Biblia Todo Logo
La Biblia Online

- Anuncios -




ሐዋርያት ሥራ 14:26 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

26 ከዚ​ያም ስለ​ሚ​ሠ​ሩት ሥራ ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ጸጋ አደራ ወደ ተሰ​ጡ​በት ወደ አን​ጾ​ኪያ በመ​ር​ከብ ሄዱ።

Ver Capítulo Copiar

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

26 ከአጣልያም፣ እስካሁን ላከናወኑት ሥራ፣ ለእግዚአብሔር ጸጋ በዐደራ ወደ ተሰጡባት ከተማ ወደ አንጾኪያ በመርከብ ተመለሱ።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

26 ከዚያም ስለ ፈጸሙት ሥራ ለእግዚአብሔር ጸጋ አደራ ወደ ተሰጡበት ወደ አንጾኪያ በመርከብ ሄዱ።

Ver Capítulo Copiar

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

26 ከዚያም ስለ ፈጸሙት ሥራ ለእግዚአብሔር ጸጋ ዐደራ ወደ ተሰጡበት ወደ አንጾኪያ በመርከብ ሄዱ።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

26 ከዚያም ስለ ፈጸሙት ሥራ ለእግዚአብሔር ጸጋ አደራ ወደ ተሰጡበት ወደ አንጾኪያ በመርከብ ሄዱ።

Ver Capítulo Copiar




ሐዋርያት ሥራ 14:26
22 Referencias Cruzadas  

ጳው​ሎስ ግን ሲላ​ስን መረጠ፤ ወን​ድ​ሞ​ችም ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ጸጋ አደራ ከሰ​ጡት በኋላ ሄደ።


በእ​ስ​ጢ​ፋ​ኖስ ሞት ምክ​ን​ያት የተ​በ​ተ​ኑት ግን፤ ወደ ፊንቄ ወደ ቆጵ​ሮ​ስና ወደ አን​ጾ​ኪያ ደረሱ፤ ቃሉ​ንም ለአ​ይ​ሁድ ብቻ እንጂ ለአ​ን​ድስ እንኳ አይ​ና​ገ​ሩም ነበር።


አክ​ር​ጳ​ንም “ከእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር የተ​ሾ​ም​ህ​ባ​ትን መል​እ​ክ​ት​ህን እን​ድ​ት​ፈ​ጽ​ማት ተጠ​ን​ቀቅ” በሉት።


እር​ሱም ኢየ​ሱስ ክር​ስ​ቶ​ስን በማ​መን ፍጹም የሚ​ሆ​ነ​ውን ሰው እና​ቀ​ር​በው ዘንድ፥ እኛ የም​ና​ስ​ተ​ም​ር​ለት፥ ሰውን ሁሉ ወደ እርሱ የም​ን​ጠ​ራ​ለ​ትና የም​ን​ገ​ሥ​ጽ​ለት፥ ሥራ​ው​ንም በጥ​በብ ሁሉ የም​ን​ና​ገ​ር​ለት ነው።


ስለ እና​ንተ በሰ​ጠኝ በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ሥር​ዐት እኔ መል​እ​ክ​ተኛ ሆኜ የተ​ሾ​ም​ሁ​ላት።


በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ቸር​ነ​ትና ይቅ​ርታ መመ​ኪ​ያ​ች​ንና የነ​ፃ​ነ​ታ​ችን ምስ​ክር ይህቺ ናትና፥ በሥ​ጋዊ ጥበብ ሳይ​ሆን፥ በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ጸጋ በዚህ ዓለም፥ ይል​ቁ​ንም በእ​ና​ንተ ዘንድ ተመ​ላ​ለ​ስን።


በኀ​ይ​ልና በተ​አ​ም​ራት፥ በመ​ን​ፈስ ቅዱስ ኀይ​ልና ድንቅ ሥራን በመ​ሥ​ራ​ትም፥ ከኢ​የ​ሩ​ሳ​ሌም አው​ራ​ጃ​ዎች ጀምሬ እስከ እል​ዋ​ሪ​ቆን ድረስ እንደ አስ​ተ​ማ​ርሁ፥ የክ​ር​ስ​ቶ​ስ​ንም ወን​ጌል ፈጽሞ እንደ ሰበ​ክሁ እና​ገር ዘንድ እደ​ፍ​ራ​ለሁ።


በቤተ ክር​ስ​ቲ​ያ​ንም አንድ ዓመት አብ​ረው ተቀ​መጡ፤ ብዙ ሕዝ​ብ​ንም አስ​ተ​ማሩ፤ ደቀ መዛ​ሙ​ር​ትም መጀ​መ​ሪያ በአ​ን​ጾ​ኪያ ክር​ስ​ቲ​ያን ተብ​ለው ተጠሩ።


ቃሉን ስበክ፤ በጊዜውም አለጊዜውም ጽና፤ ፈጽመህ እየታገሥህና እያስተማርህ ዝለፍና ገሥጽ፤ ምከርም።


ነገር ግን ኬፋ ወደ አን​ጾ​ኪያ በመጣ ጊዜ ፊት ለፊት ተቃ​ወ​ም​ሁት፤ ነቅ​ፈ​ውት ነበ​ርና።


እነ​ር​ሱም ተል​ከው ወደ አን​ጾ​ኪያ ወረዱ፤ ሕዝ​ቡ​ንም ሰብ​ስ​በው የተ​ላ​ከ​ውን ደብ​ዳቤ ሰጡ​አ​ቸው።


አሁ​ንም ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርና ሊያ​ን​ጻ​ችሁ፥ በቅ​ዱ​ሳ​ንም ሁሉ መካ​ከል ርስ​ትን ሊሰ​ጣ​ችሁ ለሚ​ች​ለው ለጸ​ጋው ቃል አደራ ሰጥ​ቻ​ች​ኋ​ለሁ።


ከዚ​ህም በኋላ ሐዋ​ር​ያ​ትና ቀሳ​ው​ስት ሕዝ​ቡም ሁሉ ከጳ​ው​ሎ​ስና ከበ​ር​ና​ባስ ጋር ወደ አን​ጾ​ኪያ የሚ​ል​ኳ​ቸ​ውን ሰዎች ይመ​ርጡ ዘንድ ተስ​ማሙ፤ ከባ​ል​ን​ጀ​ሮ​ቻ​ቸው መካ​ከ​ልም የተ​ማ​ሩ​ትን ሰዎች በር​ና​ባስ የተ​ባለ ይሁ​ዳ​ንና ሲላ​ስን መረጡ።


ለቤተ ክር​ስ​ቲ​ያ​ንም ቀሳ​ው​ስ​ትን ሾሙ፤ ጾሙ፤ ጸለ​ዩም፤ ለሚ​ታ​መ​ኑ​በት ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም አደራ ሰጡ​አ​ቸው።


ከመ​ካ​ከ​ላ​ቸ​ውም ወደ አን​ጾ​ኪያ ሄደው ለአ​ረ​ማ​ው​ያን የጌ​ታ​ችን የኢ​የ​ሱስ ክር​ስ​ቶ​ስን ነገር ያስ​ተ​ማሩ የቆ​ጵ​ሮ​ስና የቄ​ሬና ሰዎች ነበሩ።


በደ​ረሰ ጊዜም የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ጸጋ አየና ደስ አለው፤ በፍ​ጹም ልባ​ቸ​ውም በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ጸን​ተው ይኖሩ ዘንድ መከ​ራ​ቸው።


ያን​ጊ​ዜም ነቢ​ያት ከኢ​የ​ሩ​ሳ​ሌም ወደ አን​ጾ​ኪያ ወረዱ።


አይ​ሁ​ድም ከአ​ን​ጾ​ኪ​ያና ከኢ​ቆ​ንያ መጡ፤ ልባ​ቸ​ው​ንም እን​ዲ​ያ​ጠ​ኑ​ባ​ቸው አሕ​ዛ​ብን አባ​በ​ሉ​አ​ቸው፤ ጳው​ሎ​ስ​ንም እየ​ጐ​ተቱ ከከ​ተማ ውጭ አው​ጥ​ተው በድ​ን​ጋይ ደበ​ደ​ቡት፤ የሞ​ተም መሰ​ላ​ቸው።


በዚ​ያ​ችም ከተማ ወን​ጌ​ልን ሰበኩ፤ ብዙ ሰዎ​ች​ንም ደቀ መዛ​ሙ​ርት አድ​ር​ገው ወደ ልስ​ጥ​ራን፥ ወደ ኢቆ​ን​ዮ​ንና ወደ አን​ጾ​ኪያ ተመ​ለሱ።


Síguenos en:

Anuncios


Anuncios