Biblia Todo Logo
La Biblia Online

- Anuncios -




ዮሐንስ 6:70 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

70 ጌታ​ችን ኢየ​ሱ​ስም መልሶ እን​ዲህ አላ​ቸው፥ “እኔ እና​ን​ተን ዐሥራ ሁለ​ታ​ች​ሁን መር​ጫ​ችሁ የለ​ምን? ነገር ግን ከእ​ና​ንተ አንዱ ሰይ​ጣን ነው።”

Ver Capítulo Copiar

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

70 ኢየሱስም መልሶ፣ “ዐሥራ ሁለታችሁንም የመረጥኋችሁ እኔ አይደለሁምን? ነገር ግን ከእናንተ አንዱ ዲያብሎስ ነው!” አላቸው።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

70 ኢየሱስም “እኔ እናንተን ዐሥራ ሁለታችሁን መርጫችሁ የለምን? ከእናንተም አንዱ ዲያብሎስ ነው፤” ብሎ መለሰላቸው።

Ver Capítulo Copiar

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

70 ኢየሱስም “እናንተን ዐሥራ ሁለታችሁን መርጬአችሁ የለምን? ነገር ግን ከእናንተ አንዱ ዲያብሎስ ነው” አላቸው።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

70 ኢየሱስም፦ እኔ እናንትን አሥራ ሁለታችሁን የመረጥኋችሁ አይደለምን? ከእናንተም አንዱ ዲያብሎስ ነው ብሎ መለሰላቸው።

Ver Capítulo Copiar




ዮሐንስ 6:70
21 Referencias Cruzadas  

እን​ጀ​ራ​ው​ንም ከተ​ቀ​በለ በኋላ ወዲ​ያ​ውኑ በይ​ሁዳ ልብ ሰይ​ጣን አደ​ረ​በት፤ ጌታ​ችን ኢየ​ሱ​ስም፥ “እን​ግ​ዲህ የም​ታ​ደ​ር​ገ​ውን ፈጥ​ነህ አድ​ርግ” አለው።


ራት ሲበ​ሉም አሳ​ልፎ ይሰ​ጠው ዘንድ በስ​ም​ዖን ልጅ በአ​ስ​ቆ​ሮቱ ሰው በይ​ሁዳ ልብ ሰይ​ጣን አደረ።


እኔ በዓ​ለም ከእ​ነ​ርሱ ጋር ሳለሁ ግን የሰ​ጠ​ኸ​ኝን በስ​ምህ እጠ​ብ​ቃ​ቸው ነበር፤ ጠበ​ቅ​ኋ​ቸ​ውም፤ የመ​ጽ​ሐ​ፉም ቃል ይፈ​ጸም ዘንድ ከጥ​ፋት ልጅ በቀር ከእ​ነ​ርሱ አንድ ስን​ኳን አል​ጠ​ፋም።


ነገር ግን ይህን የም​ና​ገር ስለ ሁላ​ችሁ አይ​ደ​ለም፤ የመ​ረ​ጥ​ኋ​ቸው እነ​ማን እንደ ሆኑ እኔ አው​ቃ​ለሁ፤ ነገር ግን መጽ​ሐፍ ‘እን​ጀ​ራ​ዬን የሚ​መ​ገብ ተረ​ከ​ዙን በእኔ ላይ አነሣ’ ያለው ይፈ​ጸም ዘንድ ነው።


ነገር ግን ከእ​ና​ንተ ውስጥ የማ​ያ​ምኑ አሉ፤” ጌታ​ችን ኢየ​ሱስ ከጥ​ንት ጀምሮ የማ​ያ​ም​ኑ​በት እነ​ማን እንደ ሆኑ፥ የሚ​ያ​ሲ​ዘ​ውም ማን እንደ ሆነ ያውቅ ነበ​ርና።


ኃጢአትን የሚያደርግ ከዲያብሎስ ነው፥ ዲያብሎስ ከመጀመሪያ ኃጢአትን ያደርጋልና።


እንዲሁም ሴቶች ጭምቶች፥ የማያሙ፥ ልከኞች፥ በነገር ሁሉ የታመኑ ሊሆኑ ይገባቸዋል።


እር​ሱም ከእኛ ጋር ተቈ​ጥሮ ነበር፤ ለዚ​ህም አገ​ል​ግ​ሎት ታድሎ ነበር።


እና​ን​ተስ ከዓ​ለም ብት​ሆኑ ዓለም በወ​ደ​ዳ​ችሁ ነበር፤ ዓለም ወገ​ኖ​ቹን ይወ​ዳ​ልና፤ ነገር ግን እኔ ከዓ​ለም መረ​ጥ​ኋ​ችሁ እንጂ እና​ንተ ከዓ​ለም አይ​ደ​ላ​ች​ሁ​ምና ስለ​ዚህ ዓለም ይጠ​ላ​ች​ኋል።


እኔ መረ​ጥ​ኋ​ችሁ እንጂ እና​ንተ የመ​ረ​ጣ​ች​ሁኝ አይ​ደ​ለም፤ እን​ድ​ት​ሄዱ፥ ፍሬም እን​ድ​ታ​ፈሩ፥ ፍሬ​አ​ች​ሁም እን​ዲ​ኖር፤ አብ​ንም በስሜ የም​ት​ለ​ም​ኑት ነገር ቢኖር ሁሉን እን​ዲ​ሰ​ጣ​ችሁ ሾም​ኋ​ችሁ።


ይህ​ንም ተና​ግሮ ጌታ​ችን ኢየ​ሱስ በልቡ አዘነ፤ መሰ​ከረ፤ እን​ዲ​ህም አለ፥ “እው​ነት እው​ነት እላ​ች​ኋ​ለሁ፤ ከእ​ና​ንተ አንዱ አሳ​ልፎ ይሰ​ጠ​ኛል።”


እና​ን​ተስ ከአ​ባ​ታ​ችሁ ከሰ​ይ​ጣን ናችሁ፤ የአ​ባ​ታ​ች​ሁ​ንም ፈቃድ ልታ​ደ​ርጉ ትወ​ዳ​ላ​ችሁ፤ እርሱ ከጥ​ንት ጀምሮ ነፍሰ ገዳይ ነው፤ በእ​ው​ነ​ትም አይ​ቆ​ምም፤ በእ​ርሱ ዘንድ እው​ነት የለ​ምና፤ ሐሰ​ት​ንም በሚ​ና​ገ​ር​በት ጊዜ ከራሱ አን​ቅቶ ይና​ገ​ራል፤ ሐሰ​ተኛ ነውና፤ የሐ​ሰ​ትም አባት ነውና።


እንዲሁም አሮጊቶች ሴቶች አካሄዳቸው ለቅዱስ አገልግሎት የሚገባ፥ የማያሙ፥ ለብዙ ወይን ጠጅ የማይገዙ፥ በጎ የሆነውን ነገር የሚያስተምሩ ይሁኑ፤


እን​ዲ​ህም አለው፥ “ሽን​ገ​ላ​ንና ክፋ​ትን ሁሉ የተ​መ​ላህ፥ የሰ​ይ​ጣን ልጅ፥ የጽ​ድቅ ሁሉ ጠላት ሆይ፥ የቀ​ና​ውን የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን መን​ገድ ማጣ​መ​ም​ህን ትተው ዘንድ እንቢ አል​ህን?


ጌታ​ችን ኢየ​ሱ​ስና ደቀ መዛ​ሙ​ር​ቱም ወደ ሰርጉ ታደሙ።


ጌታ​ችን ኢየ​ሱ​ስም ዐሥራ ሁለ​ቱን፥ “እና​ንተ ደግሞ ልት​ሄዱ ትሻ​ላ​ች​ሁን?” አላ​ቸው።


ይህ​ንም ስለ ስም​ዖን ልጅ ስለ አስ​ቆ​ሮ​ታ​ዊው ይሁዳ ተና​ገረ፤ እርሱ ያሲ​ዘው ዘንድ አለ​ውና፤ እር​ሱም ከዐ​ሥራ ሁለቱ አንዱ ነበር።


ጌታ​ችን ኢየ​ሱስ በመጣ ጊዜ ዲዲ​ሞስ የሚ​ሉት ከዐ​ሥራ ሁለቱ ደቀ መዛ​ሙ​ርት አንዱ ቶማስ ከደቀ መዛ​ሙ​ርቱ ጋር አል​ነ​በ​ረም።


Síguenos en:

Anuncios


Anuncios