ኤልያስም ሕዝቡን አለ፥ “ከእግዚአብሔር ነቢያት አንድ እኔ ብቻ ቀርቻለሁ፤ የበዓል ነቢያት ግን አራት መቶ ሃምሳ ሰዎች ናቸው። የማምለኪያ ዐፀድ ነቢያትም አራት መቶ ናቸው።
2 ጢሞቴዎስ 4:3 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ሕይወት የሚገኝበትን ትምህርት የማይታገሡበት ዘመን ይመጣልና፤ ነገር ግን ጆሮቻቸውን የሚያሳክክ ስለ ሆነ፥ እንደ ገዛ ምኞታቸው ለራሳቸው አስተማሪዎችን ያከማቻሉ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ምክንያቱም ሰዎች ትክክለኛ የሆነውን ትምህርት የማይቀበሉበት ጊዜ ይመጣል፤ ከዚህ ይልቅ ለገዛ ምኞቶቻቸው የሚስማማውን፣ የሚያሳክክ ጆሯቸው ሊሰማ የሚፈልገውን እንዲነግሯቸው በዙሪያቸው ብዙ አስተማሪዎችን ይሰበስባሉ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ሰዎች እውነተኛውን ትምህርት የማይታገሱበት፤ ይልቁንም ጆሮዎቻቸውን የሚኮረኩራቸውን ነገር በመሻት ለራሳቸው ምኞት የሚመቹ አስተማሪዎችን የሚሰበስቡበት ጊዜ ይመጣልና። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ሰዎች ሕይወት የሚገኝበትን ትምህርት ለመስማት የማይፈልጉበት ጊዜ ይመጣል፤ ነገር ግን ለወሬ በመጐምጀት እነርሱ ራሳቸው የሚወዱትን ነገር የሚነግሩአቸውን አስተማሪዎች ይሰበስባሉ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ሕይወት የሚገኝበትን ትምህርት የማይታገሡበት ዘመን ይመጣልና፤ ነገር ግን ጆሮቻቸውን የሚያሳክክ ስለ ሆነ፥ እንደ ገዛ ምኞታቸው ለራሳቸው አስተማሪዎችን ያከማቻሉ። |
ኤልያስም ሕዝቡን አለ፥ “ከእግዚአብሔር ነቢያት አንድ እኔ ብቻ ቀርቻለሁ፤ የበዓል ነቢያት ግን አራት መቶ ሃምሳ ሰዎች ናቸው። የማምለኪያ ዐፀድ ነቢያትም አራት መቶ ናቸው።
የእስራኤልም ንጉሥ ኢዮሣፍጥን፥ “እግዚአብሔርን የምንጠይቅበት የይምላ ልጅ ሚክያስ የሚባል አንድ ሰው አለ፤ ነገር ግን ክፉ እንጂ መልካም አይናገርልኝምና እጠላዋለሁ” አለው። የይሁዳ ንጉሥ ኢዮሣፍጥም፥ “ንጉሥ እንዲህ አይበል” አለ።
እነርሱም፥ “ሕግ ከካህን፥ ምክርም ከጠቢብ፥ ቃልም ከነቢይ አይጠፋምና ኑ፤ በኤርምያስ ላይ ምክርን እንምከር። ኑ፤ በምላስ እንምታው፤ ቃሉንም ሁሉ አናዳምጥ” አሉ።
እናንተ ግን፦ ለባቢሎን ንጉሥ አትገዙም የሚሉአችሁን የሐሰት ነቢያቶቻችሁንና ምዋርተኞቻችሁን፥ ሕልም ዐላሚዎቻችሁንና ባለ ራእዮቻችሁን፥ መተተኞቻችሁንም አትስሙ፤
የእስራኤልም አምላክ የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላልና፥ “በመካከላችሁ ያሉት የሐሰት ነቢያቶቻችሁና ምዋርተኞቻችሁ አያታልሉአችሁ፤ ሕልም አላሚዎች አለምንላችሁ የሚሉአችሁን አትስሙ፥
ነቢያት በሐሰት ትንቢት ይናገራሉ፥ ካህናትም በእጃቸው ያጨበጭባሉ፥ ሕዝቤም እንዲህ ያለውን ነገር ይወድዳሉ፤ በፍጻሜውስ ምን ታደርጋላችሁ?
ያን ጊዜም የካህናት አለቆችና ጻፎች ሊይዙት ወደዱ፤ ይህን ስለ እነርሱ እንደ መሰለ ዐውቀዋልና፤ ነገር ግን ሕዝቡን ፈሩአቸው።
ሰዎች ሁሉ ስለ እናንተ መልካሙን ነገር ቢናገሩላችሁ ወዮላችሁ፥ አባቶቻቸው ለሐሰተኞች ነቢያት እንዲህ ያደርጉ ነበርና።
የአቴና ሰዎችና በዚያም የነበሩ እንግዶች ሁሉ አዲስ ነገርን ከመናገርና ከመስማት በቀር ሌላ ዐሳብ አልነበራቸውም።
ወንድሞቻችን ሆይ፥ እኔም ወደ እናንተ በመጣሁ ጊዜ በማባበልና ነገርን በማራቀቅ የእግዚአብሔርን ትምህርት ላስተምራችሁ የመጣሁ አይደለም።