ቍጣቸው ርጉም ይሁን፤ ጽኑ ነበርና፤ ኵርፍታቸውም ብርቱ ነበርና፤ በያዕቆብ እከፋፍላቸዋለሁ፤ በእስራኤልም እበታትናቸዋለሁ።
2 ጢሞቴዎስ 3:3 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ፍቅር የሌላቸው፥ ዕርቅን የማይሰሙ፥ ሐሜተኞች፥ ራሳቸውን የማይገዙ፥ ጨካኞች፥ መልካም የሆነውን የማይወዱ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም ፍቅር የሌላቸው፣ ለዕርቅ የማይሸነፉ፣ ሐሜተኞች፣ ራሳቸውን የማይገዙ፣ ጨካኞች፣ መልካም የሆነውን የማይወድዱ፣ መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ፍቅር የሌላቸው፥ ዕርቅን የማይሰሙ፥ ሐሜተኞች፥ ራሳቸውን የማይቈጣጠሩ፥ ጨካኞች፥ መልካም የሆነውን የማይወዱ፥ አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ፍቅር የሌላቸው፥ ይቅርታ የማያደርጉ፥ የሰው ስም የሚያጠፉ፥ ራሳቸውን የማይቈጣጠሩ፥ ጨካኞች፥ መልካም የሆነውን ነገር የሚጠሉ፥ መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ቅድስና የሌላቸው፥ ፍቅር የሌላቸው፥ ዕርቅን የማይሰሙ፥ ሐሜተኞች፥ ራሳቸውን የማይገዙ፥ ጨካኞች፥ መልካም የሆነውን የማይወዱ፥ |
ቍጣቸው ርጉም ይሁን፤ ጽኑ ነበርና፤ ኵርፍታቸውም ብርቱ ነበርና፤ በያዕቆብ እከፋፍላቸዋለሁ፤ በእስራኤልም እበታትናቸዋለሁ።
መልኩም የተናቀ፥ ከሰውም ልጆች ሁሉ የተዋረደ፥ የተገረፈ ሰው፥ መከራንም የተቀበለ ነው፤ ፊቱንም መልሶአልና አቃለሉት፥ አላከበሩትምም።
የአስጨናቂዎችሽም ልጆች እየተንቀጠቀጡ ወደ አንቺ ይመጣሉ፤ የናቁሽም ሁሉ ወደ እግርሽ ጫማ ይሰግዳሉ፤ የእስራኤል ቅዱስ የእግዚአብሔር ከተማ፥ ጽዮን ተብለሽም ትጠሪያለሽ።
“እናንተን የሚሰማ እኔን ይሰማል፤ እናንተንም እንቢ የሚል እኔን እንቢ ይላል፤ እኔንም እንቢ የሚል የላከኝን እንቢ ይላል፤ እኔንም የሚሰማ የላከኝን ይሰማል።”
ጌታችን ኢየሱስም መልሶ እንዲህ አላቸው፥ “እኔ እናንተን ዐሥራ ሁለታችሁን መርጫችሁ የለምን? ነገር ግን ከእናንተ አንዱ ሰይጣን ነው።”
እነርሱም ዐመፅን ሁሉ፥ ክፋትንም፥ ምኞትንም፥ ቅሚያንም፥ ቅናትንም የተመሉ ናቸው፤ ምቀኞች፥ ነፍሰ ገዳዮች፥ ከዳተኞች፥ ተንኰለኞች፥ ኩሩዎች፥ ጠባያቸውንና ግብራቸውንም ያከፉ ናቸው።
ለጸሎት እንድትተጉ ከምትስማሙበት ጊዜ ብቻ በቀር፥ ባልና ሚስት አትለያዩ፤ ዳግመኛ ሰይጣን ድል እንዳያደርጋችሁ በአንድነት ኑሩ፤ ሰውነታችሁ ደካማ ነውና ።
እንዲሁም አሮጊቶች ሴቶች አካሄዳቸው ለቅዱስ አገልግሎት የሚገባ፥ የማያሙ፥ ለብዙ ወይን ጠጅ የማይገዙ፥ በጎ የሆነውን ነገር የሚያስተምሩ ይሁኑ፤
ምንዝር የሞላባቸው ኀጢአትንም የማይተዉ ዐይኖች አሉአቸው፤ የማይጸኑትን ነፍሳት ያታልላሉ፤ መመኘትን የለመደ ልብ አላቸው፤ የተረገሙ ናቸው።
እነዚህ እንደ ምኞታቸው እየሄዱ የሚያንጎራጉሩና ስለ ዕድላቸው የሚያጕረመርሙ ናቸው፤ እንዲረባቸውም ለሰው ፊት እያደሉ አፋቸው ከመጠን ይልቅ ታላቅ ቃል ይናገራል።