በልዩ ዓይነት ልሳን መናገር፥ ለአንዱም በልሳኖች የተነገረውን መተርጐም ይሰጠዋል።
እግዚአብሔር ለቤተ ክርስቲያን የሾማቸው አስቀድሞ ሐዋርያትን፥ ሁለተኛም ነቢያትን፥ ሦስተኛም መምህራንን፥ ከዚህም በኋላ ተአምራትና ኀይል ማድረግ የተሰጣቸውን፥ ቀጥሎም የመፈወስ ሀብት የተሰጣቸውን፥ የመርዳትም ሀብት የተሰጣቸውን፥ የመምራትና ቋንቋን የመናገር ሀብት የተሰጣቸውን ነው።
እርሱም ጸጋን ሰጠ፤ ከቤተ ሰቦቹም ሐዋርያትን፥ ከእነርሱም ነቢያትንና የወንጌል ሰባኪዎችን፥ ጠባቂዎችንና መምህራንን ሾመ።